Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ለመኖር ጠላት ያስፈልጋል? ለመለምለም ጠላት ያስፈልጋል?

Post by Naga Tuma » 08 Dec 2022, 16:59

እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦችን በቅርቡ ነዉ ዜና ዉስጥ የሰማሁኝ። እንግዳ የሆኑብኝ አስተሳሰቦች ናቸዉ።

ለመኖርም ሆነ ለመለምለም ጉብዝና ወይም ታታሪነት ዋና ምንጭ ናቸዉ ብዬ ኣስባለሁ። ጉብዝና የስንፍና ጠላት ነዉ ቢባል ኣይገርመኝም። ስለዚህ ጉብዝና ያኖራል፣ ያለመልማል ቢባል እንግዳ የሆነ አስተሳሰብ ኣይመስለኝም። እንዲሁም ስንፍና ኣያኖርም፣ ኣያለመልምም ቢባል እንግዳ የሆነ አስተሳሰብ ኣይሆንብኝም። ታታሪነትን ማስተማር ባህል ዉስጥ ተቀርጾ ያለ ነዉ። ለምሳሌ ዴጋቱ ገነመ ረፈ የሚባልን መጥቀስ ይቻላል። ጠዋት መተኛት መደህየት ነዉ እንደማለት ነዉ።

ባላዉቀዉም በተለምዶ የኣሜርካ የስለላ ድርጅት ተብሎ የሚታወቀዉ ሲ ኣይ ኤ ጉብዝናን ኣድኖ ተላላኪ ለማድረግ የሚጥር ድርጅት ይመስለኛል። የስለላ ድርጅት ከማለት ማዕከላዊ የሊህቅነት ወኪል ቢባል የበለጠ የሚገልጸዉ ይመስለኛል። ከዚህ የተሻላ ትርጉምም ሊኖረዉ ይችላል። ዋናዉ ሀሳብ መደራጀቱ በልሂቅነት ዙርያ መሆኑ ነዉ። ላለመቀደም መሯሯጥ ያለ ነዉ። ቢሆንም ለመቅደም ከመሯሯጥ አይቀድምም።

ለመኖር ጠላት ያስፈልጋል ማለት፣ ለመለምለም ጠላት ያስፈልጋል ማለት ያለጠላት መኖር ኣይቻልም፣ ያለጠላት መለምለም ኣይቻልም እንደማለት ነዉ።

ታሪክ የምያሳየዉ ይህን ኣይመስለኝም። የበለጸጉ ሃገሮችን ታሪክ ብንቃኝ ጉብዝና እንዳባለጸጋቸዉ ግልጽ ይመስላል።

ጀርመን በጉብዝና መኪናን ለመጀመርያ ጊዜ ፈጠች። እንግሊዝ ለመጀመርያ ጊዜ ባቡር ፈጠረች። አሜሪካ ለመጀመርያ ጊዜ በረራን ፈጠረች። ሩስያ ለመጀመርያ ጊዜ ሳተላይት ፈጠረች። ፉክክራቸዉ በጉብዝና መብለጥ ነዉ።

እነዚህ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸዉ። መጪዉ ትዉልድ በደንብ ማስተዋል ያለበት ይመስለኛል። ጠላት መጣብህ ከማለት ይልቅ ፈጠራን ፈልግ መባል ያለበት ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። ለዚህ ነዉ ትምህርት ላይ መረባረብ ወይም የተጀመረዉን ተረባርቦ መቀጠል የምያስፈልገዉ። ኣብረሆት ተብሎ ከተጀመረ ፈጠራ ብሎ መቀጠል ነዉ። ፈጠራን መፈለግ የግድ ኣዲስ ነገር ብቻ መፍጠር መሆን የለበትም። ተፈጥረዉ አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን በደንብ ማስተዋል እና በተቻለበት ሁሉ ስራ ላይ ማዋል ነዉ።