Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11032
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

Post by Abere » 24 Jan 2023, 17:12

ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

ለዚህ የማቀርበው ምክንያት የአንድን ሀገር እምልኮዊ እና መንፈሳዊ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ በማወካቸው ብቻ ሳይሆን ነባራዊ እና ህጋዊ የእምነት ቀኖና ስርዐቱን በሽፍትነት ለመጣል በመሞከራቸው ነው። እንደ እኔ የመንፈስ ቅዱስን ስራ እጅግ ተዳፍረዋል ይህን እንደ Blasphemy እቆጥረዋለሁ። ከዚህ በፊት ፈይሳ አዱኛ የሚባል ቄስ ተመሳሳይ ክህደት በቤተ እምነቱ ላይ ሲያሳይ ምንም እርምጃ አለተወሰደበትም - ይበልጡን ተሾመ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

Post by Horus » 24 Jan 2023, 18:16

አበረ፣
የሲኖዶሱ ችግር የጀመረው ከመንግስቱ ጀምሮ ነው ። የቤተ ክርስቲያኗ ነጻነት መደፈር ከጀመረ ቆየ። ዛሬ የምናየው የብሄር ጥያቄ በሲኖዶስ ውስጥ ትግሬዎች የጀመሩት ነው ። እኔ ደጋግሜ እንዳልኩት ሰዎቹ የሚፈልጉት ስልጣንና ገንዘብ ነው! በቃ ! ክብር ሊያገኙ አይችሉም ከወዲሁ እየተዋረዱ ስለሆነ ። አሁን በእኔ ግምት ያለው ትክክለኛ መፍትሄ (1) ምልዐተ ሲኖድ ተሰብስቦ እነዚህ ዝሙተኞችን ማውገዝ በእምነት ደረጃ፤ ከስራ ማባረር፣ ቤታቸውን መቀማት፤ (2) የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና አሰራር ስርዓት ስለጣሱ ማውገዝና ማንኛውም ምዕመን እንዲያስወግዳቸው ማዘዝ፣ (3) ኦርቶዶክስ ህጋዊ ሰውነት ያልት ማህበር ስለሆነች የመፈንቅሉ መሪዎችን ፍርድ ቤት መውሰድ፤ በየትኛውም ድብር ዝር እንዳይሉ ማስደረግ፤ (4) ተገቢነት ያላቸውን የቋንቋና አገልግሎት ጥያቄዎችን ለመመልስ፣ ለምፍታት መምሪያ መስጠት ነው ። ማለትም ኦርቶዶክስ በጴንጤ እየተቀደመ ያለው ግዕዝና አማራኛ የማይሰሙትን ሕዝቦች በሚገባቸው ቋንቋ ለማስተማር አለ መቻሉ ነው ። ይህ ከድሮም ጀምሮ ያለ ችግር ነው ። ለዚህ ደሞ መፍትሄው ሁሉም የሚትዮጵያ ጎሳዎች የክህነት ገዳማት እንዲያቆሙ መርዳት ነው ። በኮንሶ፣ በጋምቤላ ሚሲዮን የሚገባውኮ የኦርቶዶክስ ገዳም ቆሞ የጋምቤላ ዲያቆን ቄስና ጳጳስ አለመሰልጠኑ ነው። ያንን ነው ማድረግ ያለብን ። እኔ ጉጂ ወይ ቡርጂ ውስጥ ያለች ማሪያም ቤተ ክርስቲያን በጉጂኛ ቅዳሴ ቢደረግባት ይህ ኦርቶዶክስን ያሳድጋል እንጂ አይጎዳትም ። ይህ ሁሉ ችግር የመጣው ግን ቤተ ክርስቲያኑ የጎሳ ፖለቲካ መናሀሪያ ስለሆነ ነው። ያ ማለት ደሞ ነጂ ምክ ኛቱ የስልጣንና ገንዘብ ክፍፍል እንጂ መንፈሳዊ ስራ ወይም የዶግማ ልዩነት አይደለም ! ለምሳሌ አሁን ላይ ይህ ነው የሚባል የዶግማ ወይም የዶክትሪን ልዩነት የለም፣ ያለው የቀኖና እና የስልጣን፣ የሹመት ልዩነት ነው ። በዚያም ሳቢያ ቁጥር ለመሙላት ሲባል ምድረ ሴክስ ኦፌንደር ሁላ አቡን እየተባለ ነው ። ይህ አጠቃላይ የሲኖዱ ችግር ነው ። በዚህ ድክመት ቀዳዳ ውስጥ ነው ጸረማሪያሙ አቢይ ጊመል እየነዳበት ያለው ። ይህቺን እመነታችንን የሚጠብቅ እራሱ ሕዝባችን ነው! ሕዝብ ደሞ ሁሌ አሸናፊ ነው! ያ ነው የሚሆነው!!!

sun
Member+
Posts: 9322
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

Post by sun » 24 Jan 2023, 20:07

Abere wrote:
24 Jan 2023, 17:12
ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

ለዚህ የማቀርበው ምክንያት የአንድን ሀገር እምልኮዊ እና መንፈሳዊ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ በማወካቸው ብቻ ሳይሆን ነባራዊ እና ህጋዊ የእምነት ቀኖና ስርዐቱን በሽፍትነት ለመጣል በመሞከራቸው ነው። እንደ እኔ የመንፈስ ቅዱስን ስራ እጅግ ተዳፍረዋል ይህን እንደ Blasphemy እቆጥረዋለሁ። ከዚህ በፊት ፈይሳ አዱኛ የሚባል ቄስ ተመሳሳይ ክህደት በቤተ እምነቱ ላይ ሲያሳይ ምንም እርምጃ አለተወሰደበትም - ይበልጡን ተሾመ።
:P :P
Last edited by sun on 24 Jan 2023, 20:50, edited 1 time in total.

sun
Member+
Posts: 9322
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

Post by sun » 24 Jan 2023, 20:31

Abere wrote:
24 Jan 2023, 17:12
ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

ለዚህ የማቀርበው ምክንያት የአንድን ሀገር እምልኮዊ እና መንፈሳዊ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ በማወካቸው ብቻ ሳይሆን ነባራዊ እና ህጋዊ የእምነት ቀኖና ስርዐቱን በሽፍትነት ለመጣል በመሞከራቸው ነው። እንደ እኔ የመንፈስ ቅዱስን ስራ እጅግ ተዳፍረዋል ይህን እንደ Blasphemy እቆጥረዋለሁ። ከዚህ በፊት ፈይሳ አዱኛ የሚባል ቄስ ተመሳሳይ ክህደት በቤተ እምነቱ ላይ ሲያሳይ ምንም እርምጃ አለተወሰደበትም - ይበልጡን ተሾመ።
According to which law? State law or "church law"? If it is a matter of state law which enjoys authority over all Ethiopians regardless of religion, region, ethnicity, gender, educational standard, etc, then the church needs to go to the court of the land and get the issues legally decided and cleared instead of getting very emotional and trying to turn in to the medieval byzantine style advocacy of barbarianism by declaring the democratizing reformists as vagabonds to be eliminated and their churches burned to the ground.

Galileo Galilei (1564-1642) is considered the father of modern science and made major contributions to the fields of physics, astronomy, cosmology, mathematics and philosophy.
Galileo's work continues to fascinate and provoke even after 400 years. The great founder of modern science was tried, convicted and sentenced in 1633 to perpetual house arrest by the Church for defending the idea that the Earth goes around the sun, and was forced to recant under oath.

Abere
Senior Member
Posts: 11032
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

Post by Abere » 24 Jan 2023, 21:44

ሆረስ፥

አመሰግናለሁ ለሰጠኸኝ ማብራርያ! እኔ ግን የሚገርመኝ በአለም ውስጥ ለመሆኑ መፈንቅለ -ሲኖዶስ ተደርጎ ያውቃል? መፈንቅለ መንግስት እንጅ በቅዱስ ሲኖዶስ መፈንቅል የተደረገባት አገር ሰምቸ አላውቅም። መቸም ይችው የፈረደባት ጉደኛ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። የጎሳ ክልል ፈጥራ የሚልዮኖችን ህይወት ፉት ጭልጥ ያደረገች እርሷ፥ መፈቅለ-ሲኖድ ብታደርግም እርሷ ብቻ ናት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ህልውና እና አስተምህሮ የሚረጋገጠው የኦሮሙማ ሽፍታ መንግስት ነኝ ባይ ሙሉ በሙሉ ሲወገድ ብቻ ነው። ኦሮሙማ ብልጽግና እስካለ ድረስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንድሁ እንደታወከች ትኖራለች። ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥርስ አልባ ተደርጓል - ዛሬ የቤተክህነት ጠባቂ ሰራዊት ሲወገድ እኮ ሲኖዶሱን እያስፈራሩት ነው በተዘዋዋሪ። የኦሮሙማው መንግስት ነው ቤተክስቲያን የሚያሻበረው።

Horus wrote:
24 Jan 2023, 18:16
አበረ፣
የሲኖዶሱ ችግር የጀመረው ከመንግስቱ ጀምሮ ነው ። የቤተ ክርስቲያኗ ነጻነት መደፈር ከጀመረ ቆየ። ዛሬ የምናየው የብሄር ጥያቄ በሲኖዶስ ውስጥ ትግሬዎች የጀመሩት ነው ። እኔ ደጋግሜ እንዳልኩት ሰዎቹ የሚፈልጉት ስልጣንና ገንዘብ ነው! በቃ ! ክብር ሊያገኙ አይችሉም ከወዲሁ እየተዋረዱ ስለሆነ ። አሁን በእኔ ግምት ያለው ትክክለኛ መፍትሄ (1) ምልዐተ ሲኖድ ተሰብስቦ እነዚህ ዝሙተኞችን ማውገዝ በእምነት ደረጃ፤ ከስራ ማባረር፣ ቤታቸውን መቀማት፤ (2) የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና አሰራር ስርዓት ስለጣሱ ማውገዝና ማንኛውም ምዕመን እንዲያስወግዳቸው ማዘዝ፣ (3) ኦርቶዶክስ ህጋዊ ሰውነት ያልት ማህበር ስለሆነች የመፈንቅሉ መሪዎችን ፍርድ ቤት መውሰድ፤ በየትኛውም ድብር ዝር እንዳይሉ ማስደረግ፤ (4) ተገቢነት ያላቸውን የቋንቋና አገልግሎት ጥያቄዎችን ለመመልስ፣ ለምፍታት መምሪያ መስጠት ነው ። ማለትም ኦርቶዶክስ በጴንጤ እየተቀደመ ያለው ግዕዝና አማራኛ የማይሰሙትን ሕዝቦች በሚገባቸው ቋንቋ ለማስተማር አለ መቻሉ ነው ። ይህ ከድሮም ጀምሮ ያለ ችግር ነው ። ለዚህ ደሞ መፍትሄው ሁሉም የሚትዮጵያ ጎሳዎች የክህነት ገዳማት እንዲያቆሙ መርዳት ነው ። በኮንሶ፣ በጋምቤላ ሚሲዮን የሚገባውኮ የኦርቶዶክስ ገዳም ቆሞ የጋምቤላ ዲያቆን ቄስና ጳጳስ አለመሰልጠኑ ነው። ያንን ነው ማድረግ ያለብን ። እኔ ጉጂ ወይ ቡርጂ ውስጥ ያለች ማሪያም ቤተ ክርስቲያን በጉጂኛ ቅዳሴ ቢደረግባት ይህ ኦርቶዶክስን ያሳድጋል እንጂ አይጎዳትም ። ይህ ሁሉ ችግር የመጣው ግን ቤተ ክርስቲያኑ የጎሳ ፖለቲካ መናሀሪያ ስለሆነ ነው። ያ ማለት ደሞ ነጂ ምክ ኛቱ የስልጣንና ገንዘብ ክፍፍል እንጂ መንፈሳዊ ስራ ወይም የዶግማ ልዩነት አይደለም ! ለምሳሌ አሁን ላይ ይህ ነው የሚባል የዶግማ ወይም የዶክትሪን ልዩነት የለም፣ ያለው የቀኖና እና የስልጣን፣ የሹመት ልዩነት ነው ። በዚያም ሳቢያ ቁጥር ለመሙላት ሲባል ምድረ ሴክስ ኦፌንደር ሁላ አቡን እየተባለ ነው ። ይህ አጠቃላይ የሲኖዱ ችግር ነው ። በዚህ ድክመት ቀዳዳ ውስጥ ነው ጸረማሪያሙ አቢይ ጊመል እየነዳበት ያለው ። ይህቺን እመነታችንን የሚጠብቅ እራሱ ሕዝባችን ነው! ሕዝብ ደሞ ሁሌ አሸናፊ ነው! ያ ነው የሚሆነው!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሆረስ በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳኝ: - < ህግ ቢኖር እነኝህ መፈንቀለ ሲኖዶስ አደረግን ያሉ እስር ቤት ወዲያውኑ መግባት ነበረባቸውባ ይ ነኝ >

Post by Horus » 24 Jan 2023, 23:00

sun የምትባል አላዋቂ ጋሊሌ ከካቶሊክ ኦርደር ጋር የነበረው ጠብ የጎሳ ወይም የቀኖና ልዩነት አልነበረም፣ ጋሊሌ የዶግማ፣ የዶክትሪን ተቃውሞ ነው የነበረው ። እነዚህ ፉሩሽካ ኦነጋዊ አላዋቂዎች ያላቸው ጠብ ዶክትሪን አይደለም። ለዛም የበቁ አይደሉም ። እነሱ ስልጣናን ገንዘብ ፈላጊዎች ናቸው። አንዱ ጥያቄያቸው የቁልቢ ስለት ለምን አልበላንም የሚል ነው ። ያው የገማው የጌኛ አባዜ ነው ። ስለጋሊሌ ባትቀባጥር ድንቁርናህን ከማጋለጥ ትድናለህ!

አበረ፣
እጅግ በረጅሙና ገናናው ታሪካዊው የኢትዮጵያ ክርስትና ታሪክ ከዚህ የባሱ ክፍሎች ነበሩ! የቅባትና ወልድ ልጆች የሚባለው የዶክትሪን ልዩነት ወዘተ ። ግ ን እንደዚህ እርካሽ መንደረኛ እንደ ማለልት ሕቡዕ አደረጃጀት ድሮ አልነበረም ። ተሟጋቾቹ ክቡርና ሊቃውንት ስለነበሩ ሲለያዩ በነገረ መለኮት ላይ ነበር ባብዛኛው ማለትም ትክክለኛው የፈጣሪ ባህሪያት ምንድን ናቸው? ትክክለኛ የእግዚአብሄር ቃል የቱ ነው? አብ ምንድን ነው? ወልድ ምንድን ነው? መንፈስ ቅዱስ ምንድን ነው? ቅብዓት ወዘተ የሚሉና የእምነቱ ሰብስታንስ ላይ ነበር ። የቀኖና ልዩነትም ከሆነ ለምሳሌ በቅርብ ግዜ እንኳን የነበረው ዝማሬ በፒያኖ፣ በኦርጋን፣ በኮምፒዩተር ይደረግ አይደረግ በሚለው ፈጣሪ የሚመለከው በከበሮ፣ ጽናጽን እና በበገና ብቻ ነው የሚሉ እስከ ዛሬ አሉን! እነዚህ ተገቢ ክርክሮችና ልዩነቶች ናቸው ።

ኦርቶዶክስ ላዕለ ኩሉ ማለት ዩኒቨርሳል ነው ብሎ የተማረ ኦነጋዊ ደደብኮ ነው የጎሳ ኦርቶዶክስ ያለ ይመስል መፈንቅለ ተዋህዶ (አንድነት) የሚሞክረው ። ተዋህዶ ካልፈለገ መሆን ያለበት ጴንጤ ነው በቃ ! ስለዚህ ይህ የጴንጤ መፈንቅለ ሃይምኖት ነውና እኛ አማኝ ሕዝቦቹ እናከሽፈዋለን።

ነገር ግን አንድ ነገር አትርሳ! ከኦሮሞ ሕዝብ ቁጥር እስላምና ፓጋኑን ወይም ዋቄ ፌታውን ቀንሰህ ስንት ኦርቶዶክስ ኦሮሞ እንዳለ ባላውቅም ባስርት ሚሊዮኖች የሚቆጠር ነው ኦርቶዶክስ ኦሮሞ የሌለበት የኦሮሞ ምድር የለም ። ታዲያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተስኪያን የነዚህ አማኞች እረኛ ነች፣ አላፊነት አለባት ። የኦነግ ወጠቴ ያን አለ ይህን አደረገ አይደለም ። ኦርቶዶክስ የኦሮሞ ሕዝብን ለጴንጢው ለሙስሊምና አዳዲስ ከልትና ጥንቆላ ለሚያስፋፉ እንደ አሸን የፈሉ የዉሸት ነቢያት አጋልጠው ሊተዉዋቸው በፍጹም አይገባል ። ኦርቶዶክስ ከላይ ያልኩትን አይነት የቋንቋና ባህል ችግሮችን ተራበተራ በፈታት የኦሮሞ ሕዝብ ኦርቶዶክስ የማምለክ ምርጫው እንድታስከብር ቤተክርስቲያኗ የግድ ይላታል ።

መፈንቅሉ እንደ ሆነ በቅርቡ መፍትሄ ያገኛል ። ቁም ነገር እነዚህ የእምነት ጁንታዎች የቤተስኪያን ሃብትና ቅርስ እንዳይዘርፉ መጠበቁ ላይ ነው ። ኦርቶዶክስ ላዕለ ኩሉ! ኢትዮጵያ ዘላለማዊ! አሜን!!!

Post Reply