Ato meleket,Meleket wrote: ↑04 Jan 2023, 08:56እኛ ደግሞ ከመተማው ጦርነት በኋላ፡ አሉላ በኤርትራ ስላጋጠመው ሁኔታ ከኤርትራውያን ተራኪዎች ያገኘነውን እናጋራችኋ! https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=295918&Meleket wrote: ↑18 Jan 2020, 05:14የትግራይ ተራኪዎች እነ ሊቀ ሊቃውንት መምህር ገብረችዳን፣ የመሀል አገሮቹ እነ ተክለጻድቕ መኩሪያና ማሞ ውድነህ እንዲሁም የባህር ማዶዎቹ እነ Richard Pankhurst ሆኑ Haggai Erlich ያልነገሩን አንዳንድ የአሉላ ታሪክ ገጽታዎች በኤርትራዉያን እይታ እንዲህም በትግርኛ ተጽፎ አጋጥሞናል፡ ይዘቱ ጸሐፊዉን የሚመለከት ሲሆን፣ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ይዘቱን ያውቀው ዘንድም በአማርኛ እንዲህ ቀርቧል። መልካም ንባብ።
ራስ አሉላ ወደ መተማ ለጦርነት በሄደበት ወቅት አንዳንድ ኤርትራውያን ተከታዮቹና የሰራዊቱ አባላት አብረውት ዘምተው ነበር። በርካታ ‘መረታ’ የተባለ ወረዳ ተወላጆች ግን አሻፈረን በማለት አብረውት አልሄዱም። ከመተማ ሽንፈቱ በኋላም በቀጥታ በትውልድ የእናቴ ዘሮች አጎቶቼ ወደሚላቸው ወደ መረታዎች በመሄድ፡ “የእናቴ ዘሮች አልከተልም አሉኝ አይደል?” በማለት ለዝርፊያ የመረብን ወንዝ ተሻግሮ እምበይቶ በተባለ ቦታ በሚገኝ የሚካኤል ቤተክርስትያን መረታ ውስጥ ሰፈረ። አቶ መርቆርየዎስ ቃላት የተባሉ የተከላቢ ተወላጅም የአሉላን ሸርና ተንኮል በደንብ ስላጤኑ፡ የሃገራቸውን ሰዎች ሁሉ አስታጥቀው በመጠበቅ፡ አሉላን አፍጉሮ በተባለ መረታ ሰበነ ውስጥ በሚገኝ ቦታ ጦርነት በመግጠም አሸነፉት። አሉላም ሸሽቶ ወደመጣበት ወደ ሃገሩ ተመለሰ። በዚህ መሰረትም ይህ የሚከተለው እንጉርጉሮና ሙሾ ተደረደረላቸው፡
የአባ ነጋን አልጋ ሰይጣን ሲያሳስታት፣
የአሉላን ሹመት ሰይጣን ሲያሳስታት፣
መግጠም ፈለገች ወይ መረታን ጦርነት!
መች የዋዛ ናቸው የመረታ ልጆች፣
መች የዋዛ ናቸው የአቶ ቃላት ልጆች፣
የመጣው ቢመጣ በጽናት መካቾች፣
በአፍጎሮ መሬት በጽናት መክታ፣
ስንትና ስንት ብረት (መሳሪያ) ማረከች መረታ፣
መረታማ ማለት የሃገር አለኝታ፣
ለሃቅ የምትቆም ለዘላለም ጸንታ።
ለዚህ ክዋኔ ጥሩ እማኝ ይሆን ዘንድም ባሻ ደበሳይ የተባለ የባሕረነጋሲ ጭሮም ልጅ ዓዲ ገሃድ የተባለ በእገላ ሓጺን ወረዳ የሚገኝ ቀየ ተወላጅ፡ በዚህ ውጊያ ለተሰዉ ለባሻ ወልደገብርኤል ዘዓረ ለተባለ ለመረታ ተወላጅ እንዲህ በማለት አለቀሱላቸው።
ሰው የማይወጣበት ያንን ገደል፣
መረታን የማያውቅ ማን ይገኛል?
ጦርነት ሲደረግ በአፍጎሮ መሬት፣
መረቶች ሆናችሁ ኃያል ከኃያላት፣
ብትን አረጋችሁት የአሉላን ሰራዊት፣
ልክ እንዲህ ነው እንጂ ወንድነትስ ማለት፣
ገበሬ ሲያሸንፍ ለንጉስ ሰራዊት።
መረታ ትርጉሙ ከሆነ ጀግንነት፣
ባሻ ወልደገብርኤል ለዓላማህ ስትሞት፣
መች ጠላት ወረሳት የሃገርህን መሬት፣
አንተ እንደሁ የሞትከው አይደለም ለውሸት፣
ሃቅን ጨብጠህ ነው ያለፍከው በጽናት።
ጀግናው አቶ መርቆርየዎስ ቃላትም የኋላ ኋላ ከደጃዝማች ባህታ ሓጎስ (ኣባ ጥመር) ጎን ከጣሊያን አንጻር ሲፋለሙ ሓላይ በተባለው ቀየ በጀግንነት ተሰውተዋል።
በርግጥ አራት ራሶች ከነሱም ውስጥ አንዱ ራስ አሉላ ወደ አጤ ሚኒሊክ ዙፋን አዲስ አበባ ድረስ ሂደው ድንጋይ ተሸክመው “ማረን” ብለው ይቅርታን ከአጤ ሚኒልክ እንደለመኑ ማሞ ውድነህ በጻፈው ታሪካቸው ውስጥ እንዳስነበበን አይዘነጋም።
I believe your post was addressed to me. I do believe you are well versed in abyssinian history and hats off to you for that. However, I am not interested about alula the coward who betrayed his negus but on the uncle of kahsay mircha (his mother was the sister of kahsay mircha's father ) known as Baalgada Araya dimtsu.
Can you research and find out about him? Just to help you out, araya dimtsu was a captive of atse tedros at the mekdella Gulag but good for him, he was released along with others by the brits during their expedition in abyssnia.
Now, my question of paramount importance lol.
The son of araya dimtsu (sorry his name escapes my memory. Is it debdib?) was a famous shifta in highland eritrea. The kebessa warlords were having bad time with him.
I am certain that you will share with us about him because you are well versed concerning abyssinian history.
If he is unknown to you then there is no problem.
P. S. I usullay apply the term KAHSAY while that was his proper name.
If you read the memoirs narrated by Napier or Rassam, they address him as KAHSAY.