ኢፈርት ድርጅቱን ከኮሜርሻል ኖሚኒስ ተረከበ
በሰላማዊት መንገሻ
August 20, 2023
Ethiopian Reporter
ተለምዶ ኢፈርት (EFFORT) ተብሎ የሚጠራው በትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የንብረት ርክክብ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡
የርክክብ ሒደት ሲከናወን የኮሜርሻል ኖሚኒስ አስረካቢ፣ የኢፈርት ድርጅቶች ተረካቢና ጠቅላይ ዓቃቢ ሕግ አረካካቢ በመሆን ባሳለፍነው ሳምንት የርክክብ ሒደት ማከናወኑን የኢፈርት ድርጅቶች የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ልማት መምርያ ኃላፊ አቶ ጎይቶም ያብረሃ ገልጸዋል፡፡
ርክክቡ የተካሄደው በ13 ድርጅቶች ብቻ መሆኑን የገለጹት አቶ ጎይቶም አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ያልተከፈለ የኪራይ ቤት ዕዳ ስላለበት ርክክብ ውስጥ መካተት አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ኮሜርሻል ኖሚኒስ የማስተዳደሩን ኃላፊነት ሲወስድ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱም ኮሜርሻል ኖሚኒስ የማስተዳደር ሥራ እየሠራ በወር አንድ ሚሊዮን ብር እንዲከፈለው የሚል ብይን ሰጥቶ ነበር፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ከተለያዩ የኢፈርት ኩባንያዎች አካውንት 20.87 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አቶ ጎይቶም ተናግረዋል፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ የተገለጸውን ያህል ገንዘብ መጠቀሙ ምንም ዓይነት መረጃ የለኝም ሲል በሪፖርቱ ተናግረዋል፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የ16 ወር ሪፖርት ማቅረቡን የተናገሩት አቶ ጎይቶም፣ ፍርድ ቤቱ ሪፖርቱን ከተመለከተ በኋላ ኮሜርሻል ኖሚኒስ የተፈቀደውን ክፍያ በምን አግባብ ይወስዱት እንደነበር፣ ኩባንያዎቹ ምን ዓይነት ሥራ ላይ እንደነበሩ፣ በምን መልኩ ሲያስተዳድ እንደነበር፣ ያልተሰበሰቡ ገቢዎች በምን ምክንያት እንዳልተሰበሰቡና ገቢ ማግኘት የሚገባቸው ገቢ ያለማግኘታው ምክንያት ምን እንደሆነ የሚገልጽ ጥያቄ መነሳቱን ገልጸዋል፡፡
‹‹በኢፈርት ድርጅቶች በኩል ያለውን የባንክ ስቴትመንት ለኮሜርሻል ኖሚኒስ የተላለፈ ስለሆነ፣ በባንክ የሚገኙትን ብር በራሳቸው ፊርማ በመጠቀም ወስደዋል›› ሲሉ አቶ ጎይቶም ተናግረዋል፡፡
‹‹ለኮሜርሻል ኖሚኒስ እንዲያስተዳድር በሚሰጥበት ወቅት ከኢፈርት ድርጅቶች መረከብ የነበረበት ቢሆንም ርክክብ አልተደረገም፡፡ የተረከብነውን ንብረት በሒደት ኦዲት ይደረጋል፡፡ ከርክክቡ በኋላ ኩባንያዎቹ ኮሚቴ አቋቁመው የየራሳቸውን የኦዲት ሥራ መሥራት ጀምረዋል፤›› ሲሉ አቶ ጎይቶም ተናግረዋል፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ የተሰኘው ኩባንያ በኢፈርት ሥር የሚገኙ 18 ድርጅቶችን እንዲያስተዳድር ከየካቲት 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስኖ የነበረ ሲሆን፣ ውሳኔው በፍርድ ቤት እንዲሻር እስከተደረገበት እስከ ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ይህንኑ የኃላፊነት ድርሻውን ሲወጣ መቆየቱን አቶ ጎይቶም ተናግረዋል።
የኢፈርት ድርጅት በኮንስትራክሽን፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ግብርና፣ ማዕድንና ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በሥሩ ሲያስተዳድ
Continue reading
https://www.ethiopianreporter.com/121549/