Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12531
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Shocking : ጨለማዋ ቅዳሜ ተብላ በምትጠራዋ ህዳር 14 የኃይለሥላሴ መንግስት ሹማምንት በ393 ጥይት ነው የተጨፈጨፉት ተባለ

Post by Thomas H » 26 Nov 2022, 11:16

ገዳዮቹ...
በየትኛውም ስርአት ወታደር የበላይ አለቃውን ትዕዛዝ የመቀበል ሙያዊ ግዴታ እንዳለበት የታወቀ ቢሆንም አንዳንድ ግዜ ደግሞ ከሙያዊ ግዴታ ይበልጥ የህሊና ጥያቄን ማዳመጥ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም። ሊገድል የመጣን መግደል አንድ ነገር ሆኖ እራሱን ለመከላከል እድሜ ጤናና ሁኔታው ያልፈቀደለትን ፡ የፊጥኝ በካቴና ታስሮ ለነብሱ የሚማጸንን ሰው በመግደል ውስጥ ግን ያለውን የህሊና እረፍት ማጣት እራሳቸው ገዳዮቹ እድሜ ሰጥቷቸው የመሰከሩትን የህሊና ስብራት በብዛት አድምጠናል።
በዛች ቅዳሜ ምሽት የመንግስቱ ኃይለማርያም የግድያ አስፈጻሚ በሆነው በኮሎኔል ዳንኤል አስፋው ትእዛዝ ተቀባይነትና በሻለቃ ጌታቸው ሺበሺ የቡድን መሪነት ሀምሳ ዘጠኙ ሰዎች የመትረየስ ጥይት ተርከፍክፎባቸው ቅሪተ አካላቸው እንዳይገኝ በመቃብራቸው ላይ ኖራ ተነስንሶበታል። የግድያውን ሁኔታ ያጠናው ልዩ አቃቤ ህግ እንደመሰከረው ከሆነ በእለቱ በጠቅላላው 393 ጥይቶች መተኮሳቸው ተረጋግጧል። (በአማካይ ለአንድ ሟች 7 ጥይት እንደማለት ነው) ይህ ቁጥር በደርግ አባላቱ ብቻ የተተኮሰውን የሚያካትት እንጂ በሌሎች ወታደሮች የተተኮሰውን አይጨምርም።
ለደርጉ ሃላፊዎች አዲስ አበባ ወህኒ ቤት ግቢ (በተለምዶአዊ አጠራሩ ከርቸሌ በሚባለውና በአሁን ግዜ የአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት በተገነባበት ግቢ) ውስጥ በአካል ተገኝተው የአፄ ኃይለስላሴን ጄኔራሎችና ሚኒስትሮች ተኩሰው የገደሉ የደርግ አባላት ስም ዝርዝርና የተኮሱት ጥይት መጠን በሻለቃ ጌታቸው ሺበሺ ሪፖርት በተደረገው መሠረት፣
- ሻለቃ ጌታቸው ሺበሺ - 43 ጥይት
- ሻምበል ተፈራ - 32 ጥይት
- ሻምበል ኃይሌ መለስ - 25 ጥይት
- ባሻ ተፈራ ጅፋር - 60 ጥይት
- 50 አለቃ በቀለ ደጉ - 32 ጥይት
- ፒቲ ኦፊሰር ሚካኤል - 25 ጥይት
- 50 አለቃ ዳምጤ - 16 ጥይት
- ወታደር ደጀኔ አ/አገኘሁ - 40 ጥይት
- ወታደር ገብረ ጊዮርጊስ ብርሃኑ - 50 ጥይት
- ሻለቃ ባሻ ለማ ኩምሳ - 7 ጥይት
- ምክትል አስር አለቃ ግርማ አየለ-3 ጥይት ተኩሰው ርሸናውን በትዕዛዙ መሰረት መፈጸማቸውን ሪፖርቱ ያሳያል።
➳ ለግድያው የተሰጠው ደረሰኝ።
የግድያውን አፈጻጸም አስገራሚ ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ለግድያው የተሰጠው ደረሰኝ ነው። በዛች እለት በትዕዛዙ መሰረት ሰዎቹ ተገደሉ። የወህኒ ቤቱ አባል ሻምበል ነጋሽ ማሞ የ60 ሰዎችን አስክሬን ተረክቦ ደረሰኝ ሰጠ። 60ኛው በዛው ዕለት ከደርጉ ጋር ተዋግተው እራሳቸውን የገደሉት የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ የመጀመሪያው ሊቀመንበር የነበሩት የሌ/ጄኔራል አማን ሚካኤል አንዶም አስክሬን ነበር።
ይህ ከሆነ እነሆ ዛሬ 48 ዓመት አስቆጥሯል !!!
ህዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም


Source : #ታሪክን_ወደኋላ