Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4207
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ዛሬ ፓርላማ ስብሰባ በመኖሩ መንገዶች ተዘጋግተው ትራንስፖርት ችግር ነበር። 54 ሺ ብር ደሞዝ የምትከፍል አገር!!

Post by Abaymado » 24 Jan 2023, 12:49

ዛሬ ስብሰባ በመኖሩ ባለስልጣን ነን በሚሉ ባለመኪኖች መንገዱ ተጨናንቆ ነበር። እነዚህ ምንም እርባና የሌላቸው ባለስልጣናት ምናለ ባያውኩን? ያ ሁሉ መኪናስ ከየት መጣ?

ባልስልጣን የሚባል ሁሉ የመንግስት መኪናን መጠቀም አቁሞ በእግሩ መሄድ ወይም የህዝብ ትራንስፖርት መጠቀም አለበት።

ሌላው ገራሚ ነገር፣ አገሪቱ ለባለስልጣናት የምትከፍለው ለማመን የሚከብድ ደሞዝ ነው።

ከወጣው መረጃ ፕሬዝዳንቷ ወደ 54 ሺ ብር ሲያገኙ አብይ ደሞ 25 ሺ ብር ነውና የሌሎችን ደሞዝ ከዚህ የተለየ አይደለም። ግን ምን ስላደረጉ ነው ይህ ወጪ?

ህዝቡ የሚያገኘው ደሞዝ የሚሰቀጥጥ ነው። እኔ ያየሁት ደሞዝ አብዛኛው ከ 2000 ብር እስከ 4000 ብር ያለ ነው ምናልባት የደሞዛቸውን ሊስት ወደ ፊት አወጣዋለሁ።

ሁለት አማራጭ አለ፣ የህዝቡን ደሞዝ ከፍ ማረግ ወይም የባለሳጣናቱን ደሞዝ ከህዝቡ ደሞዝ ጋር ማስተካከል።