የሱ ሀሳብ እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ኋላ ሊመለሱ የማይችሉ ብሎ ባስቀመጠው ካታጎሪ ውስጥ የኔን ሀሳብ ልጨምር።
በዚህ ጦርነት ሂደት እና የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ አንድ ጎልቶ የወጣ እውነት አለ። ከጦርነቱ በፊት እና በተለይ በዘመነ ኢህአዴግ ጊዜ የብሄር ፖለቲካን እንፀየፋለን በማለት "የኢትዮጲያዊነት ፖለቲካ" በሚል ማዕቀፍ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሀይል ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ የለየለት ብሄርተኛ ከፍ ካለም ዘረኛ መሆኑን በራሱ ያስመሰከረበት ነው።
ይህ ሀይል ከዚህ በኋላ በኢትዮጲያዊነት ፖለቲካ በሚል ካባ ተመልሶ ለመምጣት የሚችልበት እድል በዜሮ የተባዛ ሆኗል።
ይሄ ሀይል በኢትዮጲያ ስም የአንድ ብሄር ፖለቲካ እና ጥያቄ የሚያራምድባቸው አደረጃጀቶች በፖለቲካ፣ በሚዲያ፣ በሲቪል ማህበራት፣ በዲያስፖራ ማህበራት፣ በሀይማኖት ተቋማት፣ በሰብአዊ መብት ተቆርቋሪነት፣ እና በመሳሰሉት ነው።
እንደ እስክንድር ነጋ በኢትዮጲያዊነት ተሞሽሮ በአማራነት መልስ የተጠራ፣ እንደ መስከረም አበራ የብሄር ፖለቲካን ያነወረ መፅሃፍ አሳትሞ መርዝ ዘረኛ ሆኖ የወጣ፣ እንደ ተመስገን ደሳለኝ ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ እያለ ኢትዮጲያያ ከአንድ ጎጥ ውጪ ማየት የተሳነው፣ መላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት ብለህ ከአማራ ውጪ ወደ ውጪ የምትል፣ የኢትዮ-ምናምን የሚል ህብረት ፈጥረህ ከኢትዮጲያን አማራን የሚያስቀድም፣ እነዚህ ምሳሌ እንጂ ዘርዝረን አንጨርሰውም።
ሲጠቃለል ለአማራ ህዝብ መብት መታገል ያለውን አስፈላጊነት ማንም አይክድም። በኢትዮጲያዊነት ስም ለአንድ ብሄር መታገል ግን ላይመለስ የተቀበረ ስልት በመሆኑ በይፋ ብሄርተኝነቱን ተቀላቅለው ለአማራ ህዝብ መታገል አማራጫቸው ነው።
ይሄ ማለት ግን በኢትዮጲያዊነት ስም ፖለቲካ አይኖርም ማለት አይደለም። በኢትዮጲያዊነት ስም ሊመጣ የሚገባው ፖለቲካ ግን በአዲስ ሀሳብ፣ በአዲስ ቅርፅ፣ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ኢትዮጲያዊ በእኩልነት የሚቀበል፣ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ በእኩልነት የሚታገል፣ ብሄር እና ሀይማኖት የማያበላልጥ የእኩልነት ትግል የሚያደርግ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው የኢትዮጲያዊነት ካባ ባለፉት ጥቂት አመታት በራሱ ጊዜ ተቀዳዶ ወልቋል። መልሰህ ልትለብሰው አትችልም። ብትችልም ቀዳዳው ብዙ ነው።
Please wait, video is loading...