Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Ethiopia: A Failed Ethnocracy & The Historic Necessity For A New Political Order

Post by Horus » 06 Dec 2022, 16:49

እኔ ሆረስ ከዚህ ቀደም አንድ ነገር ብዬ ነበር ። ኢትዮጵያ በሁለት አይነት ፖለቲካዎች ተወጥራ ያለች አገር ናት ፤ እነሱም ኤትኖክራሲና ዴሞክራሲ ። ኤትኖክራሲ የሚንቀሳቀሰው በጎሳዎች የሃይል ሚዛን ስሌትና ጦርነት ነው ።

የትግሬ ጦርነት ሲያበቃ አዲስ አይነት የጎሳዎች ሃይል አሰላለፍና ሃይል ሚዛን ይፈጠራል ብዬ ነበር ። ዛሬ እየሆነ ያለው ያ ነው ። የኦሮሞ ተረኞችና ደጋፊ ኦሊጋርኮቻቸው እዚም እዛም እንዳሻቸው የኢትዮጵያ ሕዝቦችን በማዋከብ፣ ዘር በማጽዳት፣ በመከስተርና በማሸማቀቅ ሊገዙ፣ ሊቀጥሉ ያለሙት ቅዠት መና እንደሚሆን ይታወቅ ነበር ።

አሁን ጥያቄው እይተፋፋሙ ያሉት አቅጣጫ የለሽ የርስ በርስ ጦርነቶች እና አመጾች ናቸው ወይስ መሰረታዊ የሆነ አብዮታዊ ሁኔታ እያቆጠቆጠ ነው የሚለው ነው!

ኤትኖክራሲው ባለበት ቀትሎ መልካቸውን የሚለውጡት የጎሳ ርስበር ጦርነቶች ለጊዜው እንጂ ዘላቂ መፍትሄ የስርዓት ለውጥ አያማጡም። ለግዜው ግን ባለው የጎሳ ሕገ መንግስት ስርና ክልል ስርዓት የሰዎችን ደህንነት ይከላከላል ። ወለጋ እየሆነ ያለው ያ ነው ።

ነገር ግን ይህ አገር አቀፍ ትግል እራሱ የክልል ስርዓትን ወደ ማፍረስ ማደግ አለበት ። ትግሉና አመጹ ወደ ከተሞች ሁሉ ማስፋትና መቀናበር አለበት ። ክልሎች እስካሉ ድረስ የትግሬ ጦርነትም አይቆምም፤ የአማራ ኦሮሞ ጦርነት አይቀሬ ነው ፣ አይደለም አማራ ኦሮሞ ገና ደቡብ ክልሎች በጦርነቶች ይሞላሉ ።

ስለ ሆነም አሁን እየተነሳ ያለው ቀውስ ወደ አብዮታዊ ሁኔ መለወጥ አለበት ። ያም ማለት ሕዝቦች አልገዛም ብለው መነሳት አለባቸ፣ ልክ ጉራጌ እንዳለው። የጎሳ አምባ ገነኖች መግዛት የማይችሉበት ሁኒታ ውስጥ መግባት አለባቸው። ባንድ ቃል በጎሳ ተረት ላይ የቆመው የኤትኖክራሲ እምቧይ ካብ መገርሰስ አለበት ።

ኦሮሞያ የተባለ ክልል ሳይፈርስ ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን ሰላም አታገኝም! የኦሮሞ ሕዝብም መቼም ቢሆን ሰላም አያገኝም! ኦሮሞ ከ30 ጎሳዎች ይዋሰናል፣ አማራ አንዱ ብቻ ነው ። ስለዚህ የኦሮሞ ኦሊጋርኮች ገና ከብዙ ጎሳዎች ጋር ጦርነት ይጠብቃቸዋል ምክንያቱም በኢትዮጵያ መሬት ላይ ሌሎች ሕዝቦች አትኖሩም ሊሉ በፍጹም ስለማይችሉ !!!

ይህን ሃቅ በግዜ ሂደት የሚገባቸው ይመስለኛል !!

ሆረስ ዐይነ ብርሃን ነኝ



Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Ethiopia: A Failed Ethnocracy & The Historic Necessity For A New Political Order

Post by Horus » 06 Dec 2022, 17:37

የአቢይ አህመድ ድብቅ መንግስት! አቢይ እራሱ የዚህ መንግስት ቁንጮ ነው

Post Reply