Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Horus ከዚህ እጅግ ከሚያኮራ ህስብ ውስጥ መወለድህ እንዴት ታላቅ ኩራት ነው!!

Post by Wedi » 23 Jan 2023, 10:04

ከጉራጌ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በአሁኑ ወቅት ኤጲስ ቆጶሳትን ሾምን፤ በሚያገለግሉበትም ቦታ መደብን የሚሉ ሕገ ወጥ አካላት የሕግና የሥርዓት ምንጭ የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክብር የሚያቃልል፤ አንድነቷን የሚከፋፍል፤ ቀኖናዋንና ትውፊቷን የሚሸረሽር ተግባር ፈጽመዋል፡፡ የጉራጌ ሶዶ ሀ/ስብከት ጳጳስና የምሁር ኢየሱስ ገዳም የበላይ ጠባቂ ጳጳስ ተደርገው ሁለት ሰዎች ለጉራጌ ሀ/ስብከት መመደባቸውንም በአግራሞት ተመልክተናል፡፡

በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን የማታውቃቸው ሕገ ወጥ ሿሚና ተሿሚዎች እኛን የሰበሰበችንን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመበተን የሚያደርጉትን የቀኖና ጥሰት ለማውገዝ የጉራጌ ሀ/ስብከት አስተዳደር ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ አድርገናል፡፡

በመሆኑም፡-

፩) የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆናችሁ አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማጽናት በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት የምትወስኑትን የአንድነት ውሳኔ በአንቃዕድዎ ሆነን እየጠበቅን መሆናችንን በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን፤

፪) የጉራጌ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት፣ የሀ/ስብከቱ ወረዳ አብያተ ክህነት ጽ/ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀ/ስብከቱ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኗ ካህናትና ምዕመናን በሙሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ከወትሮው በተለየ ንቃትና ታማኝነት በመጠበቅ፤ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግና መረጃዎችን በመለዋወጥ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ አጥብቀን እናሳስባችኋለን፤

፫) በጉራጌ ዞን በየደረጃው ያላችሁ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅና በማስጠበቅ ሀገራዊ አደራችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የጉራጌ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት
ወልቂጤ-ኢትዮጵያ
ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም.

Please wait, video is loading...

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Horus ከዚህ እጅግ ከሚያኮራ ህስብ ውስጥ መወለድህ እንዴት ታላቅ ኩራት ነው!!

Post by Horus » 23 Jan 2023, 15:52

wedi,
አመሰግናለሁ! ወላጆቻችን ዋሻ እየቆፈሩ፣ ዛፍ ላይ ታቦት ደብቀው እያደሩ ነው ይህቺን እምነታችንን ከግራኝ ወረራ ተዋግተው እዚህ ያደረሷት! ዛሬ እንዲ ተዳክማ ያለችው ዝዋይ ሃይቅ ነች ታቦትና ንዋየ ቅዷሳን ደብቃ ለዚህ ያበቃችን! ዛሬ በእኛ ትውልድ ኦርቶዶክስ አትደፈርም እመነኝ።

በዚህ መግለጫ እኔም ኮርቻለሁ! ትላንት ያልኩትን ነው የሆነው! በጉራጌ አንዲት ኦርቶዶክስ አለች! አንድ ባንዲራ አለ! አንዲት አገር አለች፣ እሷም ኢትዮጵያ ትባላለች ነበር ያልኩት!

ኦርቶዶክስ ላዕለ ኩሉ! ኢትዮጵያ ዘላለማዊ !

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Horus ከዚህ እጅግ ከሚያኮራ ህስብ ውስጥ መወለድህ እንዴት ታላቅ ኩራት ነው!!

Post by Horus » 23 Jan 2023, 22:35

እነዚህ የመፈንቅለ ሲኖዶስ ፖለቲከኞች በቅዱስ መንፈስ ሳይሆን በእርኩስ መንፈስ የሚታዘዙ የጥፋትና እልቂት መልክተኞች እንደሆኑ ተመልከቱ ! በጎፋ አካባቢ ያለውን የክልልነት ጥያቄን ለመጠቀም ለጎፋ ባስኬቶ አዲስ የፖለቲካ ጳጳስ ሾመዋል !!! በጉራጌ ውስጥ ያለው የክልልነት ጥያቄና የሃሳብ ልዩነቶችን ለመጠቀም ታላቁ ክርስቲያን የክስታኔ ሕዝብን ደፍረው አዲስ ጳጳስ ሾመዋል ። በመሰረቱ የአቢይ ሺመልስ ኦሮሙማ ስልቃጭ ቡድን ጉራጌን ውጠው ዘሩን ለማጥፋት የሚያደርጉት አጉል መጋጋጥ ነው ይህ ሁሉ የቄስ ተብዬ ካድሬዎች መታከት ። ሌላው ሁለቱ እጅግ ገናና ገዳማት፣ የምሁር አክሊል ምሁር ኢየሱስና ታሪካዊው የምድረ ከብድን ገዳም ለመቆጣጠር የታቀደ ደባ ነው ።

ጉራጌ ጣሊያንን እንደ ተዋጋው እነዚህ ወራሪዎችንም ይዋጋቸዋል!

Post Reply