Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11057
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

< የሃይማኖት ጦርነት ሊነሳ ነው> የማይመስለው ሁሉ ሲሆን አይተናል እና አይግረመን። ዕድሜ ለኦሮሙማ

Post by Abere » 22 Jan 2023, 15:29

< የሃይማኖት ጦርነት ሊነሳ ነው> የማይመስለው ሁሉ ሲሆን አይተናል እና አይግረመን። ዕድሜ ለኦሮሙማ


ፓትርያርኩ አጋለጠዋል " ቤተክርስቲያናችን በቀኝ ግዛት ስር ናት፥ ይህን ዕልድ ሳያልፈኝ ለህዝብ ልናገር ግደታ አለብኝ"

Axumezana
Senior Member
Posts: 13485
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: < የሃይማኖት ጦርነት ሊነሳ ነው> የማይመስለው ሁሉ ሲሆን አይተናል እና አይግረመን። ዕድሜ ለኦሮሙማ

Post by Axumezana » 22 Jan 2023, 16:10

ጦርነት፥ አያስፈልግም፥ ክርስትና፥ በጦርነት፥ አልተስፋፋም፥ አልተጠበቀምም፤ ችግሮችን፥ ንስሀ፥ በመግባት፥ በመነጋገር፥ በፀሎት፥ መፍታት፥ ይቻላል። በሁሉም፥ አቅጣጫ፥ ያሉ፥ ፖለቲከኞች፥ ይኸነን፥ ችግር፥እንዳይጠቀሙበት፥ ማድረግ፥ አለብን፤

Axumezana
Senior Member
Posts: 13485
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: < የሃይማኖት ጦርነት ሊነሳ ነው> የማይመስለው ሁሉ ሲሆን አይተናል እና አይግረመን። ዕድሜ ለኦሮሙማ

Post by Axumezana » 22 Jan 2023, 16:10

ጦርነት፥ አያስፈልግም፥ ክርስትና፥ በጦርነት፥ አልተስፋፋም፥ አልተጠበቀምም፤ ችግሮችን፥ ንስሀ፥ በመግባት፥ በመነጋገር፥ በፀሎት፥ መፍታት፥ ይቻላል። በሁሉም፥ አቅጣጫ፥ ያሉ፥ ፖለቲከኞች፥ ይኸነን፥ ችግር፥እንዳይጠቀሙበት፥ ማድረግ፥ አለብን፤

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: < የሃይማኖት ጦርነት ሊነሳ ነው> የማይመስለው ሁሉ ሲሆን አይተናል እና አይግረመን። ዕድሜ ለኦሮሙማ

Post by sarcasm » 22 Jan 2023, 16:28

They say you cannot be more catholic than the pope. ፓትርያትሪኩ እንዳሉት ቤተ ክርስቲያን በቅኝ ግዛት የያዘው ኣካልማ ጽንፈኛው ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው። 6 ሚልዮን የትግራይ ኦርቶቶክሶች ለማጥፋት ከአቢይና ሻዕብያ alliance በመፍጠር የትግራይ ጄኖሳይድ የነፍስ አባት ሆነው መርተዋል።

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቅኝ ገዢዎች ተይዛለች!" ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ





ማኅበረ ቅዱሳን: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የቅኝ ገዢዎች በትግራይ ጄኖሳይድ ያላቸው ሚና


"የትግራይ ጄኖሳይድ ዋና መሪዎች ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው። የትግራይ ጠላቶች ናቸው። የቤተ ክህነት ጠላቶች ናቸው።" ብፁእ አቡነ መርሃ ክርስቶስ የትግራይ አህጉረ ስብከት ጉባኤ ጊዜያዊ ሰብሳቢ



Abere
Senior Member
Posts: 11057
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: < የሃይማኖት ጦርነት ሊነሳ ነው> የማይመስለው ሁሉ ሲሆን አይተናል እና አይግረመን። ዕድሜ ለኦሮሙማ

Post by Abere » 22 Jan 2023, 20:53

sarcasm/ምጸተኛው/

አሽትቱን እንጅ አቅምሱን አያስፈልገንም። ፓትርያርኩ ያሉት ከማህበረ ቅዱሳን በላይ ነው። እኔ ስለማህበረ ቅዱሳን የተከታተልኩት ይሁን ወይም የምከታተለው ትምህርትም ጉዳይም የለኝም።

የትግራይ ጦርነት ይመራ የነበረው በጴንጤ ወይም ፕሮቴስታንት ኦሮሙማ ባለስልጣን እንጅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አልነበረም። ወያኔ የትግራይን ህዝብ አመቻችቶ ለችግር እና መገለል በማቅረቡ ምክንያት ነው - መነኩሴ በገዳማት የሚደፍር ወያኔ ምን አፍ ሊኖረው ይችላል። ለማንኛውም ማህበረ-ቅዱሳን ከደሙ ንጹህ ነኝ - ኦሮሙማ ነው ችግሩን ያመጣው ነው እያለ ያለው። ሚከተለውን አንብበው - መሸጋገሪያውን ተጭነህ።

https://mereja.com/amharic/v2/793153


ይህ መፈንቅለ ፓትርያርክ እየተደረገባቸው ያሉት የትግራይ ክፍለ ሀገር ተወላጅ ናቸው። ከዚህ በፊት ኦሮሙማዎች ጽላት ሰርቀው ወደ ውጭ አገር ሊኮበልሉ ነበር በማለት ሊወነጅሏቸው ነበር። ከዚያም አልፎ በውጭ አገር በስደት እንድኖሩ እና በምትካቸው እንደ እነ ፈይሳ አዱኛ (ቄስ በላ) ወይም የአሁኑ የምስካየ ህዙናን አለቃ ወዘተ ኦነጎች መንበሩን እንድነጥቋቸው በርካታ ተንኮል ተሰርቶባቸው ነበር። እነ አዳነች አበቤ እንድሁ በዚህ ፓትርያርክ ላይ ብዙ ማሳደድ አድርገውባቸዋል። ይህ ሁሉ አልሆን ሲላቸው አሁን በድብቅ በመሽሎክሎክ የስልጣን እና የሃይማኖት ስርቆት ፈጸሙ። ህግ እና መንግስት ያላት አገር ብትሆን በአሁኑ ሰአት እነኝህ የኦሮሙማ የሃማኖት ሌባዎች አዳራቸውን እስር ቤት ማሳለፍ ነበረባቸው። ቀኖና የጣሱ ብቻ ሳይሆን ህገ-ወጥ ተግባር ላይ በመታየታቸው በህግ ቁጥጥር ስር መዋል ነበረባቸው። በዚህ ሰአት ማውራት የሚገባን ይህ ነበር። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ እንድሁ በአስቸኳይ እነኝህን ወንጀለኞች በማውገዝ እና ስልጣናቸውን መሻር ይጠበቅበታል። ይህን የመሰለ እርምጃ መውሰድ ባለመቻሉ ነው ሲኖዶሱ የተደፈረው። ለምሳሌ እኔ በግሌ አዱኛ ፈይሳ( ቄስ በላይ) ተመልሶ ሹመት ተሰጥቶት በማየቴ በሲኖዶሱ እጅግ አዝኛለሁ። የተሰጠውን ህጋዊ ስልጣን የጣሰ፥ቤተ-ክርስቲያን ያፈረሰ፥ ሃይማኖትን መሳለቂያ የደረገ ሀሰተኛ ሰው እንደገና እንዲያስተምር እና ስልጣን ሲሰጠው ሳይ ህዝብ ሃይማኖቱን እንድተው እና ሃይማኖት አባቶች እንድቃለሉ ያደረገ ነው።

አንድ ነገር ግን ይገርመኛል፡ ጥቂት የማይባሉ ትግሬዎች አገር አጥፊዎች ናቸው- ጅሎች። ለምሳሌ አንተ እራስህ ይህጥፋት ትግራይንም እያጠፋ መሆኑን ታውቃለህ ግን በጥፋት ላይ ጥፋት እንድፋፋም ነው በዚህ እድሜህ የምትታክተው። ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ፥አማራን እናጠፋለን ብላችሁ እራሳችሁ ጠፋችሁ። እንድሁ ኦርቶዶክስ እናጠፋለን አላችሁ ኦሮቶዶክስ የትግራይ ህዝብም ሃይማኖት መሆኑን አታውቁም ። እንድሁ በከንቱ ትደክማላችሁ እንጅ ኦርቶዶክስ የሚጠፋ ሃይማኖት አይደለም ቢያንስ በግምት ከ 66 ሚልዮን ህዝብ በላይ ተከታይ አለው - ይህ እንግድህ የሚቆረቆርላት የሌላው እምነት ተከታዮችን አይጨምርም። የሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንነት ነች በስንደ ወይም በዶላር የገባች አይደለችም።

ያለምንም ጥርጥር ይህ ክፍፍል እና ተሳስተው የኦሮሙማን መንገድ የሚከተሉ ከተገኙ የሃይማኖት ጦርነት ሊነሳ ይችላል። ማንም አይቀበለውም የኦሮሙማን ኢ-ቀኖናዊ እና ኢ-ሃይማኖታዊ ተግባር። የሰማዕትነት ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ግን አንዳንድ ትግሬዎች ምን ትጠቀሙ ይሆን? ለመጥፋት ነው የምትፈልጉት? ወይስ ለውርደት? መቸም አትማሩም።

Abere
Senior Member
Posts: 11057
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: < የሃይማኖት ጦርነት ሊነሳ ነው> የማይመስለው ሁሉ ሲሆን አይተናል እና አይግረመን። ዕድሜ ለኦሮሙማ

Post by Abere » 01 Feb 2023, 13:36

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ትናንት አብይ አህመድ ለካቢኔው የሰጠውን የቅጥፈት ነግግር በተመለከተ ዛሬ በመግለጫው ባጋለጠበት መልዕክት መደምደምያ በመንግስት የሚደገፈው ውግዙ ቡድን ላይ ህጋዊ እርምጃ ካልተወሰደበት የሰማዕትነት ተግባር እንደሚፈጽም አስታውቋል። በአብይ አህመድ ዘመን የማይገመተው ሲሆን ብቻ ማየት ነው። ከጎሳው ጦርነት ወደ ሃይማኖት እና መንግስት ጦርነት የመግባት ዕድሉ ሰፊ ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን ( አያድርገው እንጅ) ጦርነት ቢነሳ ከሰይጣን ጋር የሚይደርጉት ፍልሚያ አድርገው ነው የሚወስዱት።

Post Reply