Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ዶ/ር አቢይ የአማራ ሃይሎችን አልካዱም" ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት

Post by sarcasm » 06 Dec 2022, 17:19

Nobody is betraying nobody on this issue. Can anyone really accuse Abiy of changing his mind when what he said from the first weeks of the war is: "ጦርነቱ ክልልን የማስፋት ዓይነት ኣድርጎ የመውሰድ ኣዝማምያዎች ኣሉ። የወሰን ኣካባቢዎች የማስመለስ፤ ኣድርጎ የማቅረብም ሙከራዎች ኣሉ። ይሄም በመሰረቱ ስሕተት ነው። የኣስተዳደር ወሰን ጥያቄ የሚመለስበት ስርዓት ኣለው። ይሄ በግልጽ መታወቅ ኣለበት ?


The Defense Minster said the following after after the start of the war: "ጦርነቱ ክልልን የማስፋት ዓይነት ኣድርጎ የመውሰድ ኣዝማምያዎች ኣሉ። የወሰን ኣካባቢዎች የማስመለስ፤ ኣድርጎ የማቅረብም ሙከራዎች ኣሉ። ይሄም በመሰረቱ ስሕተት ነው። የኣስተዳደር ወሰን ጥያቄ የሚመለስበት ስርዓት ኣለው። ይሄ በግልጽ መታወቅ ኣለበት።" የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዶር ቀነአ ያደታ You cannot get clearer and more direct than that!






የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር ገልጸዋል፡፡


የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ይመለሳል₋የፌዴሬሽን ምክር ቤት
*****************************


የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
የራያ ሕዝብ ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የራያ ሕዝብ የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀረቡ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ምላሽ ሳያገኝ እንደቆየ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ሞትን ጨምሮ ሌሎች በደሎች በራያ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም የቆየ እንደነበረና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ራያዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ እና ንብረታቸውም ሲወድም እንደነበረ ተወካዮቹ በአካል ቀርበው ያስረዱ ሲሆን ጥያቄአችን ምላሽ ሊሰጠው ይገባል በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡

የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር ገልጸዋል፡፡
እንደ ከዚህ በፊቱ የሕዝቦችን ጥያቄ በኃይል ለማፈን የሚደረግ አላስፈላጊ ጫና ከሕገ መንግስቱ የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ማለታቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የሕዝቦችን ጥያቄ ሕግን መሠረት በማድረግ ምላሽ በመስጠት ሕብረብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
Please wait, video is loading...

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4070
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: "ዶ/ር አቢይ የአማራ ሃይሎችን አልካዱም" ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት

Post by Za-Ilmaknun » 06 Dec 2022, 17:45

YilQal has pinpointed the oblivious which escaped the ADP morons whose sole existence is dependent up on serving whoever is willing to claim the throne at Minilik Palace. What is not so clear to all however, is why TPLF never tried to capitalize on this clear and open invitation by OPDO ? Why did TPLF wanted the war if the question was about the Amhara territories which had been under their occupation and, which OPDO subtly always indicates its desire to maintain the then status quo? Or is it safe to conclude that TPLF's adventurous war was about to re-claim arat killo and teach the OPDO novices how inconsequential they are?

Now things are gone outta control and I ain't sure if the PM will dare to displace the people from their ancestral lands of Weqayit and Raya to resettle the Adwans. I wish he tries that and we all will once and for all be out of our current state of misery. Only crossing my fingers!!

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ዶ/ር አቢይ የአማራ ሃይሎችን አልካዱም" ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት

Post by sarcasm » 01 Jan 2023, 20:30

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ፣ የወልቃይት ጉዳይ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ይፈታል ብለዋል፡፡

ከጅምሩ የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስና ሕወሓትን ማጥፋት አልነበረም ያሉት ሬድዋን (አምባሳደር)፣ የጦርነቱ ዋና ዓላማ የነበረው የአገሪቱን ሉዓላዊነት ማስከበርና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ማስፈን የሚሉት እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ሕወሓትን እንደ ፖለቲካ ኃይል የማጥፋት ዓላማ ያለው ሰው ይኖራል፣ ነገር ግን የፌዴራል መንግሥቱ ዓላማ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ወልቃይት በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል ያለ ፀብ ነው፣ በሁለት ክልሎች መካከል ያለው ፀብ ደግሞ የሚፈታው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚመራው ሥርዓት፤›› ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹አንድ ሰው ትግራይን ሲወድ ካርታውን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን ነው፣ ነገር ግን ካርታውን ወዶ ሕዝቡን መጥላት አይቻልም፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ ‹‹ቲፎዞና ደም መርጠን መለቃቀስ ይቅር፣ የትም ቦታ ሰው ሲሞት ሁላችንም ሊሰማን ይገባል፤›› ብለዋል፡፡


‹‹የወልቃይት ጉዳይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚመራው ሥርዓት መሠረት ይፈታል›› ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ

ሲሳይ ሳህሉ
ቀን: January 1, 2023

Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/114349/


Post Reply