Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Shimales Abdissa on Fire, he failed to execute his job adequately

Post by Horus » 24 Nov 2022, 20:08

temari,
ካንተ ጋር ብዙ የምስማማቸው ነገሮች እንዳሉኝ ከዚህ ቀደም ነግሬሃለሁ ። አሁን እንደ ምንም ብለህ 'ዲፌንድ ዘ ትሩሽ'ን ከኦሮሙማ አዳዲስ ሌቦች ነጻ ሆኖ አለምን እንዲያይ አስተምርልን ።

አንተ እራስህ ዛሬ ወይም ትላንት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስለሚያደርጋቸው ምርምሮችና የነዚያ ምርምሮች ማህበራዊ ፋይዳ ወይም ኢምፓክ ቪዲዮ ለጥፈህ በጥሞና ተከታተልኩት ። ፕ/ር ጣሰው ወልደ ሃና የቻይልድ ዴቬሎፕመንት እስፔሺያልሲት ይመስለኛ ። እሱ የሰራቸው የህጻናት እድገት ሳይንስ ባለም ላይ አሁን ያደጉ አገሮች የሚሰሩበት ፓራዳይም ነው ። ዘ ፈርስት 5 (The First 5) ይባላል ። ለመጀምሪያው 5 አመት እድሜያቸው ላይ የሚሰራው ስራ ሲያድጉ የሚደርሱብትን ደረጃ ይወስናል ። እጅግ ድንቅ የሆነ የቻይልድ ስይኮሎጂን፣ ቻይልድ ዴቬሎፕመንትና ፓፕሊክ ሄልዝ መስክ ነው ።

እራሱ ሳይንቲስቱ እንደ ነገረን ለ22 አመት ያደረጋቸው ጥናቶች አሁን ተቀባይነት አፍ ኝቶ በፖሊሲ ደረጃ መንግስት ሊተገብረው እየሞከና አያይዞም አቢይና ሺመልስ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ እያደረጉት ነው ። ከጥቂት ቀን በፊት 'ዲፌንድ ዘ ትሩዥ' የሺመልስን ፕሮፓጋንዳ ቪዲዮ ለጥፎ እኔን ሆረስ ሊተች ሞከረ። ነገር ግን አንድም ቦታ የዚህን ምርምርና ፖሊሲ ባለቤት የሆነውን ጣሰው ወልደ ሃና አንድ ቦታ አያነሳውም ። ይህ ነው ቆሻሻ ሌብነት ፣ ስልቃጭነት ፣ ሁሉም የኔ ባይ የተረኞች ቆሻሻ በሽታ ።

ሺመልስት አብዲሳ ከስልጣን መባረር አለበት ብዬ የዛሬ ሁለት አመት ስጽፍ ዴፌንድ ዘ ትሩዝ (Shimels is here to stay) ያለው ዲቲቲ ነው አሁን ምጢጢ ትችት በዘረኛው ሺመልስ ላይ ለማቅረብ ሚዳዳው።

በእርሻም፣ በትምህርትም፣ በህጻናት ምገባም ዋናውን ስራ የሰሩት ሌሎች ግዙፍ ምሁራን እንጂ ሺመልስ የሚባል የቄሮ ወጠጤ አይደለም ። የሚትዮጵያን እርሻ ለማዘመን ላለፈው 50 አመት የለፉት አግሮኖሚስቶች፣ የእርሻ ሃንዲሶች፣ የአፈር ሳይንቲስቶች ናቸው የሺህ መሻሻል ባለቤቶች ። ትምህርት መስክም እነፕሮፌሰር ብርሃቡ ገና ገና ትልቅ ደረጃ ያደርሱታል ።

ልብ በል ይህን ሰሞን ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብዙ ብዙ እየተባለ ያለው ይህ ተቋም የመጀምሪያው ከመንግስት ሙሉ በሙሉ ነጻ የሆነ የአካዳሚክና ምርምር ኢንስቲቲውሽን ሆኖ እራሱን እንዲያስተዳድርና ሙሉ የአካዳሚክ ነጻነት እንዲኖረው ስለተወሰነ ነው ፣ ያ ፖሊሲ ደሞ የፕ/ር ብርሃኑ የመጀምሪያ አቋማና ፖሊሲው ሆኖ ፣ አሁን ሁሉንም ኮሌጆች ብቁ ሆነው ሲገኙ ነጻ ኢንስቲቲውሽን ሊያደርጋቸው ቆርጦ ተነስቷል።

የሺመልስ ቄሮዎች እስከ ትላንት ድረስ ፈተና በመስረቅ እያለፉ የሺመልስ መንግስት ውስጥ በዘር ኮታ ገብተው ዛሬ የኦሮሞን ሕዝብ በነጭ ጸሃይ የሚሰርቁት ናቸው ።

እባክህን በፈጣሪ ብለህ ዲ ቲ ቲ ን ከዚህ ወርደትና የሺምልስ ሌቦች መንጋ እንዲላቀቅ አንዳች በለው!!!


DefendTheTruth
Member+
Posts: 9857
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: Shimales Abdissa on Fire, he failed to execute his job adequately

Post by DefendTheTruth » 27 Nov 2022, 09:55

Shime,

you seem to have crossed the red-line, or tolerated those who opted to cross it. It is time now to settle the balance-sheet with you.

You have the right to clear your name in the court of law.
Please wait, video is loading...



Post Reply