Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

አዲስ አበባ ሆይ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

Post by Wedi » 08 Dec 2022, 10:35

አዲስ አበባ ሆይ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእስክንድ ነጋ ጡር አለበት። አዲስ አበባን ከኦሮሙማ ስልቀጣ ለመታደግ ቀድሞ የተነሳው እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ጉዳይ በኦሮሙማ በግፍ ታስሮ በሚሰቃይበት ወቅት በአንጻራዊነት ይሻለል በሚባለው የአዲስ አበባ ምርጫ ተብዮ ተውኔት ድምጹን ለእስክንድር ነጋ እንዲሰጥ የተጠየቀው የአዲስ አበባ ሕዝብ ድምጹን የሰጠው ስለ አዲስ አበባ በግፍ ለታሰረው ለእስክንድር ነጋ ሳይሆን ዛሬ በግድ ኦሮምኛ እንዲዘምርና የኦሮሙማን አርማ እንዲያውለበልብ ለሚያደርገው ለአፓርታይዳዊው ኦሮሙማ ነበር።

ዛሬ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በአዲስ አበባ ልጆች ላይ እየተጫነ ያለው የኦሮሙማ መዝሙርና የኦሮሙማ አርማ የአዲስ አበባ ሕዝብ በምርጫው ያገኘው የፍላጎቱ ውጤት ነው። ፈረንጅ 'Elections have consequences' እንዲል እነሆ ዛሬ አዲስ አበቤ ከእስክንድር ነጋ ይሻለኛል ብሎ "የመረጠው" አፓርታይዳዊው ኦሮሙማ እያንዳንዱ አዲስ አበቤ ልጆቹን በኦሮምኛ በግድ እንዲስዘምርና የኦፓርታይዳዊውን ኦሮሙማ የገዳ አርማ ከፍ አድርገው እንዲያውለበልቡ ግዳጅ ተጥሎበታል።

ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ እንዲሉ ዛሬ በየትምሕርት ቤቱ የአዲስ አበባ ልጆች ኦሮምኛ እንዲዘምሩና የኦሮሙማ አርማ እንዲያውለበልቡ ቢገደዱ የአዲስ አበባ ሕዝብ በእስክንድር ነጋ ላይ ክህደት በመፈጸመ በምርጫ ተብዮው ተውኔት ከነእስክንድር ነጋ ይልቅ አፓርታይዳዊው ኦሮሙማ ይሻለኛል በማለት ያመጣው ስለሆነ በምርጫው ባገኘው ውጤት ጣቱን ወደሌላ አካል ሊጠቁም አይችልም። የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ የአዲስ አበባ ልጆች ኦሮምኛ እንዲዘምሩና የኦሮሙማን አርማ እንዲያውለበልቡ እያደረገ ያለው የአዲስ አበባ ሕዝብ የመረጠበትን አላማ እያስፈጸመ ነው።
የአዲስ አበባ ሕዝብ ከአጨብጫቢነት በመውጣት አዲስ አበባን ፊንፊኔያቸው ለማድረግ በኦሮምኛ በግድ እንዲዘምር፣ የኦሮሙማን አርማ እንዲያውለበልብና ኦሮሞ እንዲሆን ከሚያስገድዱት ኦነጋውያን መላቀቅ ከፈለገ የኦሮሙማ ናዚዝም ቀድሞ የገባቸውን የነእስክንድር ነጋን መንገድ በመከተል መደራጀትና መታገገል አለበት።

ኦሮሙማ በአዲስ አበባ ላይ እየደገሰ ያለው መከራ እያንዳንዱ አዲስ አበቤ ኦሮምኛ እንዲዘምርና የገዳ አርማቸውን እንዲያውለበልብ ግዴታ በማድረግ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ኦሮሞ አይደለም፤ ወይም ኦሮሞ አይመስልም እያሉ ከአርሲ፣ ከሐረርጌ፣ ከጅማ፣ ከኢሉባቦር፣ ከወለጋ፣ ወዘተ በግፍ እንሚያፈናቅሏቸው ድኆች ሁሉ ኦሮሞ አይደለም ወይም ኦሮሞ አይመስልም የሚሉትን አዲስ አበቤ ሁሉ ነገ በየቤቱ እየዞሩ ከቤቱ አፈናቅለው፤ እድሜ ልኩን ያፈራኸውን ጥሪት ቀምተው ሜዳ ላይ ይጥሉታል።

ይኽንን የሚጠራጠርና በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ አዲስ አበባ ውስጥ ለማድረግ ስላቀደው አስቀድሞ ይጮኽ የነበረውን እስክንድር ነጋን እንዳበደ ሲቆጠር የነበረ ቢኖር የራሱን ጤነኛነት ይመርመር

By Achamyeleh Tamiru

Please wait, video is loading...

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: አዲስ አበባ ሆይ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

Post by Assegid S. » 08 Dec 2022, 11:08

በትክክል የተገለፅ ትዝብትና ሓሳብ ነው። ዛሬ ልጆቹን ከትምህርት ቤት ለማውጣት የሚራዋጥ ወላጅ፥ ነገ ይሔ ጎሳዊ አርማ መስሪያ-ቤቱ ደጃፍ ደርሶ የኦሮሚያ ፖሊስ አንገቱን እያነቀ ከቢሮው ያወጣዋል።

እኔ የምለው ግን፦ የኣዲስ አበባ ትምህርት ቤት አስተዳደርና ዳይሬክተሮች “ሽምቅ ተዋጊዎች” ሆኑ እንዴ? ድንገት ደርሰው ረብሻ ፈጥረው፣ የሰው ህይወት አጥፍተው የሚሰወሩ? ታዲያ እንዴት ነው የከተማ መስተዳድሩም ሆነ የፌደራል መንግስቱ እነዚህን በኃላፊነት መጠየቅ ያለባቸውን ግለሰቦች በቀጥታ አደብ ማስያዝ ሳይችል ቀርቶ … የ "ፊንፊኔዋ" ከንቲባ - ተልዕኮ ያላቸው በህብረተሰቡ ውስጥ የተደበቁ ግለሰቦች ናቸው - ብለው የሚቀልዱት?

እዚህ ላይ ኣንድ ነገር ትውስ አለኝ፦ ነጋ ጠባ ግቢያቸውና ቢሯቸው እየተረበሸ ችግር ያላቸው አሁንም በስልጣን ላይ ያሉት የኦርቶዶክስ ዕምነት ርዕሰ-ጳጳስ፥ ሴራውን በደንብ የደረሱበት በሚመስል አግባብ ለጠቅላይ ሚንስትሩ በግንባር ያቀረቡት ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር: “እንዴት መንግስት እነዚህን ረብሸኞች መከላከል አቃተው? ነው ወይስ እናንተ ናችሁ የምትልኳቸው?

ይሔ በኣዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤቶች የተጀመረው ረብሻ፦ ተጣምረው የሚሰሩት የጠቅላይ ሚንስትሩ፣ የከንቲባዋ፣ የኣባ ሜንጫና የኦፌኮ ተልኮ እንደሆነ ማንም መጠራጠር የለበትም። ለምን ዓላማ? የሚለውን ለመመለስ በደንብ መጣራት ያለባቸው ኣንድ ወይንም ከዚያም በላይ ግርድፍ ምክንያቶች (crude reasons) ይኖራሉ: የቄሮን ስነ-ልቦና ሽሚያ፣ የወልቃይትና ራያ ባለቤትነት አግባብ፣ የትምህርት ሚንስትሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሥልጣን (አመራር)፣ የጉራጌ ክልልነት ጥያቄና ሌሎችም could be qualitative variables

በኣጠቃላይ ግን የኣዲስ ኣበባ ህዝብ ይህን ዓይን ያወጣ የOPDO colonization አሁን ማስቆም ካልቻለ፥ የሰንደቅ-ዓላማው ጦርነት ከትምህርት ቤቶች ወደ ህዝባዊና መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች መሻገሩ አይቀሬ ነው። አስባችሁታል፦ አቶ በለጠ ሞላና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዛ አርማ ጀርባ በቆመ ህንፃ? ለነገሩ አይደለም የኦሮምያ ለምን የጣልያንን ባንዲራ እንደ lapel pin ደረታቸው ላይ አይውለበለብም … ክራቫት አስረው፣ እግራቸውን አጣምረው ቁጭ ነው! እንጀራ አይደል?!

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: አዲስ አበባ ሆይ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

Post by Za-Ilmaknun » 08 Dec 2022, 11:39

ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ!!

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

ከትናንት በስተያ ኀዳር 27/2015 በኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ ምክንያት በተማሪዎቸ መካከል በተከሰተው ግጭት፣ ከ10 በላይ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የመቁሰል አደጋ ጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡ ከተማሪዎች በተጨማሪ አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር መጎዳቱን አዲስ ማለዳ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የግጭቱ መነሻ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ በትምህርት ቤቱ በመሰቀሉ ቅሬታ ባደረባቸው ተማሪዎች፣ የሰንደቅ አላማውን መሰቀል በሚደግፉ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው ተብሏል፡፡ በዚህም የሰንደቅ አላማውን መሰቀል የማይደግፉ ተማሪዎች እንዲወርድ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ በአንጻሩ መሰቀሉን የሚደግፉት ደግሞ ሰንደቅ አላማው አይወርድም የሚል ውዝግ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታውቋል፡፡

በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ተማሪች ጭምር ከኹለቱም ወገን በሚወረወር ድንጋይ ቆስለዋል፡፡ በሰንደቅ አላማው ይሰቀላል አይሰቀልም ውዝግ በተነሳው ግጭት፣ ጉዳት ያስተናገዱ ተማሪችን ወደ ህክምና ተቋም ለመውስድ ኹለት አንቡላንሶች በትምህርት ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡

የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማውን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ት ቤቶች እንዲሰቀል መንግሥት ከወሰነ በኋላ፣ የተለያዩ አካላት ውሳኔውን ሲቃወሙ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እስከ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማውን በት/ት ቤቶች መሰቀሉን ይቀጥላል ከማለት ውጪ ያሉት ነገር የለም።(አዲስማለዳ)

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11627
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: አዲስ አበባ ሆይ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

Post by Noble Amhara » 08 Dec 2022, 12:14

የኦሮሚያ ባንዲራ የሚባል ነገር የለም የአማራ ባህል ልብስ ነው።





Right
Member
Posts: 2727
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: አዲስ አበባ ሆይ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

Post by Right » 08 Dec 2022, 13:35

A well articulated point. Eskinder did what is expected of him. But Addis residents gave him their middle fingers.
What goes around will come around.
The Amharas massacres that we witnessed in Welega is coming to Addis. Not that it has not been here before. Burayu is part of Addis and it has hosted the Gamo massacre in 2018.
Needless to say the oromonization of the surrounding towns are halfway through the project.

When society allows the likes is Sebhat Nega, Tamrat Layne and other notorious criminals walk freely with their blood soaked hands then something is seriously wrong. Getachew Reda and Megbe are also coming to Addis to live. Just look at the numbers of rural houses burned by General Megbe and look at how his Addis villa maintained and protected. Not a single Molotov cocktail or a stone was thrown to his villa. And people are accusing the US for what ever happened to Ethiopia.
Honestly, something is terribly wrong with our people.

Post Reply