Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በሰላም ይቋጫል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ጦርነት መጠናቀቁን ተከትሎ በኢትዮጲያዊነት ስም ለአንድ ብሄር መታገል ላይመለስ የተቀበረ ስልት ሆኗል

Post by sarcasm » 24 Nov 2022, 21:39

Moges Zewdu Teshome ዛሬ ባሰፈረው ፅሁፍ በሰላም ይቋጫል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ጦርነት መጠናቀቁን ተከትሎ አጠቃላይ ሀገራዊ ጉዳዮችን ወደ ኋላ የተመለሱ፣ በከፊል ወደ ኋላ የተመለሱ እና ወደ ኋላ ሊመለሱ የማይችሉ በሚል በሶስት ከፍሎ አስፍሯቸዋል።

የሱ ሀሳብ እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ኋላ ሊመለሱ የማይችሉ ብሎ ባስቀመጠው ካታጎሪ ውስጥ የኔን ሀሳብ ልጨምር።

በዚህ ጦርነት ሂደት እና የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ አንድ ጎልቶ የወጣ እውነት አለ። ከጦርነቱ በፊት እና በተለይ በዘመነ ኢህአዴግ ጊዜ የብሄር ፖለቲካን እንፀየፋለን በማለት "የኢትዮጲያዊነት ፖለቲካ" በሚል ማዕቀፍ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሀይል ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ የለየለት ብሄርተኛ ከፍ ካለም ዘረኛ መሆኑን በራሱ ያስመሰከረበት ነው።

ይህ ሀይል ከዚህ በኋላ በኢትዮጲያዊነት ፖለቲካ በሚል ካባ ተመልሶ ለመምጣት የሚችልበት እድል በዜሮ የተባዛ ሆኗል።
ይሄ ሀይል በኢትዮጲያ ስም የአንድ ብሄር ፖለቲካ እና ጥያቄ የሚያራምድባቸው አደረጃጀቶች በፖለቲካ፣ በሚዲያ፣ በሲቪል ማህበራት፣ በዲያስፖራ ማህበራት፣ በሀይማኖት ተቋማት፣ በሰብአዊ መብት ተቆርቋሪነት፣ እና በመሳሰሉት ነው።

እንደ እስክንድር ነጋ በኢትዮጲያዊነት ተሞሽሮ በአማራነት መልስ የተጠራ፣ እንደ መስከረም አበራ የብሄር ፖለቲካን ያነወረ መፅሃፍ አሳትሞ መርዝ ዘረኛ ሆኖ የወጣ፣ እንደ ተመስገን ደሳለኝ ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ እያለ ኢትዮጲያያ ከአንድ ጎጥ ውጪ ማየት የተሳነው፣ መላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት ብለህ ከአማራ ውጪ ወደ ውጪ የምትል፣ የኢትዮ-ምናምን የሚል ህብረት ፈጥረህ ከኢትዮጲያን አማራን የሚያስቀድም፣ እነዚህ ምሳሌ እንጂ ዘርዝረን አንጨርሰውም።

ሲጠቃለል ለአማራ ህዝብ መብት መታገል ያለውን አስፈላጊነት ማንም አይክድም። በኢትዮጲያዊነት ስም ለአንድ ብሄር መታገል ግን ላይመለስ የተቀበረ ስልት በመሆኑ በይፋ ብሄርተኝነቱን ተቀላቅለው ለአማራ ህዝብ መታገል አማራጫቸው ነው።

ይሄ ማለት ግን በኢትዮጲያዊነት ስም ፖለቲካ አይኖርም ማለት አይደለም። በኢትዮጲያዊነት ስም ሊመጣ የሚገባው ፖለቲካ ግን በአዲስ ሀሳብ፣ በአዲስ ቅርፅ፣ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ኢትዮጲያዊ በእኩልነት የሚቀበል፣ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ በእኩልነት የሚታገል፣ ብሄር እና ሀይማኖት የማያበላልጥ የእኩልነት ትግል የሚያደርግ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው የኢትዮጲያዊነት ካባ ባለፉት ጥቂት አመታት በራሱ ጊዜ ተቀዳዶ ወልቋል። መልሰህ ልትለብሰው አትችልም። ብትችልም ቀዳዳው ብዙ ነው።
Please wait, video is loading...

Abere
Senior Member
Posts: 11064
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በሰላም ይቋጫል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ጦርነት መጠናቀቁን ተከትሎ በኢትዮጲያዊነት ስም ለአንድ ብሄር መታገል ላይመለስ የተቀበረ ስልት ሆኗል

Post by Abere » 24 Nov 2022, 22:11


ከዚህ ፎረም ላይ ይህን የለጠፈው ጥላቻ የሚያራበው እና የጻፈውም ግለሰብ ጦርነት የሚፈልጉ በቀውስ ውስጥ መኖርን የሚያቀነቅኑ ናቸው። የግጭት ነጋዴ የሆኑት ወያኔዎች አሁን በአረጀው አማራ ጠል የፓለቲካ ታክቲክ ስልታቸው መቀጠል የሚፈልጉ በመሆናቸው ቅዠት ይጽፋሉ። 2 አመት በአማራ ሃይል ተደቁሰው መማር ያልቻሉ፤ በአማራ ፋኖ ወጣት ብሄራዊ ንቅናቄ ከአዲስ አበባ ከመባረራቸው ያልተማሩ ሚልዮን የትግሬ ወጣ አስጨርሰው የዛሬ 50 አመት ከነበሩበት የጎሳ ግጭት ፓለቲካ ላይ ባሉበት ቁመው የቀሩ ናቸው። የትግሬ ወያኔዎች በትግራይ ላይ ያደረሱትን ውድቀት እና ውርደት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንድ ደርስ የሙጥኝ ብለው እየታከቱ ያሉ እኩይ ፍጡራን ናቸው። ትግራይ በወያኔ ምንክያት ከፍተኛ ኪሳራ ተወራርዶባታል አሁን ይህን መጥፎ ዕድል በኦሮሞ ህዝብ ላይ አክራሪነት እና ጸያፍ አማራ ጠልነት በማጧጧፍ የዕልቂት እሳት ለመመቆ ነው። ለዚህ ነው ጦርነት ያሳከከው ወያኔ ትግሬ አሁን አማራ ጠልነት በየኢንተርኔት ጢሻው እንደ ውሻ ቡፍ ቡፍ የሚለው። አማራን ጠልታ ይሁን አሸንፋ ልትኖር የምትችል ኢትዮጵያ አትኖርም። እነዚያ የስቃይ 31 አመታት ተቋጭተዋል። አማራ የሚሰቃይ ከሆነ ሌላው በስቃይ ይቀጥላል። ኢትዮጵያ የቁማር አገር አትሆንም። ይህ በነበረበት ቁሞ የቀረ ወያኔ ወሬ ነው።



Post Reply