Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Axumezana
Senior Member
Posts: 13485
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

The Ethiopian Orthodox Church has played key role in the continuity of Ethiopia but it requires reformation!

Post by Axumezana » 26 Jan 2023, 00:49

The binding glue in the unity & continuity of Ethiopia has been the Ethiopian Orthodox Church . Any split within this church will further divide and weaken Ethiopia and exposes it to attacks from the strategic enemies of Ethiopia including Isaias, Egypt and the Arabs. However, the church has been polluted by teachings( most of them related to teachings in the አዋልድ መፅሀፎች which are included in the Chruch teachings in violation to the ፍትሀ፥ ነገስት፥ guidelines )related to worship of idols ( paints and so called tabot) , worship of saints including in the name of Mery, Arsema, worship of Angles including in the name of Gabriel, Michael etc, demonic teachings related to አስማት & ድግምት which are high level and deeper relationship with the satanic spirits . If you compare Hinduism and the Ethiopian Orthodox Church you will find similarities.Therefore what the Chruch requires is not divisive leaders but transformative and reformative leaders like Moses that shall reposition & take it toward the destiny that God has bestowed on it.

Horus
Senior Member+
Posts: 30837
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The Ethiopian Orthodox Church's has played key role in the continuity of Ethiopia but it requires reformation!

Post by Horus » 26 Jan 2023, 01:19

አቶ አክሱመዛን፣
እንዲያው በውል በማታውቀው ነገር ላይ እንዲህ አፍህን ሞልተህ መናገርህ ስላስገረመኝ ነው ይህን አስተያየት የማደርገው ። አንተ እንደ ሰው ፍጡር በግድ በሆነ ነገር ታምንለህ፤ ያ የምታምነው ነገር ምን እንደ ሆነ ባላውቅም ። በእግዜአብሄር (ጎድ) ነው የማምነው የምትል ከሆነ እግዚአብሄር ምንድን ነው? ያ አንተ የምታምነው ጎድ እሱ መሆኑን በምን አወቅክ? ማመን ማወቅ ነው ። የምታምነው ነገር ምን እንደ ሆነ ሳታውቀው ከሆነ እንዴት የማታውቀውን ነገር ነው፣ ህያው ነው፣ አለ ፣ እሱ ነው ብላህ ታምናለህ? አይ የማምነው አምላክ የተጻፈ፣ የተነገረ ነው ካልክ ደሞ የምታምነው የተጻፈው ቃል፣ ምልክቱ፣ ምስሉ፣ ስዕሉ ነው እንጂ አግዚአብሄርን በአይንህ አይተህው በእጅህ ነክተሃው፣ ዳስሰሀው አይደለም ። ታቦት ማለት የእግዚአብሄር ምልክት፣ የፈጣሪ ማስታውሻ ምስል ማለት ነው ። ኦርቶዶክስ እጅግ ረቂቅ የዘመኑን ኮግኒቲቭ ሳይንስ የተጠጋ ዶክትሪን ነው ያላት ። የሰው አይምሮ አለ ምስል ፣ አለ ምልክት፣ አለ ምሳሌ ምንም ነገር ሊያስብ፣ ሊያውቅ ሊገነዘብ አይችልም! ቋንቋ ምስል ነው! ቃል ምስል ነው! ቃል ምልክት ነው! ቃል ታቦት ነው! ቃል ጣኦት ነው ። በመጀምሪያ ቃል ነበረ ! ስለዚህ በጥሞና ስህተትክን አርም! በአይን በሚታይና በሚዳሰስ ቁሰ አካል ማመን ትችላለህ፣ በዛፍ፣ በድንጋይ፣ በተራራ ፣ እነሱ ከከርስትናና እስልምና በፊት የነበሩ ፓጋኖች ናቸው ። ካሻህ ያንን አምልክ ። ከዚያ ባለፈ የሰው አይምሮ ፈጣሪ የሚባለውን ኃይል ማወቅ የሚችለው በምስል በታቦት በስዕል! ይህ ዛሬ የመጨረሻው ኮኚቲቭ ሳይንስ ያረጋገጠው ጉዳይ ነው ።

Axumezana
Senior Member
Posts: 13485
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: The Ethiopian Orthodox Church has played key role in the continuity of Ethiopia but it requires reformation!

Post by Axumezana » 26 Jan 2023, 02:01

አለቃ፥ ሆረስ፤

አንድ፥ ክርስትያን፥ የእግዚአብሔር፥ የሆነውና፥ ያልሆነውን፥ የሚለየው፥ በመጽሀፍ፥ ቅዱስ፥ ከተፃፈው፥ ጋር፥ በማነፃፀርና፥ በተረዳው፥ መጠን፥ ነው። እንዳልከው፥ ግን፥ ዞሮ፥ ዞሮ፥ የእምነት፥ ጉዳይ፥ በየግለሰቡ፥ conviction ላይ የተመሰረተ፥ መንፈሳዊ፥ ጉዳይ፥ እንጂ፥ በአካል፥ የሚዳሰስና፥ የሚጨበጥ፥ አይደለም፤ የማልስማማው፥ ቃልን፥ የተሮጎምክበት፥ አባባል፥ ነው። ቃል፥ ሃሳብን፥ የሚገልፅ፥ ትርጉም፥ ያለው፥ ድምፅ፥ ነው፥ አይታይም፥ አይዳሰስም፥ሃሳብ/ ቃል፥ በፅሁፍ ወይም፥ በምልክት፥ ይገለጣል፥ ግን፥ ቃሉና፥ ምልክቱ፥ አንድ፥አይደሉም፥ጣኦት፥ ሃሳብ፥ በቅብ/በምስል ወይም፥ በቅርፅ፥ ተገልፆ፥ በሚታይና፥ በሚዳሰስ፥ መልኩ፥ ለአምልኮ፥ይውላል።እርግጥ፥ ከሃሳቡ፥ከቅቡ፥ ወይም፥ ከቅርፁ፥ በስተጀርባ፥ የሚሰራው፥መንፈስ፥ አይታይም፥ አይዳሰስም( በመንፈሳዊ፥ አይን፥ ብቻ፥ ነው፥ የሚታየው፥)። ክርስትና፥ ጣኦታዊ፥ አምልኮን፥ በሃሳብም፥ በምስልም፥በቅርፅም፥ ይከለክላል። በክርስትና፥ እምነት፥ አንድ ሀሳብ፥ ወይም፥ ቃል፥ ከእግዚአብህሔር፥ ወይም፥ ከሰይጣን፥ ወይም፥ ከሰው፥ ሊመነጭ፤ ይችላል፥ የእግዚአብህሔር፥ መሆኑና፥ አለመሆኑን፥ ክርስትያን፥ የሚለየው፥ ከላይ፥ እንደገለፅኩት፥ በመጽሀፍ፥ ቅዱስ፥ ከተፃፈው፥ ጋር፥ በማነፃፀርና፥ በተረዳው፥ መጠን፥ ነው። ክርስትና፥ የሚያስተምረው፥ የእግዚአብሔር፥ መንገድ፥ አንድና፥ ጠባብ፥ መሆኑን፥ ነው፥ ከሌሎች፥ እምነቶች፥ በዚህ፥ ይለያል።
Last edited by Axumezana on 26 Jan 2023, 02:43, edited 5 times in total.


Horus
Senior Member+
Posts: 30837
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The Ethiopian Orthodox Church has played key role in the continuity of Ethiopia but it requires reformation!

Post by Horus » 26 Jan 2023, 02:54

አቶ አክሱማኢዛና፣
የጀመርከውን መተንተን ትንሽ ብትቀጥልበት ኖሮ እኔ ያልኩ መደምደሚያ ላይ ትደርስ ነበር ። ቶሎ አቆምክ እንጂ! አንተም እንዳልከው ከተጻፈው መጽሃፍ፣ ከተቀባው ቅብ (ስዕል ፣ ከተነገረው ድምጽ (ቃል) ጀርባ ያለው ይዘት፣ መለኮታዊ ዲቫይን ሰብስታንስ ምንድን ነው? ማነው? ምን ይመስላል? ወዘተ ማንም አያውቀውም ። በቃ! የሰው ልጅ በጁ ነክቶ (ቁሰ ነገር) ባይኑ አይቶ (ምስል/ኢሜጅ)፣ በጆሮ ሰምቶ (ድምጽ)፣ በእጁ ዳሳሶ (ገላ) እና ባፍንጫው አሽትቶ (ሽታ) የሚያውቃቸው ነገሮች ሁሉ ድሮ በዘመነ ፓጋኒዝም ተመልከዋል ። ቁሳቁስ ያመለኩ፣ ድምጽ ያመለኩ፣ የሰማይ ቀለም (ቀስተ ደመና) ያመለኩ አሉ ፣

የማይታየውና የማይዳሰሰው እግዚአብሄርን የሚያመልኩት ህዝቦች ዛሬ የእግዚአብሄርን እውነትነት የሚያውቁት እንዴት ነው? ይህን መመለስ አለብህ! በቃ። ይህን የሚያውቁት ወይም ነው ብለው የሚቀበሉት (ኮንቪንስድ) የሚሆኑት በምልክት አማካይነት ነው ። ሃሳብ ነው ካልክ ደሞ ሃሳብ ማለት ባይምሮ ውስጥ ያለ ምስል ማለት ነው ። አንድ በሚሆን ታምር ማለት በሚታይ አክሽን ነው ካልክ ደሞ ያ አክሽን፣ ታ ታምር እንደ ምልክት፣ እንደ አመልካች ሆኖ የሚያገግለው ። የዝናብ መዝነብ የእግዚአብሄር መኖርን የሚያሳይ ነው ካልክ ያ ዝናብ ምክልት እንጂ እራሱ እግዚአብሄር ኣይደለም ።

ስለዚህ ከዛሬ ጀምረህ የኦርቶዶክስ ካህናትን የእውቀት ጥልቀት ማድነቅና ማክበር አለብህ ። ይህ እዚህ ምነግርህ ዛሬ ግዙፍ ያሜሪካ ዩኒቨርሲቲዋች የሚያስተምሩት ኮግኒቲቭ ሳይንስን ነው ! ኮንቪክሽን ምን እንደ ሆነ ማወቅ አለብህ! ክኖቪክሽን በሃሳብ ማመን አሜን ፣ አው፣ ነው ፣ ማለት ነው ። ማለትም አንድን ነገር ለማሰብ የምንችለው ባይምሮ ውስጥ ስለምናየው፣ ሜንታል ኢሜጅ ስለሆነው ነው ። ባይምሮ ወይም በአይን የማናየውን ነገር ማሰብ በፍጹም አንችልም!!! በቃ!

ባይምሮ የምናየው ነገር በእውን ባለም ላይ አለ ማለት አይደለም ! የሰው አይምሮ የሌለ ነገር እንደ ሜንታል ኢሜጅ ባይምሮው ማየት ይችላል ። ስለዚህ አንድ ሰው ያመነበት ነገር ሁሉ በእውን ህያው ነው ማለት አይደለም፣ ለምሳሌ ኢሉዥን! ግን ልብ በል ኢሉዥን ፣ ማንኛውም ሜንታል ኢሜጅ ምስል ነው! ስዕል! ፎቶ ነው! ቃል ነው! ጣኦት ነው! ታቦት ነው! ይህ ዛሬ የሰው ልጅ ሁሉ ሪያሊቲ ምን እንደ ሆነ የሚለካበት ኮግኒቲቭ ሳይስን ነው!

የሰው ልጅ ካንጎሉ ውጭ ያለውን አለም ለምሳሌ ዛፍና ተራራ የሚያውቀው ዛፉና ተራራው አንጎሉ ውስጥ በማስገባት አይደለም! የዛፉና የተራራው ምስል ጣኦት ታቦት (ወይም ቅርጽ) አይምሮው ውስጥ በማስገባት ነው ! ስለዚህ ኦርቶዶክን በጣኦት ወይም ምስል አምላኪነት የሚተቹ ጴንጤዎች ያልተማሩ ያልተመራመሩ መሃይም ሙጃዎች ናቸው ። የሚያነቡት ቃል ምን እንደ ሆነና ያ ቃል ያ ምልክት ምንን እንደ ሚያመለክት የማያውቁ ደንቆሮዎች ናቸው እነአቢይን የሚመሩት መሃይሞች!

Axumezana
Senior Member
Posts: 13485
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: The Ethiopian Orthodox Church has played key role in the continuity of Ethiopia but it requires reformation!

Post by Axumezana » 26 Jan 2023, 03:32

የኢትዮጵያ፥ ኦርቶዶክስም፥ ሆነ፥ አገልጋዮቿ፥ የእምነት፥ አባቶች፥ በክብር፥ መያዝ፥አለባቸው፥ የሚለውን፥ እስማማለሁ፥ ነገር፥ ግን፥ ከጊዜ፥ ብዛት፥በውስጧ፥የገቡ፥ እድፎችን፥ መጦቆሙ፥ ጴንጤ፥ የሚል፥ ቅጽል፥ ስም፥ ሰጥቶ፥ በጭፍን፥ መቃወሙ፥ ተገቢ፥ አይሆንም።
ከላይ፥ ለሰጠኸው፥ አስተያዬት፥ መልስ፥ ተጨማሪ፥ ትነተና፥ መስጠት፥ሳይሆን፥ የክርስትና፥ እምነት፥ ውስን፥ ዳር፥ ድንበር፥ያለውና፥ ጠባብ፥ መንገድ፥ መሆኑን፥ በሚከተለው፥ መልኩ፥የገለጽኩበት፥ በቂ፥ ነው።

በክርስትና፥ እምነት፥ አንድ ሀሳብ፥ ወይም፥ ቃል፥ ከእግዚአብህሔር፥ ወይም፥ ከሰይጣን፥ ወይም፥ ከሰው፥ ሊመነጭ፤ ይችላል፥ የእግዚአብህሔር፥ መሆኑና፥ አለመሆኑን፥ ክርስትያን፥ የሚለየው፥ ከላይ፥ እንደገለፅኩት፥ በመጽሀፍ፥ ቅዱስ፥ ከተፃፈው፥ ጋር፥ በማነፃፀርና፥ በተረዳው፥ መጠን፥ ነው። ክርስትና፥ የሚያስተምረው፥ የእግዚአብሔር፥ መንገድ፥ አንድና፥ ጠባብ፥ መሆኑን፥ ነው፥ ከሌሎች፥ እምነቶች፥ በዚህ፥ ይለያል።

Axumezana
Senior Member
Posts: 13485
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: The Ethiopian Orthodox Church has played key role in the continuity of Ethiopia but it requires reformation!

Post by Axumezana » 26 Jan 2023, 03:32

የኢትዮጵያ፥ ኦርቶዶክስም፥ ሆነ፥ አገልጋዮቿ፥ የእምነት፥ አባቶች፥ በክብር፥ መያዝ፥አለባቸው፥ የሚለውን፥ እስማማለሁ፥ ነገር፥ ግን፥ ከጊዜ፥ ብዛት፥በውስጧ፥የገቡ፥ እድፎችን፥ መጦቆሙ፥ ጴንጤ፥ የሚል፥ ቅጽል፥ ስም፥ ሰጥቶ፥ በጭፍን፥ መቃወሙ፥ ተገቢ፥ አይሆንም።
ከላይ፥ ለሰጠኸው፥ አስተያዬት፥ መልስ፥ ተጨማሪ፥ ትነተና፥ መስጠት፥ሳይሆን፥ የክርስትና፥ እምነት፥ ውስን፥ ዳር፥ ድንበር፥ያለውና፥ ጠባብ፥ መንገድ፥ መሆኑን፥ በሚከተለው፥ መልኩ፥የገለጽኩበት፥ በቂ፥ ነው።

በክርስትና፥ እምነት፥ አንድ ሀሳብ፥ ወይም፥ ቃል፥ ከእግዚአብሔር፥ ወይም፥ ከሰይጣን፥ ወይም፥ ከሰው፥ ሊመነጭ፤ ይችላል፥ የእግዚአብህሔር፥ መሆኑና፥ አለመሆኑን፥ ክርስትያን፥ የሚለየው፥ ከላይ፥ እንደገለፅኩት፥ በመጽሀፍ፥ ቅዱስ፥ ከተፃፈው፥ ጋር፥ በማነፃፀርና፥ በተረዳው፥ መጠን፥ ነው። ክርስትና፥ የሚያስተምረው፥ የእግዚአብሔር፥ መንገድ፥ አንድና፥ ጠባብ፥ መሆኑን፥ ነው፥ ከሌሎች፥ እምነቶች፥ በዚህ፥ ይለያል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30837
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The Ethiopian Orthodox Church has played key role in the continuity of Ethiopia but it requires reformation!

Post by Horus » 26 Jan 2023, 04:17

አቶ አክሱም ፣
የትም ቦታ እኔ ስለ ኦርቶዶክስ ካህናት (ዲያቆን፣ ቄስ፣ ጳጳስና ፓትሪያርክ) አልተናገርኩም ። እነዚህ ሰዎች ናቸው ! ካቶሊኮች ህጻናትን በመድፈር የታወቁ ባሌጌዎች ናቸው ። እኔ ስለ ኦርቶዶክስ ዶክትሪን ባነሳሃው ትችት ላይ ነው የምወቅስህ ! ኦርቶዶክስ ምስል ያመልካል፣ ጣኦት ያመልካል የሚሉ ያልተማሩ ደደቦች ናቸው! ሃሳብ ምንድን ነው? ማወቅ ምንድን ነው? ማመን (ኮንቪክሽን) ምንድን ነው? ብትላችደው መመለስ የማይችሉ ጥሬዎች ናቸው የ2000 አመት ምርምር ውጤት የሆነውን ሃይማኖት ሊተቹ የሚዳዱ!!!

ይቺ ቤተ ክርስቲያኮ የቅባትና ወልድ (ማለትም የምስልና አካል) ከፍተኛ ክርክር አድርጋ የፈታች ተቋም ናት ። ስለዚህ በውል የማታውቀው መንገድ አትጓዝ! ካህናት አይረቡም፣ ባለጌዎች ናቸው ! ወያኔ ገብቶ የደንቆሮ ካድሬ መጨፈሪያ አደረገው ያ ሌላ ጥያቄ ነው ! ትክክል ነው ። ይህ ደሞ የማንኛውም አሮጌ እምነት እንደ ካቶሊክ ያለበት ችግር ነው!!

ግን አትርሳ ኢትዮጵያ የምትባል ገናና አገርን የፈጠረ ኦርቶዶክስ ነው! ዛሬ የማንም ሙጃ ኢትዮጵያዊ ነኝ ግን ኦርቶድክስን እጠላለሁ የሚል አባቱን የማያውቅ ወፍ አራሽ ሙጃ ነው !

Axumezana
Senior Member
Posts: 13485
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: The Ethiopian Orthodox Church has played key role in the continuity of Ethiopia but it requires reformation!

Post by Axumezana » 26 Jan 2023, 08:59

የኢትዮጵያ፥ ኦርቶዶክስ፥ ቤተክርስትያን፥ ዶክትሪን፥ ወሰን፥ የተበጀለት፥ ፍትሃ፥ ነገስት፥ በሚባለው፥ መፅሃፍ፥ ሲሆን፥ ከአዋልድ፥ መፃህፍት፥ ጋር፥ የተያያዙት፥ እምነቶችና፥ ትርክቶች፥ ፍትሃ፥ ነገስት፥ ከገደበው፥ውጭ፥ ናቸው።

Post Reply