Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5546
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ዋጀሀ ድንቅ (ስድስት ድንቅ ነገሮች)

Post by Naga Tuma » 22 Jan 2023, 02:18

ከወራት በፊት ኣዲስ ሀሳብ ሰማሁ። ጋለሊዮ ጋሌሊ ያግኝቱን ሀሳብ ያገኘዉ ከተቃጠለዉ ኣሌክሳንድርያ ዩኒቨርዚቲ ነዉ ይላል። ከዛ በፊት ሰምቼ ኣላዉቅም። እዉነት ይሁን ኣይሁን ኣላዉቅም። ሀሳቡን ከሰማሁበት ግዜ ጀምሮ ልረሳዉ ኣልቻልኩም።

ከዛ በልጅነት ሳሰማ ያደኩትን ስድስት ድንቅ ነገሮች የሚል ኣስታወሰኝ። ኣሁን ሳስባቸዉ የሳይንስ ምንጮች ሆነዉ ታዩኝ።

1) ለፈ ድሪርሰን መሌ ድሪሬ (ሳይዘረጋ የተዘረጋ ምድር)

ጋለልዮ ጋሌሊ ምድር ዝርግ ኣይዴለቸም ብሏል።

2) ሰሚ ኡቱባ መሌ ዻበቱ (ያለ ምሶሶ የሚቆም ሰማይ)

ኒዉተን ዩኒቨርሳል ግራቭቴሽን ኣግኝቷል።

3) ብሻን ዺበን መሌ ያኡ (ያለ ግፊት የሚፈስ ዉሃ)

ይህ የሚሆነዉ በግራፊቲ ነዉ።

4) ቆራቲ ቆረን መሌ ቆረሙ (ሳይሾል የሚሾል እሾህ)

የዕፅዋት ራስን የመከላከል ሀሳብ

5) ህዲ ሮበ መሌ ገበቱ (ያለ ዝናብ የሚፏፋ እምቧይ)

የዕፅዋት በረሃን የመቋቋም ሳይንስ

6) ኡሞ ዹኩበ መሌ ኣዱ (ያለ በሽታ የምያቃስት ኡሞ [አማርኛ ትርጉሙን ዘነጋክሁ])

በዶክተር ተመርምሮ ነዉ ወይስ ሳይመረመር?

ምን ትላላችጉ?