Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Meleket » 03 Nov 2022, 07:21

ውሾቹን “ተው” በሏቸው
በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

በኦሮምኛ አንድ ድንቅ ተረት አለ። በአንድ የኦሮሞ መንደር ውስጥ ሮቤል መገራ የሚባሉ ጥበበኛ ሽማግሌ ነበሩ። አንድ ቀን የሁለት ጎረቤታሞች ንብረት የሆኑ ሁለት ውሾት ሲጣሉ ያያሉ። እኒህ ጥበበኛ ሽማግሌም “እነዚህ ውሾችን እንገላግላቸው፤ ያለበለዚያ ችግራቸው ለሁላችንም ይተርፋል። በዓለም ላይ ችግር የሚነሣው ከአጥንት በላይ ማሰብ በማይችሉ ውሾች የተነሣ ነው” ይላሉ። በአካባቢው የነበሩ ሽማግሌዎች እና መንገደኞችም በሽማግሌው አባባል ተገርመው “ሁለት ውሾች ተጣልተው ምን ሊያመጡ ነው” እያሉ ሳቁባቸው።

በዚህ መካከል ከሁለቱ ጐረቤታሞች መካከል አንድ ልጅ ወጣና የውሾቹን ጠብ ተመለከተ። የእርሱ ውሻ የተበደለ ስለመሰለው ፍልጥ አምጥቶ ያኛውን ውሻ ደበደበው። ወዲያውም ከሌላኛው ቤት ሌላ ልጅ ወጣና ያኛውን ውሻ መደብደብ ጀመረ። ነገሩ ወደ ልጆቹ ተዛመተና በውሾቹ ምትክ ልጆቹ ይደባደቡ ጀመር። ሽማግሌውም “እባካችሁ እነዚህን ልጆች አስታርቁ” አሉ። በሥፍራው የነበሩትም “ተዋቸው ይዋጣላቸው” ብለው እንደ ቀልድ አለፉት።

ልጆቹ እየተደባደቡ እያሉ የአንዱ እናት ብቅ ኣለች። ወዲያውም ያኛውን ልጅ በፍልጥ ታንቆራጥጠው ጀመር። የልጇን ጩኸት የሰማቺው ሌላ እናትም። . . . “ሁለት ሴቶች ተጣልተው የት ይደርሳሉ” እያሉ ንቀው ተውት።

. . . እንዴት ሚስቴን ትመቻታለሽ ብሎ የዚኛይቱን ሴት መደብደብ ያዘ። ይኼኔ ነገሩን የሰማው ሌላኛው ባልም ሲሮጥ መጥቶ ድብድቡን ተቀላቀለ። . . .

http://www.danielkibret.com/2011/12/blog-post_26.html

መልእክቱ መቼም ግልጥ ነው። በዚህም በዚያም የሚራወጡ ተራ ካድሬዎችን ጀሮ ባለመስጠት፡ ለሰላም መትጋት ያስፈልጋል። ከተቻለም እንደ ሮቤል መገራ ምክር፡ "ውሾቹን 'ተው' ማለት" ይገባል፤ አደፍርሶችን ዕድል መንሳት ያሻል፡ "ሳይቃጠል በቅጠል" ነው ነገሩ። :mrgreen:

Wedi
Member+
Posts: 7996
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Wedi » 03 Nov 2022, 07:34

ስለወያኔ ከታች በቪድዮ ያለው የተናገረው ሳይጣን ዳንኤል ክስረት "ተበታትኖ ዶቄት ሆኗል" የተባለው እና እሱ አምርሮ የሚጠላው ወያኔ ሻንጣውን ተሸክሞ አዲስ አበባ መጥቶ ከእሱ ጎን ፕርላማ ወንበር ውስጥ ሲቀመጥ ምን ይሰማው ይሆን?
:lol: :P
Please wait, video is loading...

Educator
Member
Posts: 2015
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Educator » 03 Nov 2022, 07:48

Amen.
Meleket wrote:
03 Nov 2022, 07:21
ውሾቹን “ተው” በሏቸው
በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

በኦሮምኛ አንድ ድንቅ ተረት አለ። በአንድ የኦሮሞ መንደር ውስጥ ሮቤል መገራ የሚባሉ ጥበበኛ ሽማግሌ ነበሩ። አንድ ቀን የሁለት ጎረቤታሞች ንብረት የሆኑ ሁለት ውሾት ሲጣሉ ያያሉ። እኒህ ጥበበኛ ሽማግሌም “እነዚህ ውሾችን እንገላግላቸው፤ ያለበለዚያ ችግራቸው ለሁላችንም ይተርፋል። በዓለም ላይ ችግር የሚነሣው ከአጥንት በላይ ማሰብ በማይችሉ ውሾች የተነሣ ነው” ይላሉ። በአካባቢው የነበሩ ሽማግሌዎች እና መንገደኞችም በሽማግሌው አባባል ተገርመው “ሁለት ውሾች ተጣልተው ምን ሊያመጡ ነው” እያሉ ሳቁባቸው።

በዚህ መካከል ከሁለቱ ጐረቤታሞች መካከል አንድ ልጅ ወጣና የውሾቹን ጠብ ተመለከተ። የእርሱ ውሻ የተበደለ ስለመሰለው ፍልጥ አምጥቶ ያኛውን ውሻ ደበደበው። ወዲያውም ከሌላኛው ቤት ሌላ ልጅ ወጣና ያኛውን ውሻ መደብደብ ጀመረ። ነገሩ ወደ ልጆቹ ተዛመተና በውሾቹ ምትክ ልጆቹ ይደባደቡ ጀመር። ሽማግሌውም “እባካችሁ እነዚህን ልጆች አስታርቁ” አሉ። በሥፍራው የነበሩትም “ተዋቸው ይዋጣላቸው” ብለው እንደ ቀልድ አለፉት።

ልጆቹ እየተደባደቡ እያሉ የአንዱ እናት ብቅ ኣለች። ወዲያውም ያኛውን ልጅ በፍልጥ ታንቆራጥጠው ጀመር። የልጇን ጩኸት የሰማቺው ሌላ እናትም። . . . “ሁለት ሴቶች ተጣልተው የት ይደርሳሉ” እያሉ ንቀው ተውት።

. . . እንዴት ሚስቴን ትመቻታለሽ ብሎ የዚኛይቱን ሴት መደብደብ ያዘ። ይኼኔ ነገሩን የሰማው ሌላኛው ባልም ሲሮጥ መጥቶ ድብድቡን ተቀላቀለ። . . .

http://www.danielkibret.com/2011/12/blog-post_26.html

መልእክቱ መቼም ግልጥ ነው። በዚህም በዚያም የሚራወጡ ተራ ካድሬዎችን ጀሮ ባለመስጠት፡ ለሰላም መትጋት ያስፈልጋል። ከተቻለም እንደ ሮቤል መገራ ምክር፡ "ውሾቹን 'ተው' ማለት" ይገባል፤ አደፍርሶችን ዕድል መንሳት ያሻል፡ "ሳይቃጠል በቅጠል" ነው ነገሩ። :mrgreen:

Axumezana
Senior Member
Posts: 13645
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Axumezana » 03 Nov 2022, 08:29

ደብተራ፥ መለከት፥ የደብተራ፥ ዳንኤል፥ ክስረትን፥ አስተሳሰብን፥ ደጋፊ፥ ከሆንክ፥ ጤነኞነትህን፥ መርምር!

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Meleket » 03 Nov 2022, 10:27

ወዳጃችን Wedi እንኳን የዕርቀሰላምን ድምጽ ለመስማት በቃህ እያልኩ፡ ዲያቆኑ ከወንድሞቹ ጋር ፓርላማ ጎን መቀመጥ ላይ ከደረሱ፡ መልካም ነገር ነው። ከብጥብጥ በምንም መልኩ በጠረጼዛ ዙርያ በሃሳብ መፋተጉ ሳይሻል ኣይቀርም።

በነገራችን ላይ ጠቅላዩ የሚጠቀሙባት "አየር ላይ የተበተነ ዱቄት" የምትለውን አባባል ከዬት እንደተዋሷት ጥርጣሬያችንን እናጋራህን?

ኤርትራዊው 'ወንጌላዊና ጋዜጠኛ' ገዛኢ ዮሃንስ ማለትም የኤልሻዳይ መጽሔት መስራች ከGMM TV ጋር "ህያዉ ምስክር" በሚለው ፕሮግራም ከጋዜጠኛ ተስፋዬ ካሳሁን ጋር 3 ክፍል 'ምስክርነት' አድርጎ ነበር። እናማ በ1977ዓ.ም. ያጋጠመውን ጉዳይ በሶስተኛው ክፍል ቃለመጠየቁ ከ33 ደቂቃ ጀምረህ ስማውማ። በተለዪ ግን ትክክል ለመሆን 35፡39 ደቂቃ ላይ የሚለውን ስማው። ምንም እንኳ ኣገላለጹ የቄሮንና የፋኖን ሚያ በሚገባ ባይገልጸውም፤ ጠቅላዩ ስለተጠቀሙበት አባባል ግን ቍልጭ አድርጎ ገልጾታል።
:mrgreen:
Wedi wrote:
03 Nov 2022, 07:34
ስለወያኔ ከታች በቪድዮ ያለው የተናገረው ሳይጣን ዳንኤል ክስረት "ተበታትኖ ዶቄት ሆኗል" የተባለው እና እሱ አምርሮ የሚጠላው ወያኔ ሻንጣውን ተሸክሞ አዲስ አበባ መጥቶ ከእሱ ጎን ፕርላማ ወንበር ውስጥ ሲቀመጥ ምን ይሰማው ይሆን?
:lol: :P
Please wait, video is loading...

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Meleket » 03 Nov 2022, 10:33

ወዳጃችን Axumezana የማንኛውም ሰው ደጋፊም ተቃዋሚም አይደለንም። ከማንኛውም ሰው የሚደገፍ ሃሳብም የሚተች ሃሳብም ሊኖር ይችላል ብለን እናምናለን። ምክንያቱም የሰው ልጆች ፍጹማን ኣይደለንምና። :mrgreen:
Axumezana wrote:
03 Nov 2022, 08:29
ደብተራ፥ መለከት፥ የደብተራ፥ ዳንኤል፥ ክስረትን፥ አስተሳሰብን፥ ደጋፊ፥ ከሆንክ፥ ጤነኞነትህን፥ መርምር!

Right
Member
Posts: 2832
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Right » 03 Nov 2022, 10:35

At least he believes PP is a dog devoid of thinking Afar. Just like the other dog TPLF.
He mentioned about cadres of both group. He is one stinky cadre.

Wedi
Member+
Posts: 7996
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Wedi » 03 Nov 2022, 10:40

ወዳጄ Meleket "ዲያቆን" እንዲህ ጨካኝ ከሆነ እምነት ዋጋ የለውም ማለት ነው!! :lol: :lol:

በነገራችን ላይ ብዙዎቹ ይህን ወሰስላታ ዲያቆን ተብዬ የቤተመንግስቱ የተረት አባት እያሉ ነው የሚጠሩት!! አብይ አህመድ የሚተርታቸው ተረቶች በሙሉ ምንጫቸው ይኸው ወስላታ ሰው ነው!!

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Meleket » 03 Nov 2022, 10:52

ወዳጃችን Wedi እንግዲህ ይህን ጉዳይ ለሱ ለኅሊናው እንተውለት። ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ይህ ዲያቆን ዕርቀሰላም አውርዶ፡ በጋራ ለጥዮን ማርያም ባንድላይ አዅሱም ላይ ቢቀድሱ መልካም ነው። እሳቸው እንደ ፓትርያርክነታቸው እሱም እንደ ድቁናው!በዚህም በዚያም ግን ልብ ይንጻ! :mrgreen:
Wedi wrote:
03 Nov 2022, 10:40
ወዳጄ Meleket "ዲያቆን" እንዲህ ጨካኝ ከሆነ እምነት ዋጋ የለውም ማለት ነው!! :lol: :lol:

በነገራችን ላይ ብዙዎቹ ይህን ወሰስላታ ዲያቆን ተብዬ የቤተመንግስቱ የተረት አባት እያሉ ነው የሚጠሩት!! አብይ አህመድ የሚተርታቸው ተረቶች በሙሉ ምንጫቸው ይኸው ወስላታ ሰው ነው!!

Axumezana
Senior Member
Posts: 13645
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Axumezana » 03 Nov 2022, 17:42

ደብተራ፥ መለከት፥ ማርያም፥ ጽዮን፥ እንጂ፥ ጥዮን፥ማርያምን፥ ከዬት፥ አመጣኸው? ነው፥ ወይስ ፀለምትን፥ ጠለምት፥ ብለው፥ እንደሚጠሩት፥ መሆን፥ ፈለክ፥?

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ውሾቹን “ተው” በሏቸው! በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Post by Meleket » 04 Nov 2022, 02:57

ወዳጃችን Axumezana ለዘመነ እርቀሰላም እንኳን ኣበቃህ።

አባባልህና ጥያቄህ ገብቶናል። እንደኛ ኣመለካከት፡ ጥዮን አልከው ጽዮን ወይም ጭዮን፡ ጠለምት አልከው ፀለምት፡ ጠገዴ ኣልከው ጸገዴ፡ ምንም ልዩነት የለውም። ዋናው ልንለው የፈለግነው ከገባህ፡ አንተ የምትለው አባባልም ለኛ ከገባን በቂ ነው። ነገሩን በየዋህነት ተቀብሎ መግባባቱ ላይ ነው ምስጢሩ።

ትንሽ ስለ ፊደልና ድምጽ ካነበብነው

እኛ አገር ፀሐይን ጨሐይ የሚሉ አሉ። በየን መጺካ? ለማለት በየን መጪካ? ይላሉ፡ አባባሉን ከቀደምቶቻቸው ወርሰው ማለት ነው። ታድያ የቋንቋና የፊደላት የሆሂያት ተመራማሪዎች ሲመራመሩ የት ደረሱ መሰለህ። . . . ጨ፣ ሸ፡ ኸ ወዘተ የተባሉ ፊደሎች የተፈጠሩት ትግርኛና ኣማርኛ ወደ ጽሑፍ ከገቡ በኋላ ነው። (ግዕዙ ላይ ዬሉም መሰል . . . እባካችሁ የቋንቋና የፊደላት ሊቃውንት ካላችሁ ጉዳዩን አብራሩልንና፡ አብረን እንማር)
ምሳሌዎች
ጨው - ፄው
ጨሐይ - ፀሐይ - ጠሐይ
መጩ - መፅአ - መጣ
ጭዮን - ጽዮን - ጥዮን
ተጨዉየ - ተፄወወ
ተቀቢጩ - ተቀቢፁ
በዅበዀ - በኁበኈ . . . ወዘተ

እና ምን ለማለት ነው መሰለህ በግዕዝ በ"ፀ" ቢጻፍም ድምጹ ግን የ"ጨ" ነው። ስለዚህ የፊደሎች አደማመጥ ጉዳይ ክቡር ተጋዳላይ ዶ/ር ኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ የጻፉት ነገር ነበር፡ ካገኘነው አንድ ቀን እናጋርሃለን። አንተም ከግዕዝ ትግርኛ አማርኛ ጽሑፍና ከፊደላት ዙርያ ያነበብከው ወይ የተመራመረ ሰው ካለ ይዞታውን አካፍለን ባክህ እንማማርበት። ህዝባችን እንዲህ መመራመር እንጂ በረባ ባረባው ሰይፍ መማዘዝ ቢበቃው የሚሻል አይመስልህም?

እና ጥዮን ማርያም ወይ ማርያም ጥዮን ወይም ማርያም ጭዮን የሚል አጻጻፍ ካጋጠመህ አንተ በሚገባህ “ማርያም ጽዮን” ብለህ ተረዳው። እኛ እላይ የጻፍነው ምንም ዓይነት ቦተሊካዊ ትርጉም የለውም ምክንያቱም አማርኛ ሆነ ትግርኛ ሁለቱም መግባቢያ እንጂ መናቆሪያ መሆን የማይገባቸው የአንድ እናት ልጆች ናቸውና . . . የ'ጥዮን' ማለትም የ'ጽዮን' ኣዎን የ'ጭዮን'ም! አይመስልህም ወዳጃችን?
:mrgreen:
Axumezana wrote:
03 Nov 2022, 17:42
ደብተራ፥ መለከት፥ ማርያም፥ ጽዮን፥ እንጂ፥ ጥዮን፥ማርያምን፥ ከዬት፥ አመጣኸው? ነው፥ ወይስ ፀለምትን፥ ጠለምት፥ ብለው፥ እንደሚጠሩት፥ መሆን፥ ፈለክ፥?

Post Reply