Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 21 Oct 2022, 09:44

ይህን ጽሁፍ ወንድማችን Abere በኣማርኛ ተርጉመን፡ ለሰፊው አንባቢ እንድናቀርብ በጠዬቀን መሰረት፡ እነሆ ጀምረነዋል። ከምዚ በሚቀጥለው ክፍል የደራሲውን ትረካ፡ እንደወረደ በተወላገደው አማርኛችን ለማቅረብ እንሞክራለን፡ መጀመርያ ግን በዚህ ጽሑፍ ኣሟሽተነዋል። መልካ ንባብ። :mrgreen:
Meleket wrote:
21 Oct 2022, 04:07
ወንድም Abere፡ እዚህ የምትጽፋቸውንና የምታራምደውን አካሄድ በማዬት፡ ኣንተ ለእውቀት ያለህ ኣመለካከት ሁነኛ መሆኑን ተረድተናል። ኣንዳንድ ሰዎች "እኛ ብቻ እንናገር፡ እኛ ብቻ ነን ሃቀኞች፡ እነ እገሌ ሃሰተኞች ናቸው፡ እኛን ብቻ ስሙ" ብለው ስም ሊያጠለሹ ሲሞክሩ፡ ኣንተ ደግሞ “መናገር የሚፈልግ ይናገር፡ እኛ ደግሞ እንስሶች ኣይደለንም ኣእምሮ ያለን ለባዊ ፍጥረቶች ነንና መርምረን እውነቱን ከሃሰቱ ራሳችን እንለያለን" የምትል፡ ጎበዝ የእውቀት ሰውና የህዝብህ ሁኔታ የሚያንገበግብህ ዜጋ እንጂ “እረኞች ፈቅደው ባሰማሩት ቦታ ብቻ እንደሚግጥ ከብት" ማለትም መናኛ ካድሬ ኣለመሆንህን ተረድተናል። በመሆኑም ለአንተና ያንተ ለሆኑት ሁሉ ክብር የዚህን ጽሑፍ የአማርኛ ትርጉምም ለማቅረብ እንሞክራለን

ጽሑፉን የጻፉት ኣባት ኤርትራዊ የነጻነት ታጋይ ማለትም ሻዕብያና ኣባም ናቸው፡ ኤርትራ ውስጥ በርካታ መጻሕፍት ጽፈዋል ተብለው ከሚጠቀሱት ሰዎች መካከል ኣንዱ እኒህ ኣባት ናቸው። የመጻሕፍታቸው ዝርዝር አርእስት እዚህ ይገኛል https://mereja.com/forum/viewtopic.php? ... 8&start=20 ኤርትራዊው የነጻነት ታጋይ ኣባ ይስሃቅ ገብረኢየሱስ በአንድ የአውሮፓ ዩኒቨርሲቲም ለእውቀት መስፋፋት ያደረጉትን ጥረት በማዬት ይመስለናል የክብር ዶክትሬት ማእረግ ተሰጥቷቸዋል። . . . እንደነ ጥላሁን ገሠሠና ቴዲ ኣፍሮ ወዘተ መሆኑ ነው መሰል።

ይሄኛውን ጽሁፋቸው ያጠናከሩት፡ ከ1897 እስከ 1907 ኤርትራን ‘ያስተዳደረው’ ኢጣሊያዊው ፈርዲናንዶ ማርቲኒ “ዲያርዮ አሪትረዮ፡ አርትራዊ ‘ዜናመዋዕል’” በሚል ርእስ የ10 ዓመታት ዕለታዊ መረጃዎቹን፡ በ4 ትልልቅ ቅጾች በጠቅላላ 2626 ገጽ ባዘለው የ19,300 ዝርዝር መረጃዎችን ከሰነደባቸው መጻሕፍት ውስጥ ቀንጭበው ያቀረቡት ነው።

እንደሚታወቀው በተለያዩ አካላት መካከል፡ ቅዱስ ኪዳን (ቃልኪዳን) ወይ ውል እንዳለ ሁሉ “ዘይቅዱስ” ማለትም ቅዱስ ያልሆነ ኢፍትሓዊ ወይ ርካሽ ኪዳን (ውል) ስምምነትም ኣለ። እንደ እርሳቸው አመለካከት በጣልያንና በምኒልክ መካከል የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ ቅዱስ ያልሆነ ኪዳን ተደርጎ ነበር፡ በማለት በማስረጃ አስደግፈው ለመግለጽ ሞክረዋል። ጽሑፉ ኤርትራውያንን ያለመ ነው። እዚህ መረጃ ላይም በርካታ ኤርትራውያን ይኖራሉ ብለን ስለገመትን፡ ታሪኩን ለማያውቁ ኤርትራውያን ይጠቅም ዘንድ፡ በትግርኛ እንዳለ ለመጋራት እንሞክራለን። ለኢትዮጵያውያን አንባቢዎችም ሊጠቅም ስለሚችልም፡ በጥያቄህ መሰረት በተወላገደው ኣማርኛችን ተርጉመን አዲስ ርእስ በመክፈት እዚያ ለማቅረብ እንሞክራለን። እዚህኛው ክፍል ግን በትግርኛው ትርክት እንቀጥላለን።

ቍምነገሩ፡እነ ፕሮፌሶር ኣፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ሚኒልክን በአንድ በኩል ሲያዩዋቸውና ሲገልጧቸው፡ እነ ታጋይ ዶ/ር ኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ ደግሞ ሰነድ አጣቅሰው፡ ምኒልክን በሌላ በኩል ተመልክተዋቸዋል። የጽሑፉ ዓላማ “ኪዳን፡ ቃል ኪዳን፡ ውል፡ ስምምነት” ቅዱስ መሆን ኣለበት፡ አለበለዚያ ኣንድን የህዝብ ክፍል ወይ ኣንድን ህዝብ ወይም ኣንድን አካል ለመደፍጠጥ የሚደረግ “ኪዳን፡ ቃልኪዳን፡ ውል፡ ስምምነት” ርካሽ ነው ለማለት ይመስላል። ለምሳሌ፡ ኤርትራን ለማጥቃት “ሰንዓ-ፎረም” የተባለ ቅዱስ ያልሆነ ኪዳን በቅርብ ግዜ ነበር፡ . . . አሁንም ተመሳሳይ ቅዱስ ያልሆነ ኪዳን በአካባቢያችንና በቀጠናችን ካለ ለማስተዋል ይበጀናል። . . . ኣንድን ብሄር ኣማራ ሊሆን ይችላል፡ ትግሬም ሊሆን ይችላል፡ ኦሮሞም ሊሆን ይችላል ወዘተም ሊሆን ይችላል ለማጥቃት የሚደረግ የቦለቲካ ፓርቲዎች ሆነ የሃገራት ርካሽ-ኪዳን ኣለ ወይስ የለም? ግለሰቦችን፡ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ እንዳሉት አርበኞችን ወይም ፋኖዎችን ለማጥቃት የተደገሰና የተከወነ የቦለቲካ ፓርቲዎች ሆነ የ ሃገራት ቅዱስ ያልሆነ ኪዳን ኣለ ወይስ የለም? ለማጤን ይጠቅመናል። ወዘተ . . .

ይህንና መሰል ጽሑፎችን ማንበብም፡ አንድን አካል ሌሎች እንዴት እንደሚመለከቱት በመገንዘብ፡ ወደፊት ለሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ውይይት፡ የኔ ብቻ ነው ትክክለኛው ኣመለካከት ከማለት ይልቅ፡ ሌሎችስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? በማለት ይዘቱን ኣብጠርጥሮ በመመዘን፡ በኅሊና በመመራት ሚዛናዊ ግንዛቤን በማጉልበት፡ “ቅዱስ ኪዳን”ን በማበራከት “ቅዱስ ያልሆኑ ኪዳኖችን”ም ለማስተዋል ለመንቀፍም ጭምር በር ይከፍታል ብለን እናስባለን፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
:mrgreen:
Abere wrote:
20 Oct 2022, 10:41
ወደ አማርኛ ብትተረጉምልን ምን እንደተጻፈ፥ ከየት መረጃው እንደተጠናቀረ፤ ለምን እንደተጻፈ እውነት ወይም ሃሰት ስለመሆኑ አግቦ ለመስጠት ለብዙሃኑ አንባብያን ይጠቅም ነበር።
Meleket wrote:
20 Oct 2022, 10:16
ኪዳናት ምንሊክን ጣልያንን ኣብ ምጭፍላቕ ህዝቢ አርትራ (ሰነድ 1897 – 1907) ብኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

ታሪኽ ኤርትራውያን ሓርበኛታት፦
* ደግያት ማሕራይ ኣባሰላማ
* ደግያት ኣቡበከር
* ዓሊ ኑሪ . . .

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 21 Oct 2022, 10:09

መቅድም
ተመስገን . . . ! ዛሬ ከምንሊክ ጋር ባደረገነው ውይይት፡ የተነጋገርንባቸውን ጉዳዮች ሁሉ በስምምነት ፈጽመናቸዋል። . . . የደንከል (አፋር) በኩል ድንበር፡ ካርታ ላይ እንዲሰፍርና እንዲረጋገጥ ተስማምተናል። የንግድ ውሎችንም በተመለከተ፡ በኛ በኩል የቀረበው ንድፈ ሃሳብ ተቀባይነትን ኣግኝቷል። . . . ምኒልክ ጤንነቴን በተመለከተም ስለ ደህንነቴ ጠይቆኛል። ትግሬዎች ክፉዎች ናቸው። . . . የኛን ጓደኝነት ለማበላሸት፡ የሆነ ዓይነት ሴራ እንዳይፈጽሙ እጠረጥራለሁ በማለት ስጋቱን ነገረኝ። . . . የዓጋሜ ኣውራጃን በተመለከተም፡ “ደስታ የተባለውን ሹም ከናንተ ጋር ስለማይግባባ፡ ከዚያ ስፍራ አስንቸዋለው ወይ ኣስወግጀዋለው።

“የዓጋሜ አውራጃን ለገረስላሰ የተባለው ሹሜ ሰጥቸዋለው (አርግቸለታለሁ)። ይሄን ያደረኩት እኛና እናንተ በሰላም እንኖር ዘንድ ነው። የዓሰብ ወደብንም እንከፍትለት ዘንድ በምስጢር ጠይቆኛል። “እኛ ወደ ቀይ ባህር ዳርቻ ብንደርስ፡ ምን መጥፎ ነገር እንዳናደርጋችሁ ሰግታችሁ ነው? በማለትም ጠየቀኝ። እኔም ደህና እጠይቅልሃለሁ ስለው፡ እርስዎ የተከበሩ ትልቅ ሰው ስለሆኑ እባክዎን ይህን ጕዳይ እንደምንም ብለው አሳኩልኝ በማለት ጠየቀኝ።

ምኒልክ ሲሰናበተኝም፡ ከአውሮፓውያን መካከል ዋና ጓደኞቹና ኣጋሮቹ እኛ ጣልያኖች እንደሆንን እያሳሰበኝ፡ ከኛ ከጣልያኖች ትልቅ ቁምነገር እንደሚጠብቅ . . . ገለጸልኝ። (የማርቲኒ ዲያሪ፡ 1906፡ ገጽ 492,493)።

ይህ ቃላት፡ ከ1897 እስከ 1907 ኤርትራን ያስተዳደረው የኢጣሊያዊ ፈርዲናንዶ ማርቲኒ፡ ምንሊክን በጎበኘበት ወቅት ማለትም በ19.7.1906 በዝነኛው ዲያሪው (Diario Eritieo) የከተበው ጽሑፍ ነው።

ከዚህ ጽሑፍ መጀመርያ የሚከሰትልህ ቁምነገር፡ ምኒልክ በጣልያኖች ፊት ያሳዬው መቅለስለቅና ቅጥ ያጣ መሽኮርመምን ነው። በመሰረቱ ምንሊክን ጣልያኖች ስለፈጠሩት፡ አፍሪካ ውስጥ የመጀመርያው አጋራቸውና ጓዳቸው ነበር።

ይህን ሃቅ የሚመሰክር ስፍርቁጥር ዬሌለው ሰነድ አለ። የህዝባችን ወግም ጭምር ይህንን ታሪካዊ ሓቅ የሚያደምቅ ነው። ምኒልክ ጣልያንን ይዞ የዛሬዋን ኢትዮጵያ፤ ጣልያንም ምንሊክን ይዞ የኤርትራን ህዝብ ጨፍልቆ ኤርትራን ገዝቷል። ይህም ማለት የአውሮፓ አጼያዊ ሃይልና ኋላ ቀሩ የአፍሪካውያን ጭካኔያዊ የመስፍንነት አገዛዝ፥ ዕጹብ ድንቅ በሆነ ‘ኪዳን’ ተጣምረውና ተዋህደው ተገኙ!

በዚህ በምሥራቅ ኣፍሪካው ቀጠናችን፡ አንድ ሐበሻዊ ተብሎ የሚታወቅ ስልጣኔ ነበር። ሓበሻዊ ስልጣኔ ሲባል፡ በቀይባህር ምዕራባዊ ዳርቻ፡ እስከ የኤርትራ ደጋማ ክፍሎች ሲንሰራፋ ቆይቶ፡ ኣመሻሹ ላይ፡ ማእከሉን ኣኽሱም ላይ አድርጎ የነበረ ስልጣኔ ነው።

ኣኽሱም ከስዋኪን እስከ ዘይላ፡ ከአትባራ እስከ የተከዜ መነሻ ድረስ ተጽእኖውን ዘርግቶና አንሰራፎቶ የነበረበት ግዜም ነው። ተመሳሳይ የጥንታዊ ባርነት ስልጣኔዎች፡ በየራሳቸው ልዩ ታሪካዊ ምክንያት እንደከሰሙት ሁሉ፡ የኣኽሱም ስልጣኔም፡ በደቡብ ህዝቦችና አሁን አርትራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ጐልብተው በነበሩት የበጃ ህዝቦች መካከል ተቀርቅሮ፡ ተፈረካክሶ ከሰመ። ሓበሻዊቷ ኣክሱም ተጽእኖዋንና ባህሏን ኣንሰራፍታበት የነበረው በአካባቢዋ የሚገኙ ቦታዎች በሙሉ፡ የሓበሻ ምድር ማለትም “አቢሲንያ” በመባልም እስከ አሁን ድረስ ሳይቀርም ይጠራሉ።

በአቢሲንያ የተለያዩ ክፍሎች፡ ሓበሾች የተባሉ የተለያዩ ስርወመንግስቶች ወይ መንግስቶች እየታዩ ከሰሙ። ከነዚህም ዋንኞቹ
በሸዋ
በላስታና
በበጌምድር . . . ወዘተ ማእከላቸውን ያደረጉት ናቸው። የሓበሾች ምድርም ቡግ እልም በማለት ታዪተው ከከሰሙት ትንንሽ ጨካኝ መሳፍንቶች፡ ወደ ቀጣዩ የጭካኔ ዝቕጠት ተሸጋገረች።

በመጨረሻም ከሚካኤል ስሑል በመጀመር በውቤ በተገባደደው የዘመነ መሳፍንት፡ አንድ “አበሻን አንድ አደርጋለሁ፡ አንድ ስጋ ኣብልቸ፡ በአንድ ሃይማኖት ስርም አደርጋታለሁ” እያለ የሚፎክረው፡ ቴድሮስ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ጨካኝ መስፍን ተከሰተ። ቴድሮስም “ክርስትያን ሁኑ! ክርስትያን ያረደውን ብሉ!” እያለ፡ በእስልምና ያምን የነበረውን የህዝብ ክፍል ከመደምሰስ ኣልፎ ሌላ ደረጃ ላይ ሳይደርስ፡ እሱም የጭካኔውን ካባ እንደተከናነበ ተንደባሎ ከሰመ።

ከቴዎድሮስ በኋላ የተከሰተው የሓበሻ መስፍን ዮሃንስ በመባል የሚታወቀው ነው። የዩሃንስ ማእከሉ ትግራይ ነበረች። ዮሃንስ በተለዪ የኤርትራን ደጋማ ክፍሎች አሰቃቂ በሆነው ወረራና ዝርፊያው ኣሰቃየ። በመሆኑም ኣብዛኞቹ የኤርትራ መሳፍንት ዮሃንስን ለመመከት ዱርቤቴ በማለት ወደ ትግል ሜዳና በረሃ ተመሙ።

በዚያ ወቅት፡ ጣልያን መጀመሪያ በዓሰብ በኋላም በምጽዋ በኩል ብቅ ኣሉ። ዮሃንስም ከጣልያን ጋር የነበረውን ውስጣዊ ስምምነት በተግባር ለመፈጸም ፋታ ሳያገኝ፡ መተማ ላይ ድርቡሽ ራሱን ቆርጠው ወሰዷት። በዚህ መልኩም ጨካኙ የትግራይ ኣገዛዝም ከሰመ።

ዳግማዊ ምንሊክ በሚል የንግስና ስምም፡ ኣንድ ጨካኝ ሓበሻዊ ኣገዛዝ በሸዋ በኩል ተከሰተ። በመሰረቱ ምንሊክ፡ ምጽዋ ውስጥ ማእከላዊ ቦታቸውን አድርገው አርትራን ይገዙ በነበሩት ጣልያኖች ተፈጥሮ፡ በጣልያኖች ድጋፍ አገዛዙን ለማጽናት የቻለ ሰው ነበር። በጣልያኖች ብቻ ታግዞም፡ እንደተባለው አንዲት ኢትዮጵያ የምትባለውን አንዲት ሓበሻዊት መንግስትን መሰረተ።

ምንሊክ ኤርትራውያንን እየጨፈለቀላቸው፡ ጣልያንም ትግራይን እየጨፈለቁለት፡ በግዜው ባደረጉት ውልና ኪዳንም፡ የጣልያኗ ኤርትራና የምንሊኳ ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ጥለው በየፊያቸው ተስፋፍተው ተንዥረገጉ።

ይህን የምኒልክና የጣልያን የሴራ ጉድኝነትና ሽርክነትን በተመለከተ፡ ኣህያ ተጭናም በማትችለው በርካታ ሰነድና ማስረጃ የተረጋገጠ ነው።


በመሆኑም ይህ ከፈርዲናንዶ ማርቲኒ የ10 ዓመታት የስራ ዘመን ማስረጃ፡ ዲያርዮ አሪትረዩ ኤርትራዊ ዕለታዊ ፍጻሜ በሚል፡ በ4 ቅጾች ማለትም በ2616 ገጾች በተዋቀረው ታሪካዊ ሰነድ ውስጥ ቁልጭ ብሎ የተገለጸው ማስረጃ፡ እጅግ አስደማሚና ጉድ የሚያሰኝ ነገሮችን ያስተምረናል። በዚህ የ19300 ዝርዝር ዕለታዊ ፍጻሜዎች ማስረጃ ውስጥም፦

- የኤርትራ ህዝብን ኣልምበረከክም ባይነትና ቀጣይ ተቃውሞን እንዲሁም

- የምንሊካዊት ኢትዮጵያንና የጣልያንን ጽኑ ኪዳን በማያወላዳ ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ በማስረጃ ያሳየናል።


በተመሳሳይ መልኩም፡ ከምኒልክ ጀምሮ፡ ሁሉም ራሶቹ፡ ደጀዝማቾቹ ወዘተ በየግላቸው ሳይቀር፡ ኤርትራን ይገዛ ከነበረው ከማርቲን ጋር ጓደኛ ለመሆን ሲጥሩና ሲፈጉ፡ እያንዳንዳቸውም በጣልያን ይወደዱ ዘንድ፡ አንዳንድ ማባበያ ስጦታም ይሰጣቸው ዘንድ ሲፋለጡና ሲጥሩ ይታያሉ። አብዛኞቹ የምኒልክ መኳንንት በስውር የጣልያን ስርኣት ፎርማቶሪ (ሰላዪ) ሆነው ሲሰሩም እንታዘባለን። ከመንግስታቸው አንጻር ይሁን ከኤርትራ ኣንጻር፡ ያገኙትን የየዕለቱን ክቡር ማስረጃ ለጣልያን መንግስት ሲለግሱ በማዬት በተግባራቸውም እናፍራለን።

ቀጥለን እንደ አብነት የምገልጸው የኤርትራውያን አርበኞች ተቃውሞም፡ እላዪ የገለጽነውን የግዜውን ፖለቲካዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ስናስገባ፡ ለኤርትራውያን አርበኞች ምን ያህል ከባድና ብርቱ ሁኔታ እንደነበረ ለመረዳት ይቻላል።

በቀጣዩ ትረካ ደራሲው ያቀረቡትን የ“መግቢያ” ሃሳብ እንኮመኩማለን።
ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Abere
Senior Member
Posts: 11097
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Abere » 21 Oct 2022, 11:49

ወንድም መለከት፥

በቅድምያ ጥያቄየን ተቀብለህ ጊዜህን በመሰዋት ጽሁፉን ወደ አማርኛ በመተርጎምህ ከልብ አመሰግናልሁ። ብዙ አንባብያን ስለጽሁፉ ከሚያውቁት ይሁን ከሚያነቡት ካላቸው መረጃ ጋር እያነጻጸሩ እንድ ፈትሹት እና እንድመረምሩት ይረዳል። በዐደባባይ የወጣ ነገር ወይ ጸሀይ የሞቀው ሀቅ ይሆናል ወይ በጸሀይ ጠውልጎ የሚቀር ቅጠል ይሆናል። ለዚህ ጽሁፍም ከማጀት ወደ አደባባይ ወጥቶ በተለይ ይህ ጽሁፍ ያልሰማውን እና የሚፈረጀውን ኢትዮጵያዊያን እንድመረምረው ያደርጋል። ልብ በል! የተጻፈ ሁሉ እውነት የመሰከረ ሁሉ ምስክር አይሆንም። ስለዚህ ሊፈተሽ ማድረግህ መልካም ነው። ለዐደባባይ መቅረብ እራሱ አንድ እርምጃ ነው። ይህን ካልኩ ዘንዳ በቀጣይ ጊዜ የእራሴን አተያይ እሰጣለሁ። እኔ የእምዬ ምኒልክ አድናቂ ነኝ። እስከ አሁን ኢትዮጵያ ከአስተዳደሯት 225 ነገስታት በታሪክ እንደ አጼ ምኒልክ ያለ መሪ አላገኘችም። ወደ ስልጣኔ እና ብርሃናማ ዘመን እንድት ገባ ፈርቀዳጅ ናቸው። የምናወራው ስለ ሰው ልጅ እንጅ ስለ መልዐክ ስላልሆነ ስለ እርሳቸው የተጽፈ ሳካ ካለም አንብቦ ፍርድ መስጠት አግባብ ነው። ትልቁ ጭብጥ አጼ ምኒልክ ይኖሩበት የነበረው ዘመን እና በእርሳቸው አቅም ስንት መስራት ይችላሉ ነው? በጽሁፉ ምን አዲስ ነገር በሳይንሳዊ ማስረጃ ለአንባብያን ቀረበ እንድሁም ምን አይነት ተአማኒ ዋቢ ማስረጃ ተጣቅሰዋል የሚሉት ታሳቢ እንድሆኑ የግድ ይላል።

በድጋሜ ከልብ አመሰግናለሁ!

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 22 Oct 2022, 04:48

ወንድም Abere ስለ መልካምና የሰለጠነ እዪታህ ከልብ አመስግነንሃል። ወደ ትረካው ስንቀጥል . . ።

መግቢያ

የ19ኛውን ክፍለዘመን ወደ ኋላ ተመልሰን በጥሞናኣ በአንክሮ ስንመለከተው፡ በሁሉም ኣቅጣጫ የሚገኙት የኤርትራ ሃገራችን ዱር ገደልና ሸንተረሮች፡ የጣልያንን ኣገዛዝ በሚቃወሙ፡ ግን ደግሞ በቅጡ ባልተደራጁ የታጠቁ ኃይሎች ተሞልቶ ነበር። እነኚህ ኣብዛኞቹ ኤርትራውያን ታጣቂዎችም ከትግራይና ከአማራ በኩል የሚመጡትን ወራሪ ኃይሎች ለመመከት ይችሉ ዘንድ በጣልያን ኃይሎች የታጠቁ ኣርበኞች ነበሩ።

የኋላ ኋላ ግን ጣልያኖችንና የጣልያን ደጋፊዎችን እንዲሁም ወታደራዊ ካምፖቸው በየተመቻቸው አጋጣሚ ያጠቁ ነበር።

ይህ ከግዜ ወደ ግዜ ከጣልያን ኣገዛዝ ኣንጻር እየተቀጣጠለ የሄደው የእምቢታና የአልገዛም ባዪነት መንፈስና እንቅስቃሴም፡ ከእውቁ የደጃዝማች ባህታ የአርበኝነት ትግል በኋላ፡ ከግዜ ወደ ግዜ እየተፋፋመና እዬተጋጋለ ሄደ። በተለዪም የሳሆ ህዝብ ከጣልያን አንጻር ያሳየው የእምቢታና የአልገዛም ባዪነት የተቃውሞ ትግል ለአስራ ኣምስት ዓመታት ሊቀጥል ቻለ።

ይህ የኤርትራ ህዝብ የእምቢታ መንፈስና ወደር ዬለሽ የአልገዛም ባዪነት የነጻነት ትግል፡ ጣልያንና ምንሊክ ተመሳጥረው በአፍሪካው ቀንድ ለመስፋፋት ያደርጉት ለነበረው ኣደገኛ ዓላማ እንቅፋት ነበር። በመሆኑም የኤርትራ ህዝብ በምኒልክና በጣልያን እንዲጨፈለቅ፡ ምኒልክ ባያግዝና ባይተባበር ኖሮ፡ ጣልያኖችም የትግራይ ህዝብን በመጨፍለቅ ባልተባበሩት ነበር። ስለሆነም የጣልያንና የምኒልክ ኃይሎች ግዛቶቻቸውን ለማስፋትና ለማጽናት ይችሉ ዘንድ አንድ እኩይ-ኪዳን መዋዋላቸው ባህርያዊና የግድ ሆነ። ይህን በመሰለ ሁኔታም፡ የገዢው የጣልያን ኃይል ትብብር ባይታከልበት ኖሮ ሊደፈጠጥና ሊከስም የማይችል የነበረው የትግራይ አገዛዝ ተጨፍልቆ ከሰመ። በተመሳሳይ መልኩም የኢትዮጵያዋ የምኒልክ ኃይል ባይተባበር ኖሮ፡ ሊገዛ የማይችል የነበረው የኤርትራ ህዝብም ተጨፈለቀ ተገዛም።

በዚህ ጽሑፍ ቀጣይ ምዕራፎች ከምንተርከው የኤርትራውያን እምቢታና ጀግንነት ሌላ በማያዳግም ሁኔታ የምንማረው እውነት ካለ ይህ የጣልያንና የምኒልክን እኩይ ኪዳንን ነው።

በቀጣዩ ክፍል "ምዕራፍ 1፡- አጼ ምንሊክ የጣልያን ስሪት" የሚለውን ክፍል እንሄድበታለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 24 Oct 2022, 07:18

ምዕራፍ 1 - ኣጼ ምንሊክ - የጣልያን ስሪት

በድክሪስቶፎሪስ ይመሩ የነበሩት የጣልያን ወታደሮች፡ ተድዓሊ (ዶግዓሊ) ላይ በአጼ ዮሃንስ ሃይሎች ሲደመሰሱ፡ ጣልያኖች በአጼ ዮሃንስ ላይ ብርቱ ቂም ቋጠሩ። አጼ ዮሃንስንም በምን ዘዴ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ሊያጠፉ እንደሚችሉ የተለያዩ መንገዶችን መዘየድ ተያያዙት። ይህ ኣጼ ዮሃንስን የመገርሰሻ መላም፡ በራሱግዜ በሸዋ በኩል አለሁ እያለ ከተፍ አላቸው።

አጼ ዮሃንስን “ እሽ . . . ከጐንዎት ነኝ . . .” እያለ፡ የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግ፡ በተንኰል ላይ ተንኰል በመሸረብ ይጣጣር የነበረው የሸዋው ራስ(ንጉስ)፡ ከአውሮፓውያን ኃይሎች መካከል አለኝታና ድጋፍ ሊሆኑት የሚችሉ ኃይሎችን ይፈልግ ነበር። ምንሊክ ለጣልያኑ ንጉስ ኡምበርቶ በ10-3-1889 የሚከተለውን ይዘት ያለው መልእክትም ላከ፦

“ . . . ግርማዊነትዎ፡ ምጽዋ ላይ የሰፈሩትን ጀነራሎችዎን የትግሮቹን ወሬ እንዳይሰሙ ንገሯቸው። . . . ይልቁንስ ኣስመራን እንዲቆጣጠሩና፡ በብርቱ እንዲመሽጉባት፡ ትግሮቹንም ወደ ምጽዋ በኩል ዝር እንዳይሉ እንዲከለክሏቸው እዘዟቸው። . . . እግዚሄር ስልጣን ለኔ ሰጥቶኛል። . . . ጣልያን መሳርያ በመለገስ ከተባበረችኝ፡ ዶግዓሊ ላይ የፈሰሰውን የጣልያን ወታደሮችን ደም እኔ ራሴ እበቀለዋለው . . .” (ጉዊዶ ኮርተዘ፡ 1934፡ 66) አለ።

ለአውሮፓውያን ገዢዎች ማጐብደድንና መለማመጥን በተመለከተ፡ ኣጼ ዮሃንስም ቢሆን ዋናና ቀንደኛ ነው። ኣጼ ዮሃንስ የእንግሊዞች ስሪት መሆኑን ታሪክ የመሰከረው ሃቅ ነው። ዓይለት በተባለው አካባቢ መሽጎ ለነበረው የጣሊያን ጀነራል ዲ ሳማርሳኖ በ29.3.1888 የጻፋት መልእክት የሚከተለው ይዘት ነበራት፦

“የአምላክ ነብይ፡ የጽዮን ንጉስ፡ የኢትዮጵያ ንጉሰነገስት
ይድረስ ለተከበረው ጀነራል ዲ ሳማርሳኖ፡ የጣልያን ሰራዊት አዛዥ።

“እንደምን አለህ፡ በስም ብቻ ነው የማውቅህ። እኔና ሰራዊቴ በአምላክ ኃይልና ለጽዮን ባለን እምነት እንዲሁም በቅዱሳን ጸሎት ምክንያት ደህና ነን። ከዚህ በፊት ከጣልያን ንጉስ ኡምበርቶ ጋር የወዳጅነት መልእክቶችን እንጻጻፍ ነበር። ጓደኞችም ነበርን።

ብራንኪ ከተባለው አስተዳዳሪ ጋር፡ መተንፈሻ ይሆነን ዘንድ ለኛ ዓሰብን ስለ ምትከፍቱበት መንገድና ዘዴ ተነጋግረናል። ምኞቴ እኔና እናንተ በጋራ ሆነን የአረመኔ ህዝቦችን (ኤርትራ፡ ደቡብ ኢትዮጵያና ድርቡሽ ወዘተን) እንድንወጋ ነው። አንድ ኣካል ብንሆን ኖሮ በጋራ በገዛናቸው ነበር። ብራንኪን በጥሩ ሁኔታ ተቀብዬ፡ መዳልያም ሸልሜ አስተናግጀ ሸኝቸዋለው። ከሱ በኋላም ሲኞር ቢያንኪ ጐብኝቶናል። ከሱ ጋርም እንዲሁ ተነጋግረናል ተወያይተናልም። የወዳጅነት መልእክትና ለጣልያን መኮንኖች የሚሆን ሽልማትን ሰጥቸም ሸኘሁት።

“ . . . እግዚኣብሄር ኃይል ከሰጠኝ፡ እኔና እናንተ በየበኩላችን ድርቡሽን ተዋግተን ደምስሰን ግዛቶቻችንን ልናሰፋ እንችላለን። በርግጥ እንዲህ ማድረጉ ለሁላችን ይበጀናል። እኔና እናንተ ክርስትያን ወንድማማቾች ነን፡ ባለመስማማታችን ምክንያት የሌሎች መሳቂያ መሆን አይገባንም። ራስ አሉላ የፈጸመው ጉዳይ፡ እኔን ሳይማከር ነው። የተፈጸመው ተግባር የሰይጣን ተግባር ነው። ድሆችና ነጋዴዎች እንዲነግዱ ምጽዋን ክፈቱልን። መጋቢት 26 1880 ዓ.ም. ተጻፈ (ኮርተዘ፡ 1934፡66-6/)።

አጼ ዮሃንስ፡ ምድረ ባርያ ብሎ የሚጠራውን ጐጃምን በ9/10/88 በመውረር፡ ይህ ነው ተብሎ በቃላት ሊገለጽ የማይችል አረመኒያዊ ጭካኔና ዘረፋን ፈጸመ። በህጻናትና በሴቶች ላይ የተፈጸመው ዘረፋና አስነዋሪ የዘር ማጽዳት ዘመቻ፡ ለወሬ የሚሰቀጥጥ ነበር። በ15/1/1889 ምንሊክ ከጣልያን የመሳርያ እርዳታን ተቀበለ።

አጼ ዮሃንስም በ10/3/1889 መተማ ላይ በድርቡሽ ተገደለ። ምንሊክም አጼ ተብሎ በ22/3/1889 የሸዋን መንግስት መሰረተ። ከዓለም መንግስታት ወኪሎች መካከል፡ በምንሊክ የዘውድ መጫን የንግስነት በዓል ላይ የተገኘው አንዱና ብቸኛው ወኪል የጣልያን ወኪል ብቻ ነበር። ሌላ የተሳተፈ የውጭ መንግስት ወኪል አልነበረም። ለምን ቢባል ምክንያቱ ምንሊክን እየፈጠሩት የነበሩት ጣልያኖች ስለነበሩ ነው። በቀጣዩ የግንቦት ወርም ማለት በ2/5/1889፡ ምንሊክ ሙሉ ንግስነቱን ሳይቀር በጣልያን ግዛት ስር የሚያደርግ የውጫሌ ውልን ተፈራረመ። በቀጣዩ ሰኔ 2 ቀን 1889 ጣልያን ከረንን ተቆጣጠረች። በምንሊክ ምክር መሰረትም ነሐሴ 30 1889 ጣልያን አስመራን ተቆጣጥራ መሸገችባት።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 2 -የምንሊክና የጣልያን መወዳደስ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 25 Oct 2022, 05:32

ምዕራፍ 2 - -የምንሊክና የጣልያን መወዳደስ

የትግሬው አጼ ዮሃንስ ሞት ለጣልያንና ለምንሊክ ትልቅ ድል ነበር። ምንሊክ ወደ መተማው ጦርነት ክተት ተብሎ እያለ፡ “እዬመጣሁ ነው” በማለት ነገር ግን በጦርነቱ አለመሳተፉ፡ ትግሬዎቹንም ከነ አጼያቸው ኣጋፍጦ መክዳቱ፡ ድሮውንም ያለመው ነገር ቢኖረው ነው። የትግራይ ሰራዊትም አጼውን ከስሮ ብቻ ሳይሆን ከመተማ ቀልቡን ተገፎ ነበር የተመለሰው።

ይህ ሁኔታ ለምኒልክና ለጣልያን እኔ ነኝ እንዳለ ፋሲካና ድል ያለ ፌሽታ በጥቅሉ ሰርግና ምላሽ ነበር። ጣልያንና ምንሊክ የትግራይን ንግስና ለመጨፍለቅ አንድ ዓይነት ኣቋምና ሚዛን ስለነበራቸው፡ በጋራ ጥቅም ምክንያት ይበልጡኑ ተሳሰሩ። አስመራን እንደተቆጣጠረ የጣልያኑ ጀነራል ኦርሮ በጽሑፉ እንዲህ ነበር ያለው፦

ማእከላዊ ቦታዬን ከምጽዋ ወደ አስመራ የቀየርኩት፡ እኒያ ጠላቶቻችንና የምንሊክ ጠላቶች የሆኑትን (ኤርትራና ትግራይ)ን ባስቸኳይና በተቻለ ሁኔታ መፈናፈኛ ለማሳጣት እንዲያመች ብዬ ነው” . . . የሚል ይገኝበታል (ኮርተዘ ገጽ 115)። እኒያ ምናልባት ኣለን ኣለን የሚሉትን ትግራዮችንም ራሳቸውን እንዳያቀኑ ወኔያቸውን በመስለብ፡ የጣልያን ወዳጅ ለሆነው ለምኒልክ ይምበረከኩ ዘንድ ለማድረግ ጀነራል ኦርሮ፡ ዓድዋን በድንገት በመውረር በ27.8.1890 ተቆጣጠራት። የትግሮች ወኔ መሰለብና መርበትበት እንዲሁም የሸዋውን ምንሊክ ወኔ ካረጋገጠ በኋላም፡ የጣልያኑ ጀነራል ኦርሮ ዓድዋን ለቆ ወደ አስመራው ተመለሰ። በዚህም ጣልያንና ምንሊክ በመተባበር እጅጉኑ ፈነጠዙ።


ይህ ብቻም ኣልነበረም። ጣልያን እስከ ዛሬ ድረስ “ምንሊክ” ተብሎ የሚታወቀውን፡ የንጉስ ምንሊክን ስእል የታተመበት ጣሳ፡ ኤርትራና ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት አሰራጩ። ይህ ኣሁን ምንም ፋይዳ ዬሌለው የሚመስለው ጉዳይ ጣልያን ምንሊክን ለማሞኘት የተጠቀመበት ዘዴ በመሆኑ፡ በግዜው ትልቅ ትርጉም ነበረው። ምንሊክም በበኩሉ በ24.3.1891 ፣ በ15.4.1891 ፣ እንዲሁም በ5.5.1894 በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት፡ የጣልያኖችን የአፍሪካው ቀንድ ገዥነታቸውን በማያወላዳ መልኩ ተቀበለ። (ማርቲኒ፡ ዲያርዮ 1ኛ ቅጽ ገጽ 170) እንዲህም የሚል ውልም ተዋዋለ፦

“ግርማዊነታቸው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት፡ ከሌሎች ኃይሎች ወይ መንግስታት ጋር ለሚኖራቸው ማንኛውም ዓይነት ጉዳይ፡ በኢጣልያው ግርማዊ ንጉስ “ረ” ይከናወን ዘንድ ፈቅደዋል” የሚል የውጫሌ ውል ዓንቀጽ 17ን ተዋዋለ፡ በዚህም በእጁ ስር እንድትሆን ያስቻሉትን ኢትዮጵያን ሳይቀር በጣልያን መንግስት ጥላ ስር እንድትሆን ምንሊክ ፈረመ።


በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 3 - የደጃዝማች ገረስላሰ አዋጆች” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Right
Member
Posts: 2819
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Right » 25 Oct 2022, 06:25

No such thing called Eritrea before the Italians occupation of the region.

Inventions or fabrication based on the Italians narrative.

Return the Afar land to the Afars. The only legit state in the region is the Republic of Afar.

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 26 Oct 2022, 03:04

ምዕራፍ 3 - የደጃዝማች ገረስላሰ አዋጆች

የምንሊክ ቡችላ የነበረው ትግሬው ደጃዝማች ገረስላሰ በ1904 በተደጋጋሚ ያስለፈፈው አዋጅ፡ የጣልያን መንግስትንና የኢትዮጵያው አጼ ምንልኪን ወዳጅነት ይበልጥ አጉልቶ ያሳያል። እንዲህ የሚሉ ቃላትም ይገኝበታል፦

“ኣዋጅ ኣዋጅ!! በጣልያኑ ንጉስ ረ ትእዛዝ መሰረት፡ እኔ ከክቡር ካቫለር ፈርዲናንዶ ማርቲኒ ጋር፡ ሁለገብና ይፋዊ ስምምነትን ኣድርጌያለሁ። ያለምንም ማወላዳትና ውልውል ሕግ እንዲከበር ለማድረግም ወስነናል።”

ስምምነታቸውም ማንኛውም ዓይነት ተቃውሞን፡ በተለይም በኤርትራውያን ኣማካኝነት የጣልያን ኣገዛዝን የሚቃወም ማንኛውንም ዓይነት እንቅስቃሴና ተቃውሞን፡ በጋራ ሆነው ለመደፍጠጥ የተወሰነ ውሳኔ እንጂ፡ ሌላ ትርጉም እንደሌለው የሚከተሉት የአዋጁ ክፍሎች ቁልጭ አድርገው ይመሰክራሉ።
ኣዋጁ እንዲህ ነበር የሚለው፦

“ስምምነታን እንደሚከተለው ነው።”

“ማንኛውም ሰው፡ መንግሥቱን ጣልያንን በድሎ፡ ወይም ሕግ ጥሶ፡ ከቅጣት ለማምለጥ፡ ድንበር ተሻግሮ ወደ ምድራችን ወይ ወደ ሃገራችን ከገባ፡ ታስሮና ተጠፍሮ ለኤርትራው የጣልያን መንግስት ይረከባል።”

የየቀየው አስተዳዳሪዎችና መሪዎችም እንዲሁም ጭቃ ሹሞች በሙሉ ይጠንቀቁ። እኒህ የተጠቀሱትን ሰዎች እያሰሩ ካላስረከቡ፡ እጅግ ብርቱ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

“የትግራይ ኗሪዎች በትግራይ የምንሊክ ተወካይ የሆንኩትን እኔን በድለው ወደ ኤርትራ ከሄዱ፡ ተቀፍድደው ይመለሷታል፡

- ይህ ኣዋጅ በሁለቱ የጣልያንና የኢትዮጵያ መንግስታት ታውጇል

- የተከበራችሁ የጣልያንና የኢትዮጵያ ህዝቦች፡ የሁለቱ ሃገራት ህዝቦች ፍጹም በሆነ ወዳጅነት በሰላም መኖር እንዳለባቸው የአምላክ ፍቃድ መሆኑን እወቁ

- ማንኛውም ነገር በፍትህ ኣልባት ያገኛል ወይም ይዳኛል። እምቢተኛም በሃገራችን ሆነ በኤርትራ የሚገባውን ቅጣት ይቀበላል።

- ይህን ኣዋጅ ያወጅንበት ምክንያት፡ ሁላችሁም ህግን እያከበራችሁ በሰላም እንድትኖሩ በማለም ነው። ይህን ኣዋጅ ያላከበረ ሁሉ ይቀጣል። ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆኗል እንደልባችሁ እረሱ ነግዱ!

- ይህን ኣዋጅ የካቲት 6 1904 ዓመተ ምሕረት በዓድዋ ከተማ ጽፊዋለሁ “(ማርቲኒ፡ ዲያርዮ 3ኛ ቅጽ፡ ገጽ 490)

ታድያ ከዚህ የላቀ ወይ ከዚህ የተሻለ በሁለት ተስፋፊ መንግስታት መካከል ምን ዓይነት ኪዳን ወይ ውል ሊኖር ይችላል? እርግጥ ነው ይህ ግዜ፡ የጣልያን መንግስትና ምንሊክ የተኩራሩበትና አንድነታቸውና ፍቅራቸው ጠርዝ ላይ የደረሰበት ግዜ ቢሆንም፡ በግል ይሁን በየፊናቸው፡ እንደ የጸዓዘጋው ደጃዝማች አበራ የመሳሰሉ በርካታ የኤርትራውያን የእምቢታና ኣልገዛም ባይነት እንቅስቃሴዎች የተደቆሱበት፡ የጣልያንና የምንሊክ ስርዓቶች ግን እርስበእርስ ያደርጉት ለነበረው መደጋገፍ እርስበእርስ ይመሳገኑበትና ይወዳደሱበት የነበረ ግዜ ነበር።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 4 - ምንሊክ ድንበር ለማመላከት በገንዘብ ሲዋዋል” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 27 Oct 2022, 02:05

ምዕራፍ 4 - ምንሊክ ድንበር ለማመላከት በገንዘብ ሲዋዋል

እስቲ አሁን እንዲህ ሃቁ ሲነገር፡ የዘመናችንን የአማሮቹን ጉራና ትርክት ማን ሊያምነው ይችላል? ያም ሆነ ይህ፡ ከአሁኖቹ ማለትም ከዘመናችን የአማራ ገዢዎች ይልቅ ከ 100 ዓመታት በፊት የነበረው፡ አልተማረም ተብሎ የሚታሰበው ምንሊክ ይበልጥ አስተዋይና ብልህ ነበር ለማለት ይቻላል። ምንሊክ ሆዬ፡ ኤርትራ ይቅርና ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገርም ብትሆን ካለ የውጭ መንግስታት ድጋፍ ሊያገኛት እንደማይችል ኣብጠርጥሮ ያውቅ ኖሯል። ስለሆነም ኤርትራን የግዛቴ አካል ነች በማለት ሰራዊቱን ወደ የኤርትራ በማስገባት መዳማትን አልሞከረም ኣልመረጠምም።

ለምኒልክ፡ ትግራይ ከተደፈጠጠችለት በቂው ነበር። የደንበሩን ጉዳይም ተደራድሮ፡ የሆነ ገንዘብ ካገኘበት፡ በቂው ነው።
ይህ ጉዳይ ለምንሊክ “የትኛው ብልህ ነው ያማከረህ?” የሚያስብል ትልቅ ትርፍ ነበረው። ምክንያቱም ምንም ከማይመለከትህ ጉዳይ ትርፍ እንደማግኘት ነው የሚቆጠረውና። እስቲ የሚከተለውን ተጨባጭ ማስረጃ እንመልከት፦

“ከአዲስ አበባ በ23/4/1900 ኣንድ የቴሌግራም መልእክት መጥቷል። ምንሊክ፡ ከመረብ - በለሳ- ሙና ደንበር ወዲህ ምንም ዓይነት ቦታን እንደማይሻ በማያዳግም ሁኔታ ገልጿል።

በምትኩ ግን 5,000,000 ፍራንክ ጠይቋል። ነገርየው ግን በጥብቅ ምስጢር እንዲያዝለትም ጠይቋል።
ይህን ቴሌግራም አንዲትም ቃል ሳልጨምርበት ወደ ሮማ እልከዋለው። ግን ሃሳቡን ይቀበሉት ይሆንን? ባለፈው በነሓሴ ወር እንኳ 6 ሚልዮን ፍራንክ ለመስጠት ተዘጋጅተው ነበር። ታድያ ኣሁን ምን ቆርጧቸው ነው የማይቀበሉት? ምስጢራዊ ውሉስ?

“ . . . እንደኔ እንደኔ፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ሳይውል ሳያድር መስማማት ያስፈልጋል። 5 ሚሊዮኑን ፍራንክም ከዚችው ግዛታችን ከኤርትራ ገቢ እኔው ራሴ አገኛለሁ” (ማርቲኒ ዲያርዮ 2ኛ ቅጽ፡ ገጽ 143-44)። ነገርየው “ገመል ሰርቆ አጉነብሶ” እንዲሉ ነው። ምንሊክ 5 ሚልየን ፍራንክ መቀበሉን እንደሆነ፡ በጣልያን ግዛት ወቅት የነበረ ማንኛውም ሰው የሚያውቀው የአደባባይ ምስጢር ነበር።


በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 5 - የኤርትራን ህዝብ በጋራ የመጨፍጨፍ የጣልያንና የምንሊክ እኩይ እቅድ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 28 Oct 2022, 02:12

ምዕራፍ 5 - የኤርትራን ህዝብ በጋራ የመጨፍጨፍ የጣልያንና የምንሊክ እኩይ እቅድ

በተለዪ ያለንበት ዘመን የፕሮፓጋንዳዊ ኣቀራረብ ያለውን ትርክት ለሚያውቅ ሰው፡ የጣልያንና የምንሊክን የዓድዋው ጦርነት በተመለከተ፡ እዚህ ያቀረብነው ታሪክ ግር ሊያስብለው ይችላል። በኤርትራ በነበረው የጣልያን ሰራዊትና በምንሊክ ሰራዊት መካከል በ29/2/1896 የተካሄደው፡ ያልተሳካው የጣልያን የዓድዋው ጦርነት፡ ዋንኛ ምክንያቱ ኪሳራቸውንና ትርፋቸውን በቅጡ ሊገነዘቡ የማይችሉት የጣልያን ሰራዊት መሪዎች ግዚያዊ ስህተት እንጂ፡ በኢትዮጵያና በኢጣልያ መካከል ስር የሰደደ ጥላቻና የጦርነት ትልም ስለነበረ ኣይደለም።

የዓድዋው ጦርነት፡ ለግዜውም ቢሆን የጣልያንና የምንሊክን ወዳጅነት ትንሽ ጥላሸት የቀባ፤ ነገር ግን ታሪካቸው ብቅጡ ገና ያልተነገረላቸው ኤርትራውያን ምርኮኞችን፡ በታቦትና በመስቀል የታጀቡ ካህናትና አቡናት ፊት፡ አካላታቸውን በመቁረጥ ቁጣውን ያበረደ፡ ከመቅጽበትም የታረመ፡ የጣልያኖች ግዜያዊ ስህተት ነው የነበረው።


በዓድዋው ጦርነት፡ በገዢዎቹ በጣልያኖች እየታፈሱ በግድ ወደ ጦርነት እንዲገቡ የተደረጉ ኤርትራውያን የጦር ምርኮኞች እንጂ፡ በቤተክህነትና በታቦት ፊት ተከቦ አካላቱ በመጥረቢያ የተቆረጠ ኢጣልያዊ ይሁን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ኣልነበረም። ይህ ግፍ በኤርትራውያኖች ላይ ብቻ ዬተበየነ ግፍ ነበር።



“አስቃቂው ድርጊት በተለያዩ ካምፖች ውስጥ ነው የተፈጸመው። በቁጥር 800 የሚሆኑ ኤርትራውያን፡ አብዛኞቹ በአንድ ስፍራ አካላታቸው እንዲቆረጥ ተደርጓል። በርካታዎቹ ኤርትራውያን የተማረኩት፡ በጦርነቱ መካከል የቆሰሉ ጓዶቻቸውን ለማዳን ሲጥሩ ነበር። ከ“ፍረሞና” ወደ “ዓሰም” በሚወስደው ቁልቁለት፡ የተቆራረጠ የኤርትራውያን እጅና እግር ተከምሮ ነበር። የተቆራረጠው የኤርትራውያን እጅና እግር ክምርም እቦታው ላይ ሳይነሳ ለረዢም ግዜ እንዲቆይ ተደርጓል። ምርኮኞቹ ስቃያቸውን ዋጥ አድርገው በትዕግስት ተቋቁመውታል። እንደሚባለውም ኡይ ብሎ የጮከ ኣንድም ምርኾኛ ኣልነበረም። አንዳንዶቹ በዚህ አስከፊ ሁኔታ በቀን ፀሃይና በሌሊት ብርድ ሲፈራረቅባቸው ተሰቃይተው ሞቱ። አንዳንዶቹም ወደ ኤርትራ ለመጓዝ እዬጣሩ መንገድ ላይ በድካምና በስቃይ ተዳክመው ሞቱ። 400 ገደማ የሚሆኑት ደግሞ ኤርትራ በመግባት ህክምና ሊያገኙ ቻሉ።” [Carlo Conti Rossini. Italia e Etiopia, dal trattato di Uccialli alla battaglia di Adua page 451]

ይህ ጉዳይ እስከ ዛሬ ድረስ ዓለምን ያስደመመ ጉዳይ ነው።


በዚህ በዓድዋው ጦርነትም፡ ምንሊክ አስቀድሞ የነበረውን እንዲሁም ለወደፊቱ ያሰበውን የጣልያን ወዳጅነቱን አላስረሳውም። ምንሊክ ሁሉንም የጣልያን ምርኮኞች በክብርና በሰብአዊነት ሲንከባከባቸው፡ በሽዎች የሚቆጠሩትን ኤርትራውያን ምርኮኞች ግን መግለጫ በማይገኝለት አረመኔነትና ጭካኔ አካላቸውን ቆራረጠው። በኤርትራና በኤርትራውያን ላይ የነበረውን ጥላቻም ፍጹም ሊደመሰስ የማይችለውን የጥላቻ ማህተሙን ኣሰፈረበት። አሁን ወደ ታሪካችን እንመለስ።


አጣልያንን ካርበደበደውና ካንቀጠቀጠው የደጃዝማች ባህታ እምቢታና አመጽ በኋላ፡ በስፋቱ ሆነ በጥንካሬው ጣልያንን ያሰጋው የአልገዛም ባዪነት እንቅስቃሴ፡ የጸዓዘጋው ደጃዝማች አበራ እምቢታ ነው። ይህ የደጃዝማች አበራ የእምቢታ እንቅስቃሴ ምንም እንኳ ጣልያኖችን ቢያሰጋቸውና ቢያናውጣቸውም፡ ይህኛው እንቅስቃሴም ለድል አልበቃም።

የጸዓዘጋው ደጃዝማች አበራ ከነ ተከታዮቹ ዋልታና ማገር ትሆነኛለች ወዳላት ወደ ትግራይ ተሻገረ። ምንሊክም ምንም እንኳ “ከሺ አማራ አንድ አበራ” በማለት የደጃዝማቹን ጀግንነት ለማድነቅ ቢገደድም፡ ደጃዝማቹ ከትግራይ በመነሳት ጣልያኖችን እንዳይወጋ አጥብቆ ከለከለው። ይህን ሃቅ የሚመለከተውን ይህን ሰነድ እስቲ እንመልከት፦

“ . . . የዓድዋ አስተዳዳሪው ደጃዝማች ገረስላሰና የሽሬው አስተዳዳሪ ደጃዝማች አብርሃ ታርቀዋል። ይህ ጉዳይ ለኛ መልካም ነገር ነው። ገረስላሰ ከማንኛውም ፍርሃት ነጻ ሆኖ፡ ለኛ እምቢ አንገዛም የሚሉትን ጠላቶቻችን እያደነ ድንበሩን ሁሉ ይቆጣጠርልናል ማለት ነው። የጸዓዘጋው አበራም ከትግራይ እንዲርቅ ተደርጓል፡ ተከታዮቹም ከሱ እንዲርቁ ስለተደረገ ቁጥራቸው ተመናምኗል” (ማርቲኒ ዲያርዮ 8-6-1902)

ከዚህ ጽሑፍ አንድ ወር በፊት ደግሞ ፈርዲናንዶ ማርቲኒ እንዲህ በማለት ከትቧል፦

“ኣባ ወልደገርግስ ባህልቢ የተባለ መነኩሴ ባለበት፡ በመጋቢት ወር መጨረሻ ንጉስ በተገኘበት አንድ ትልቅ የተስካር ዝክር ተደርጎ ነበር። ደጃዝማች አበራና ሌሎች ኤርትራውያን፡ “እኛ መሬታችንን በሚሸጡ፡ የዱር ዛፎቻችንን ቆርጠው በሚቸበችቡ፡ ለመቃብር ቦታ ሳይቀር ግብር የሚያስከፍሉ የባዕድ ኃይሎች እየገዙት ወዳለው ወደ ሃገራችን የማንመለስበት ምክንያት ምንድን ነው? ንጉሱ እርስዎ ከሆኑ ታድያ ሁሉንም ግዛትዎን የማያስተዳድሩት ለምንድን ነው? . . .”በማለት ስሞታቸውን አቀረቡ። ምንሊክም “እኔ ከነሱ [ከጣልያኖች] ጋር ታርቂያለው፡ ሰላምም አድርጊያለሁ። በዚ ላይ ደግሞ እነሱ ጎበዞች ናቸው” በማለት መለሱላቸው። ደጃዝማች አበራ በንጉሱ ሆነ በራሶቹ የሚታየው በመጥፎና በክፉ ሁኔታ ነው።” (ማርቲኒ ዲያርዮ 13.5.1902: 600) በማለት ፈርዲናንዶ ትዝብቱን አስፍሯል።

ይህ እላይ የተገለጸውን እውነታ እንደ መግቢያ ወስደን፡ እስቲ ወደ አንዳንድ ዝርዝር ኣብነቶች እንግባ። በዝርዝር ሊጠቀሱ የሚችሉ አብነቶች ስፍር ቁጥር ባይኖራቸው እንኳ፡ በዚህ ጽሑፍ

- የአባ ሰላማው ደጃዝማች ማሕራይ

- የሳሆ ተወላጁ አቡበከር እንዲሁም

- የሳሆ ተወላጁ ዓሊ ኑሪ

ላይ ትኩረት ሰጥተን ታሪካቸውን በጥቂቱም ቢሆን የምንመለከታቸው ኤርትራውያን አርበኞች ይሆናሉ።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 6 - የአባ ሰላማው - ደጃዝማች ማሕራይ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 29 Oct 2022, 03:04

ምዕራፍ 6 - የአባ ሰላማው - ደጃዝማች ማሕራይ

ደጃዝማች ማሕራይን በተመለከተ፦ አንድ ገበሬ የነበረ ወንድማቸው እንዲህ በማለት እየቆዘመ ሙሾ ደርድሮላቸው ነበር ይባላል፦

"ማሕራይ ሓወየ፡ ማሕራይ ሓወየ፡
ኣጥፊኦሙኻዶ ናብ ናዅራ ናብ ቀላየ፡
ሽመትካ እምበር ኮነት ኣደዳ ትግራየ፡
ሕነ ከይፈድየልካ ኰይን ዘባጥ ብዕራየ።"

ግርድፍ ትርጉሙ እንዲህ ማለት ነው

ማሕራይ ወንድምዓለም ማሕራይ ወንድሜ ሆይ፡
ናኩራ ደሴት ወስደው ኣስረው ኣጠፉህ ወይ?
ወረሷት ትግራዮች ስልጣን ሹመትህን
አልበቀል ነገር፡ ኣይ ገበሬ መሆን! እንደማለት ነው፦

“ማሕራየ ማሕራየ
ጨዲድዋ ከደ ንቐላየ” ተብሎም ተገጥሞላቸዋል ግርድፍ ትርጉሙ እንዲህ እንደማለት ነው፦

ማሕራይ ጀግናው ማሕራይ የወንድ ቁና፡
ባሕሩን ከፍሎ ሄደ ስሙ ነው ገናና።

ይህ ዘመን ተሻጋሪ ግጥምም፡ ደጃዝማች ማሕራይ በቀይባሕር በምትገኘው ከናዅራ የጣልያን የግዞት እስርቤት አምልጦ፡ ቀይባሕርንም በዋና ጣጥሶ ጣልያኖችን እንዳመለጠ የሚያበስር የህዝባችን ዘመን ተሻጋሪ ዜማም እስከ ዛሬ ድረስ ህያው ሆኖ ይታወሳል

የመጀመርያው የወንድማቸው የቁዘማ ሙሾ ላይ እንደምናስተውለው፡ “እምቢ ኣሻፈረኝ ኣልገዛም” ባለው በደጃዝማች ማሕራይ ቦታ በጣልያን ስር ለሆዳቸው ያደሩ የትግራይ ባንዶች የአከለጕዛይን ህዝብ ያሰቃዩ እንደነበር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ይህ ደግሞ በፍጹም የማይታበል ታሪካዊ ሓቅ ነው።

ከደጃዝማች ባህታ እምቢታና አልገዛም ባይነት በኋላ፡ ረዢም ግዜ በወሰደው አከለጕዛይን የማንበርከከ ዘመቻ፡ እንደ ደጃዝማች ፋንታ የተባሉ ባንዳ የትግራይ ሰዎች፡ በጣልያኖች ስር በመግባት፡ ያለ ርህራሄ ህዝቡን ጨፍልቀዋል። ደጃዝማች ፋንታ አስቀድሞ የራስ አሉላ ወታደር የነበረ ቅጥረኛ ሰው ነበር። የኋላ ኋላ ግን ለረዢም ግዜ የበለጠ ጥቅም በመስጠት ያዛልቁኛል ብሎ ወዳሰባቸው ወደ ጣልያኖች በመክዳት በነሱ ስር ተቀጠረ። ይህም ሆኖ ደጃዝማች ፋንታ ጣልያኖችን በሙሉ እምነት በማገልገል በኤርትራውያን ላይ ግፍ ቢፈጽምም፡ ኣመሻሹ ላይ በእስተእርጅናው ግዜ ግን ያለ አንዳች ጥሮታ ጣልያኖች እንዳገለገለ እቃ ወረወሩት።

እስቲ አሁን ወደ ቁምነገራችንና ዋና ታሪካችን እንመለስ። እስከ ዛሬ ድረስ በህዝባችን ልማድ ውስጥ ሲወርድ ሲዋረድ እንደሚተረከው፡ በናኵራ ደሴት “ሞት ይፍታህ” ተብለው ዘመናቸውን በሙሉ “ዓለም በቃችሁ ተብለው” በእስር እንዲማቅቁ የተፈረደባቸው በርካታ ኤርትራውያን፡ ከእለታት አንድ ቀን፡ በጥቂት የጣልያን ወታደሮች ትመራ የነበረችን አንዲት መርከብ ማርከው፡ ወታደሮቹንም ቀይባሕር ውስጥ አድፍቀው፡ ወደ የመኗ ዓደን ተሻገሩ። የዚች የተጠለፈች መርከብ መጨረሻ ምን እንደሆነ፡ ጣልያኖቹም የደረሱበት ምንም ዓይነት መረጃና ማስረጃ ሰነድ የለም፤ እዚህ ገባች ሳይባል ዱካዋ ጠፍቶ እንደወጣች ቀርታለች።

አባት ኣርበኞቹ ግን መሳርያዎቻቸውን በገዢዎቹ በጣልያኖች ላይ ለማቅናት ዞረው ተመልሰው በመምጣት ትግራይ ላይ ታዩ። ከነዚህ መካከል አንዱ በምንሊክ ትእዛዝ መሰረት ተይዞ ለጣልያኖች ተላልፎ ተሰጠ። ከንቲባ ሰንጋልም ይባላል። ጣልያን ከንቲባ ሰንጋልን ዓዲቐይሕ ውስጥ በመርዝ ገደሉት። የተቀሩት ሌሎች ግን ገዢ ጣልያኖችን ዕረፍትና እንቅልፍ ነሷቸው። በምኒልክና በትግራይ ራሶቹ ትብብር ጣልያኖች እነዚህ አርበኞችን ሊደፈጥጡ ቻሉ። ከነዚህ አርበኞች መካከል አንዱ ደጃዝማች ማሕራይ ነው። ታሪኩ እንዲህ ነው፦

“ደጃዝማች ማሕራይ በናኩራ ደሴት ታስሮ ነበር። የታሰረበት የራሱ ምክንያትም ነበረው” በማለት አስተዳዳሪው ፈርዲናንዶ ማርቲኒ ተብሰልስሏል ( ማርቲኒ፡ ዲያርዮ፡17-3-1900)

ማርቲን እንዲህ በማለት ያሳሰበበትና የተብሰለሰለበት ምክንያት፡ በትግራይ ደንበር በኩል የብብት ቁስል በመሆን እንቅልፍ ይነሳው የነበረው ደጃዝማች ማሕራይ ዳግም ታስሯል የሚል ወሬ እንደሰማ ነው። ነገር ግን ደጃዝማች ማሕራይ ታስሯል የሚል ወሬ ቢሰማም እንኳ፡ የደጃዝማች ማሕራይ ተግባር በትግራይና ኤርትራ ደንበር መካከል ሲቀጥል እንታዘባለን። ለምሳሌ፦

“በ23-3-1900. ባለፈው ወር መገባደጃ፡ አንድ ተድላ ጻዕዱ የተባለ ወታደራችንን [የጣልያን መሆኑ ነው]፡ አንዳንድ የታጠቁ አካላት ተኩስ ከፈቱበት። እሱም በበኩሉ የመከላከል ተኩስ ከፍቶ ተከላክሏል። ነገር ግን መጨረሻ ላይ ተድላ በጥይት ተመትቶ ቆስሏል። ጓዶቹ ተሸክመው እስከ ‘ዝባን ጕላ’ ቢያደርሱትም ህይወቱ ግን አልተረፈችም። ተኩስ የከፈቱበት አካላት፡ የደጃዝማች ማሕራይ ተከታዮች እንደሆኑ ታውቋል” (ማርቲኒ ዲያርዮ - ገጽ 101) በማለት ከጻፈ በኋላ፡ እንደሚከተለውም ያብራራል፦

“ገረንክኤል ዕቝባይ የተባለው ሰላያችን፡ ደጃዝማች ማሕራይን በዓድዋ ከተማ በዓይኑ በብሌኑ እንዳየው ነግሮኛል” (ማርቲኒ ዲያርዮ 29-3-1900)።

ጣልያኖች ኤርትራውያን እምቢተኞችን ለመደምሰስ ማንኛውንም ዓይነት ወራዳ ተግባር እንደሚጠቀሙ የሚያሳየውም፦

“አንድ ደጃዝማች ማሕራይን ከልቡ የሚጠላ፡ አሳላፊ ገበንየ የተባለ የትግራይ ሰው ‘ደጃዝማች ማሕራይን ብገድለው፡ አከለጉዛይ ውስጥ ሊያኖረኝ የሚችል ገንዘብ ትሰጡኛላችሁን?” በማለት ጠየቀኝ” (ዲያርዮ 9-4-1900) የሚል ጽሑፍ እንታዘባለን። አሰላፊ ገበንየ፡ እንደተባለው ደጃዝማች ማሕራይን ይግደል አይግደል፡ እንዲሁም ለምንስ ደጃዝማቹን ይገድላል ለሚለው ጥያቄ ምንም እንኳ መልስ ባይናገኝም፤ ደጀዝማቹ በአሳላፊ ገበንየ እንዳልተገደለ፡ ይልቁንም ኤርትራውያን እምቢተኛ አርበኞች ይበልጡኑ ከግዜ ወደ ግዜ እንደተበራከቱ ከሚከተለው መልእክት እንረዳለን፦

ራስ መኰንን ከሓውዜን እንዲህ የሚል መልእክት ልኳል፦ "እኔ ከአከለጉዛይ እከላከልልሃለሁ፡ አንተ ደግሞ ከትግራይ ሰዎች ተከላከልልኝ፡ በዚህም ሁለታችንም እንጠቃቀማለን"” (ማርቲኒ ከማሁ) የሚለው ሰነድ ከቀጣዩ ጋርም ይስማማል። በ20-4-1900 የተመዘገበው የማርቲኒ ዕለታዊ ዜና እንዲህ የሚል ይገኝበታል፦

“አንድ ሰላያችን እንዳለው፡-
- የዓሳውርታው ዓሊ ኑሪ
- ባሻ ንጉሰ
- እንዲሁም ሌሎች እምቢተኞች በራስ መኮንን አማካኝነት ታስረዋል። ደጃዝማች ማሕራይም ወደዚህ ግዛታችን በኩል ዝር እንዳይል ተከልክሏል።(ደሮሲ/ደርሶ)”
ከዚህ መረጃ ከሁለት ቀን በኋላም፡ ደጃዝማች ማሕራይ፡ የምንሊክ አገልጋይ በነበረው በራስ መኰንን እንደታሰረ ይታወቃል፦

“በወሩ በ22ኛው ቀን 11 ሰዓት፡ ሰገነይቲ ላይ የአኽራኑ ሹም ጓንጕል እንደገለጸው፡ ደጃዝማች ማሕራይ በራስ መኮንን ትእዛዝ ታስሯል። የታሰረበት ምክንያትም ለደጃዝማች ተድላ አባጎበን የጻፈው መልእክት ስለተደረሰበት ነው። - ደሮሶ/ደርሶ”። ከሶስት ቀናት በኋላም፦

“በ - 4-1900 ደጃዝማች ተስፋማርያም እንደገለጠው፡ ደጃዝማች ማሕራይና የልጅ ተድላ ወንድም ልጅ ገረመድህን የታሰሩበት ምክንያት በራስ መኰንን ትእዛዝ ነው። ልጅ ተድላ ግን ከአንድ ጀሌው ጋር ያለ አንዳች መሳርያ ወደ ኢጣልያዋ ኤርትራ ደንበር አቅጣጫ ሲጓዝ ታይቷል። - ሙላሳኒ።”

እንደኛ ጥቁር፡ እንደኛ አፍሪካዊ፡ እንደኛ የሓበሻ ልጅ ወደ ሆነው ወደ ምንሊክ ተጠግተን፡ ከትግራይ ደንበር በመነሳት ጠላታችንን ጣልያንን ልንወጋ እንችላለን ያሉ አባት አርበኞች፡ ያልገመቱት የቆዳ ቀለምና ጉርብትና አታለላቸው። አንድ ጐረቤትህ የሆነ አፍሪካዊ መንግስት፡ ከአንድ ባህር ተሻግሮ ከመጣ ዓመጸኛ መንግስት ጋር በመሻረክ፡ አንድ ጭቁን ጐረቤት አፍሪካዊ ህዝብን ሊያጠቃ ይችላል ብለው ባለመገመታቸው፡ በተግባር ከባድ ሰቆቃ ውስጥ በመግባት ገፈት ለመቅመስ ተገደዱ። ከናኩራ አምልጠው ወደ የመን ዓደን በመርከብ በሄዱበት ተሰደው፡ ሰርተው መኖር ይችሉ ነበር። ነገር ግን የሃገር ፍቅር ስሜታቸው ይህን ለማድረግ አልፈቀደላቸው። ኤርትራዊ ወኔያቸው እንደወጡ ከመቅረት ይልቅ ተመልሰው ጣልያንን ለመውጋት አነሳሳቸው። ይህ ተግባራቸው ደግሞ ክቡር ዋጋን አስከፈላቸው።

የነዚህ አባት አርበኞች ድራማዊ ተግባር በዚ ኣላቆመም። እስቲ ከዓዲ ኳላ በሙላሳኒ (መረሳኒ?) አማካኝነት የተላከውን አንድ መረጃ እንመልከት፦

“በ9-6-1900 ከመቀሌ የተነሳው ሰላያችን ተስፋይ ወልደማርያም፦ ሰባት የደጃዝማች ማሕራይ ጀሌዎች ታስረው፡ ከራስ መኰንን ስር ሲጎተቱ በዓይኔ በብረቱ ኣይቻለው። ራስ መኰንንም ወታደሮቹን እስከ ቆቦ ድረስ እንዲቀጥሉ በማስፈራራት ሲያዛቸው ሰምቻለሁ። - መላሳኒ።”

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 7 - ደሞ ጀመረን” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ! :mrgreen:

የዕውቀት ሰዎች ይህንም ብታነቡት አንዳንድ ታሪካዊ ቁምነገር ታገኙበታላችሁ

http://www.ehrea.org/historypast.php

https://shabait.com/2013/01/18/the-infa ... of-nakura/

Digital Weyane
Member+
Posts: 8528
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Digital Weyane » 29 Oct 2022, 03:22

ውፈር ተበገስ ኻምዚ ሕዚ፣ ሳይንሳዊ መብረቕካ አውርደሎም፣
ብሱል ክእለት አማዕቢልካ፣ ብስልታትካማ አርዕዶም፣
መርአያ መንነት ውዳቤኻ ፣ አው መረጃ ፎሩም ዓልል ዓልል፣
መልሓሶም ክሕይኹ ፀላእትኻ።

ለትግራዋይ ጁንታዋይ ዎንድሜ Meleket ያለኝን አድናቆት አልደብቅም። :roll: :roll:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 29 Oct 2022, 04:58

"ፈስ ያለበት ዝላዪ ኣይችልም"! . . . "እውነት ሲነገር፡ ሓሰተኛ ያነጥሳል!" ብለን እኛም እንጨምርበት እንጂ! :mrgreen:

በነገራችን ላይ ታሪኩን የጣፉት ተጋዳላይ ዶ/ር ኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ ናቸው። :mrgreen: እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ታሪኩን ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ፡ በወንድማችን በAbere ጥያቄ መሰረት ነው ያጋራነው።

ተራ ካድሮችና የጦርነት ጥቅመኞች (ጦ.ጥ.) እንዲሁም ታሪኩ ላይ እንደተጠቀሰው "የደግያት ፋንታ፡ የደግያት ገረላሰና የአሳላፊ ገበንየ ልጆች" ቢስማማቸውም ባይስማማቸው፡ የኤርትራውያን አያት አርበኞች ታሪክ እንደ ትላንቱ ዛሬም ነገርም ከነገ ወዲያም ይተረካል፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። [አራት ሚልየን ነጥቦች]
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 31 Oct 2022, 03:54

ምዕራፍ 7 - ደሞ ጀመረን

ወቅቱ ምንም እንኳ ጣልያን ግዛቷን ለማረጋጋት በርካት እርምጃዎች ብትወስድም፡ የሃገሬው ሰው የአልገዛም ባዪነትና የእምቢታ መንፈስ የገነነበት እንደነበረ የሚያመለክቱ መረጃዎች አሉ። እዚህ እንደ አብነት ያቀረብናቸው ጥቂት ግለሰቦችና ተከታዮቻቸውን ቢሆንም፡ ጉዳዩ ለበርካታ ምርምሮች በር የሚከፍት ነው። እርግጥ ነው ‘አንገዛም እምቢ አሻፈረን’ በማለት ዱር ቤቴ በማለት መሳርያቸውን አንግበው የታገሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጀግኖች እንደነበሩ ይታወቃል።

ለምሳሌ በዚሁ ዓመት ስማቸው ጎልቶ ከሚወሱት እምቢተኛ ኣልገዛም ባዪ ዜጎች መካከል፦

“ በ‘ደምበላስ’ በኩል ከንቲባ ሓየሎም፡ በ‘ሰለድ’ ኣቅጣጫም የዓሳውርታው ዓሊ ኑሪ። በ‘አኽሩር’ ፊተውራሪ ስብሃቱ። እንዲሁም ደጃዝማች ባህታ ያሳደጉት፡ ልጅ ህብትዝጊ” (ማርቲኒ፡ ዘገባ 1898-9-1900) ገጽ 7) ይጠቀሳሉ።


በየአቅጣጫው ሲያንዣብቡ ይታዩ የነበሩት፡ ገዢዎችን ያርበደበዱ ኤርትራውያን፡ ኤርትራን ለወረራት የጣልያን ኃይል ከፍተኛ ስጋት ነበሩ። ስለሆነም፡ ገዢዎቹ ጣልያኖች፡ የነዚህ የኤርትራውያን አርበኞችን ዕለታዊ እንቅስቃሴ፡ ባለ በሌለ የስለያ መዋቅራቸውና የግንኙነት መስመራቸው ለመከታተልና ለማነፍነፍ ይገደዱ ነበር። ይህን የጣልያን ኣገዛዝ ዘመን በተመለከተ በቅጡ የተጠናና የተመረመረ የምርምር ውጤት ባለመጻፉ፡ የያኔውን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የከተበ ጥናት ባለመካሄዱ እጅግ ሳያሳዝነን ኣይቀርም። ለምሳሌ እስቲ የሚከተለውን የጭፍለቃና ድፍጠጣ ሰነድ እንመልከት፦

30-1-1901. ሂድ እንግዲህ! ከእምቢተኞች ጋር ደሞ ጀመረን!! ከ‘ኰዓቲት’ ከ‘ለመጨሊ’ እንዲሁም ከ ‘ሰገነይቲ’ መረጃዎች እየጎረፉ ነው። አንዳንድ የታጠቁ ኃይሎች፡ አንድም ወደ አከለጉዛይ ገብተዋል፤ ኣሊያን ለመግባት ሲያንዣብቡ ታይተዋል። ለምሳሌ በልጅ በይን (ደጃዝማች) የሚመሩ 12 ታጣቂዎች ታይተዋል።” (ማርቲኒ ዲያርዮ፡ 2ኛ ቅጽ፡ 337)።

ከሁለት ዓመታት በኋላ፡ ፈርዲናንዶ ማርቲኒ፡ ኤርትራን በጎበኘበት በኣንድ ተልዕኾው በተራራማው ስፍራ የምትገኘውን የ‘አባ ሰላማ’ን ቀዬም ጐብኝቶ ነበር፦

ይህ በድንጋይ የተካበው የአባ ሰላማ ቤተክርስትያን የተሰራው በደጃዝማች ማሕራይ ነው። ማሕራይ አልገዛም በማለቱ ናኵራ ላይ ታስሮ ነበር። ከናኵራ ደሴት በ1899 ከሌሎች ጓዶቹ ጋር አምልጧል” (ዲያርዮ 17-11-1903) በማለት ሲያስታውስ የኤርትራውያን ጀግንነትንም መስክሯል። ከናኵራ ደሴት አፈትልከው ስላመለጡት ጀግኖች ሲያስታውስም ድፍረታቸውና ቆራጥነታቸው ቁልጭ ብሎ እዬታየው ነበር።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 8 - የዓድዋው ደጃዝማች ገረስላሰ ቀጣዪ ተግባር” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 01 Nov 2022, 02:46

ምዕራፍ 8 - የዓድዋው ደጃዝማች ገረስላሰ ቀጣዪ ተግባር

አስቀድመን እንደገለጽነው ደጃዝማች ማሕራይ እንደታሰረ ብንገልጽም፡ ገዢዎቹን ጣልያኖችንና ተባባሪያቸውን የምንሊክን ኢትዮጵያን ግን፡ ገና እንቅልፍ ሲነሳቸውና ቁምስቅል ሲያሳያቸውን ግን እንታዘባለን። እስቲ ይህን የፈርዲናንዶ ማርቲኒ ሰነድ እንመልከት፦

“ደጃዝማች ገረስላሰ፡ ደጃዝማች ማሕራይን የሚይዙና የሚያስሩ ሰዎችን እያሰማራ እንደሆነ፡ ከዓድዋ ወኪላችን ‘ማሰ’ቲ’ የተለግራም መልእኽት ልኮልናል። ይህ ደግሞ የኛ የጣልያኖችና የንጉሱ የምንሊክም ፍላጎት ነው።

ማሕራይ የትግራይ ሰዎች ካዋከቡት፡ ወደ ግዛታችን እንዳይገባ ‘ሞሰ’ቲ’ ፍራትና ስጋት አለው። ምናልባት ‘ኣኽራን’ ወደተባለው ስፍራ ይሸሽ ይሆናል። ደጃዝማች ገረስላሰ ከሱ የአደን ስራ ጋር በተቀናጀ መልኩ እኛም አደኑን እንድናጧጡፍ ጠይቆናል። መልካም ነው! የሱ ሰዎች አደኑን መቼ እንደሚጀምሩት ይንገረን፤ ከአሁን በኋላ አደፍራሹና ለጸጥታችን ስጋት የሆነው ማሕራይ ብቻ ነው” (ማርቲኒ ዲያርዮ 17-9-1905)።

ታድያ ከዚህ የከፋ፡ በኤርትራውያንና ላይ ያነጣጠረ የሁለት እኩይ ኃይሎች ትብብር ምን ሊኖር ይችላል? ራሱ ፈርዲናንዲ ማርቲኒ በአካል ከተሳተፈበትና ማንም ሳያስገድደው ለመሰከረውና ላመነበት እኩይ ጉዳይ ታድያ ሌላ ምን ምስክርና እማኝ ያስፈልጋል?

በዓለማችን ላይ የተለያዩ የክዳት ተግባሮች ይፈጸማሉ። እንዲህ እንደ ኢትዮጵያው ያለ፡ አንዲት አፍሪካዊት ሃገር፡ እንደርሷ ኣፍሪካዊ በሆነ ጐረቤት ህዝብ ላይ፡ ከአውሮፓዊ ተስፋፊ ሃይሎች ጋር በመመሳጠር ፖለቲካዊ ዝሙት የፈጸመ ግን በፍጹም ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። ኢትዮጵያ ይባስ ብላም አይኗን በጨው ታጥባ ሳታፍር “ኤርትራ የኔ ነች፡ ትገባኛለች፡ አካሌ ናት” ማለቷ ደግሞ ይሉኝታ ቢስነትና ግልሙትና ከመባል ያለፈ ምንም ዓይነት መግለጫ ሊገኝለት የማይችል ጉዳይ ነው (የዚህ ጽሑፍ ኣብዛኛው ክፍል በነጻነት ትግል ወቅት የተጻፈ ነው)። በዚህ ይሉኝታ ቢስነት በተላበሰ አመለካከት ምክንያት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የህዝብ ልጆች ህይወት ተቀጥፏል። ለማንኛውም ወደ ዋናው ታሪካችን እንመለስ።

በኤርትራውያን እምቢተኞችና ኣልገዛም ባዮች ላይ እኩይ የሆነ ተንኰል ለመሸረብ ተዘጋጀው የነበሩት፡ ምንሊክ፡ የትግራይ አገልጋዮቹና ተስፋፊዎቹ ጣልያኖችም፡ በቀትር መነጋገሩ አልበቃ ብሏቸው፡ የተንኰል ሴራቸውን በሌሊትም ሳይቀር ይሸርቡ ነበር። እስቲ ይህን መረጃ እንመለከተው፦

“ዓድዋ 5-12-1905 ። ከዓጋሜው ሹም ከራስ ስብሓት ልጅ ማለትም ከደጃዝማች ደስታ ጋር ብዙ ግዜ ተገናኝተናል። ዛሬ ግን፡ ሰው እንዳያየን በሌሊት መጥቶ ነው የተገናኘነው። የውይይታችን ምክንያት ደጃዝማች ማሕራይን በተመለከተ ነው። የኤርትራ መንግስት እንዳይጠላው፦ ምንም እንኳ ማሕራይ በግዛታችን ውስጥ ቢኖርም፡ እሱን መያዝ ግን ቀላል ኣይደለም በማለት ይገልጻል የዓጋሜው ሹም ደስታ። ቢሆንም ግን፡ የደጃዝማች ማሕራይ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ መሆኑን፤ ራሱ ሹም ዓጋመ ደስታም የኛ የጣልያኖች ወዳጅ መሆን እንደሚሻም ገልጿል። በዝግ ቤት ውስጥ ነው የተወያዬነው። እኔም፡ የኤርትራ መንግስት የሚፈለገው፡ ማሕራይ ከደንበር አካባቢ እንዲርቅ እንጂ ሌላ የምንሻው ነገር እንደሌለ ገልጨለታለሁ። -“ሞሰቲ”( ማርቲኒ ዲያርዮ)።

ይህ እንግዲህ ዓድዋ ላይ የነበረው የጣልያን መንግስት ወኪል ‘ሞሰቲ’ የጻፈው የቴሌግራም መልእኽት መሆኑ ነው።

ይህም በመሆኑ ከተወሰነ ግዜ በኋላ ደጃዝማች ማሕራይ በትግራዩ ሹም ዓጋመ ደስታ አማካኝነት በቁጥጥር ስር ዋለ። በምን ሁኔታና መቼ እንደተያዘ በውል ባይታወቅም፡ በዓጋመው ሹመኛ ብደስታ ቁጥጥር ስር ዋለ። ባልታወቀ ምክንያትም የዓጋመው ሹመኛ ደስታ፡ ለግዜውም ቢሆን ደጃዝማች ማሕራይን ለጣልያንም ሆነ ለምንሊክ አሳልፎ ለመስጠት እንደማይሻ የሚከተለው መረጃ ይጠቁማል፡ ይህ ውሳኔው ግን ግዜያዊ ነበር፦

“የጣልያን ወታደሩና የዓዲዃላው ሰው አዝማች ተስማንኪኤል፡ ለኣዅሱም ጽዮን ክብረበዓለ በሕዳር ወር ወደ ኣዅሱም እንደሄደ፡ የዓጋሜውን ሹመኛ ደስታን ኣግኝቶት ነበር። ተስማንኪኤል፡ የዓጋመውን ሹመኛ ደስታን “ደጃዝማች ማሕራይን ለምን እንዳሰረ” ጠይቆት ነበር። የዓጋመው ሹም ደስታም “ማሕራይ ክፉ ሰው ስለሆነ ነው ያሰርኩት” በማለት መልሶለታል። “ለምንሊክስ ታስረክበዋለህን?” ብሎ ተስማንኪኤል ሲጠይቀውም፤ የዓጋመው ሹም ደስታ እንዲህ ነው ያለው “ይህን ጉዳይ በምስጢር ያዘው እንጂ፡ ለጣልያን ሳላስረክብ በኔ ቁጥጥር ስር እንዲቆይ ከንጉስ ምንሊክ ጋር ተስማምተናል” በማለት ነግሮታል።” (ማርቲኒ ዲያርዩ 7-11-1905 ።)

የትግራዩ ሹም ዓጋመ ደስታ “ምስጢር ነው፡ ጉዳዩን በምስጢር ያዘው እንጂ” ወዘተ እያለ የቀባጠረው ዝም ብሎ ነው።

ከአገላለጹ የምንረዳው በደጃዝማች ማሕራይ ላይ የግል ጥላቻ እንደነበረው ነው። ማሕራይን ከሱ ጋር ስለመያዝና አለመያዝ እንደሆነ፡ እሱ የዓጋሜው ሹም የሚወስነው ጉዳይ አልነበረም። ስልጣኑ ከትንሿ የዓጋሜ ኣውራጃ የሚያልፍ አልነበረም። ደጃዝማች ማሕራይም ቢሆን የታሰረው በዚህ በዓጋሜው ሹመኛ ትእዛዝ ኣይደለም።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 9 - ምኒልክን ማርቲኒ እንደጐበኘው” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 02 Nov 2022, 02:16

ምዕራፍ 9 - ምኒልክን ማርቲኒ እንደጐበኘው

ግዜው፥ ጣልያንና ምንሊክ እርስ በእርስ የሚወዳደሱበትና የሚላላሱበት፡ አሁንም አሁንም አዳዲስ ውሎችንና አዳዲስ ኪዳኖችን የሚፈጽሙበት ወቅት ነው። የሸዋው ንጉስ ምንሊክም፡ ፈርዲናንዶ ማርቲኒን፡ በአካል ፊት ለፊት ለማግኘት በመመኘት ስፍርቁጥር ዬሌለው የናፍቆት የቴሌግራም ጥሪዎችን በማድረግ ጋበዘው። “ቦሩ ሜዳ” በተባለው ስፍራ ለመገናኘትም ቀጠሮ በመያዝ ተስማሙ። ነገር ግን በራስ መኰንን (የኃይለስላሴ ኣባት) ሞት ምክንያት፡ ምንሊክ ስፍራውን ለቆ ለመሄድ ስላልቻለ፡ ማርቲኒን ወደ አዲስ አበባ ጋበዘው።

ማርቲኒም በ23-4-1906 ከአስመራ በመነሳት ጉዞውን ጀመረ። እስከ ዓዲዃላ ድረስ በበቅሎ ተጓዘ። ከትግራይ እስከ ሸዋ ድረስ ያሉ ሁሉም የምንሊክ ራሶችና ደጃዝማቾችም በየግዛታቸው፡ ለማርቲኒ ክብር በወታደራዊ ሰልፍ አጅበው እንዲያስተናግዱት ከምንሊክ ትእዛዝ ተላለፈላቸው። ራሱ ምንሊክም፡ በኤርትራ የጣልያን አስተዳዳሪውን ፈርዲናንዶ ማርቲኒን፡ 60 ሺ ወታደሮችን አሰልፎ አዲስ አበባ ላይ በክብርና በአጀብ ተቀበለው።

ማርቲኒ ምንሊክን ለመጎብኘት አዲስ አበባ በቆየባቸው ከ100 በማያንሱ ቀናቶች፡ በጉዞው የታዘበውንና ያየውን ብዙ ነገር ጽፏል።

አዲስ አበባንም “ከተማ ሳትሆን የመንደር ጥርቕሞሽ ነች” በማለት ገልጿታል። ይህን በመሰለው፡ ምንሊክ ከአውሮጳ ተስፋፊ ገዢዎች ጋር በሚሞዳሞድበትና በሚላላስበት ወቅት፡ በኤርትራ ህዝብ ላይ የነበረውን ጥላቻ ለመግለጽና ከአውሮጳውያን ተስፋፊዎች ጋር የነበረውን ጠንካራ ኪዳንና ውል ለማስመስከር፡ ኤርትራውያን አርበኞችንና አንገዛም ባዮችን ለመጨፍለቅ ኣበርትቶ ሲሰራ ታዬ። ደጃዝማች ማሕራይንና በርካታ ሌሎች ኤርትራውያን አያት አርበኞችን በሰንሰለት አስጠፍሮ ወደ መሃል አገር በመውሰድ ደብዛቸውን አጠፋ። ከአሁን በኋላ ባሉት ምዕራፎች ስለ ደጃዝማች ማሕራይ ላናነሳ ነው። ይህቺኛዋ የመጨረሻዋ ነች፦

ፈርዲናንዶ ማርቲኒ፡ ወደ ሸዋ ለመሄድ በትግራይ በኩል ያልፍ በነበረበት ወቅት በደብተሩ እንዲህ ብሎ አስፍሯል፦

“ዛሬ ደጃዝማች ገረስላሰ አልሸኘኝም።” በማለት ጀምሮ እንዲህ ይቀጥላል “ ደጃዝማች ገረስላሰ ከሐውዜን ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ግዛቱ ሄዷል። ከእምባ ጽዮን እየመጡ ያሉትን እስረኞች [ያለም ንም ጥርጥር ኤርትራውያን እስረኞች ናቸው] እየተጠባበቀ ነው። ይዟቸውም ወደ ሸዋ ያቀናል። ከእስረኞቹ መካከል ያ ከ ‘ናዅራ’ ያመለጠው ደጃዝማች ማሕራይም ይገኝባቸዋል።” (ማርቲኒ ዲያርዮ 3-5-1906 ።)

ከጥንት ከጠዋቱ የኢትዮጵያ ኣካሎች የሚባሉቱ፡ የኢትዮጵያ አካሎች የሚያስብላቸው አንድ ታሪካዊ ነጥብ ቢኖር ይህ የሚከተለው ታሪካዊ ሃቅ ነው። እሱም፦

ኤርትራውያን ከጥንት ከጠዋቱ ለነጻነታቸው ሲታገሉ፡ የትግራይና የአማራ መሳፍንቶች ደግሞ ከማንኛውም ወራሪ ኃይል ጋር ተጎዳኝተውና ተባብረው ኤርትራን ሲጨፈልቁ ነው ዬታዩት። ለምሳሌ የጎንደር ታሪክ ከቱርዅ ጋር፡ የአጼ ዮሃንስ ታሪክ ከእንግሊዝና ከግብጽ ጋር፡ የምንሊክ ታሪክ ከጣልያን ጋር፡ የሃይለስላሴ ታሪክ ከጣልያንና ከአሜሪካ ጋር፡ የደርግ ታሪክም ከአሜሪካና ከሶቭዬት ህብረት ጋር ወዘተ መመልከት ይቻላል። ይህ ታሪካዊ ሃቅ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳዬን፡ የኤርትራ ህዝብን በፍጹም የማይነጥፍና ዝንፍ የማዪል የአርበኝነትና የአልገዛም ባዪነት የትግል ስሜትንና፤ የኤርትራን ህዝብ ለመጨቆንና ለመደፍጠጥ የኢትዮጵያን ከማንኛውም የዓለም ተስፋፊ ኣካል ጋር የነበራትን ጉድኝት ነው፡ ፍንትው አድርጎ የሚያስተምረን።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 10 – ከሳሆ ህዝብ ታሪክ በጭልፋ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:


Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 02 Nov 2022, 04:54

ታለም ምነው፡ ታጋይ ኣባቶቻችን የጻፉትን የኤርትራ ታሪክ፡ በወንድማችን በAbere ጥያቄ መሰረት ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ብናጋራቸው፡ ምኑ ነው የቆረጠሽ እቴዋ! :mrgreen:

አንድማ ዴስ ያላለሽ ነገር ኣለ። ታድያ ኣንቺን ዴስ አላለሽም ቢለን ታሪካችንን ከመንገር ወደ ኋላ የምንል ይመስልሻልን? ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ኤርትራዊ ታሪካችንን ዛሬም ነገርም ተነገወዲያም እንደትናንቱ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር ለታሪክ አፍቃሪዎች እንነግራለን። ዴስ ታላለሽ የኛን ጥሑፍ አለመክፈት ዲሞክራሲያዊ መብትሽን መጠቀም ነው እጂ፡ ይሄን ያህል በፎቶ ሾፕ መቕዘን ኣይጠበቅብሽም፡ ምን ኣለፋሽ እቴ?
:mrgreen:
Fiyameta wrote:
02 Nov 2022, 04:07
. . .


ነገሩ ነው እንጂ፡ በፎቶ ሾፕሽ ያስቀመጥሻው ኣካላትን በተመለከተ የኛ ነጻ እዪታ

ነፍስኄር ስዩም መስፍንን በተመለከተ https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=245489

ጌታቸውን ረዳን ወዘተዎቹን በተመለከተ ዴግሞ https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=191091

እንዲህ አድርገን፡ ተሩቅም ከቅርብ ታሪክ አጣቅሰን ወረኛንና የሌለ ታሪክ ፈጣሪን ዕርቃኑን እናስቀራለን እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 03 Nov 2022, 03:05

ምዕራፍ 10 – ከሳሆ ህዝብ ታሪክ በጭልፋ

የብሄረ ሳሆ ህዝብ፡ ነጻነታቸውን ኣፍቃሪ በማንነታቸው ኩሩ ከሆኑ የኤርትራ ህዝብ መካከል፡ አንዱ ነው። ለዘመናት ከጥንት ከጠዋቱ ጀምረው፡ እየተግተለተለ ለሚመጣባችው ማንኛው ዓይነት ወራሪ ኃይል፡ በፍጹም "አንምበረከክም" በሚል ወኔ በመጋፈጥ ለማንነታቸው ለነጻነታቸውና ለብሄራዊ ኩራታቸው ሲሉ በአይበገሬነት መክተዋል።

የሳሆ ህዝብ በተለይም ጣልያን ወደ ቀጠናችን ከመምጣቱ 300 ዓመታት በፊት በ”ዓሳውርታ”ዎች እየተመሩ፡ እጅግ ገደላማና አዳጋች በሆነው መልክዓምድራቸውም ታግዘው፡ ከምጽዋ በመሳሊሕ - ማህዮ - ሓዳስና ሕርጊጎ ኣድርጎ የሚሄደውን የንግድ መስመር ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውት ነበር።

የትግራይ ሆኑ የጎንደር ነገስታት ከሳሆ ህዝብ ጋር በመስማማት ለሳሆዎችም ግብር በመክፈል፡ በዚህ በጠቀስነው ወደ ምጽዋ የሚወስድ የንግድ መስመር ሊተላለፉና ሊጠቀሙ ይችሉ ነበር። ለምሳሌ እንደ
- ቆዳ
- የዝሆን ጥርስ
- ዝባድ . . . ወዘተ የመሳሰሉ ጭነቶችን የያዙ የትግራይና የአማራ መሳፍንት ነጋዴራሶች፡ መጀመርያ በመሳሊሕ በኋላም በማህዩ ከዚያ በመቀጠልም በተኮንዳዕ ቀተጥ ይከፍሉ ነበር።

- ለአንድ የበቅሎ ጭነት ግማሽ ባጤራ ‘ብር’
- ለአንድ የግመል ጭነትም ግማሽ ባጤራ ‘ብር’
- ለአንድ ጭነት አህያም ሩብ ባጤራ ‘ብር’
- ለአንድ የተሸከመ ሰውም፡ አንድ እፍኝ (እህል) ይከፍሉ ነበር።” (ማርቲኒ ዲያርዮ 1904፡ ገጽ 406)

ግብሩ ወይ ቀረጡም፦
“- 1/5 ለ”ፈቐርቶ”ዎች
- 2/5 ለ ‘ላሊሽ ዓረ’
- 2/5 ለ ‘ማሱንዳ’ (ለ’ዓሳሊሰ’ ሰራዊት) ይከፋፈል ነበር” (ማርቲኒ ፡ ከማሁ)።

በ1891 የጣልያን ‘አስተዳደር’ ይህን ከጥንት ሲሰራበት የቆየውን የቀረጥ አሰራር በመሻር፡ ለ”ዓሳውርታ” መሪዎች ደሞዝ መክፈል ጀመረ።
በኋለኛው ዘመን የታወቁት የሳሆ መሪ ዓሳውርታ የጎበዝ አለቃ ሹመኖች
- ኣቡበከር ናስር፡
- ሹም ዕመር ሲለማን፡
- ሹም ዕመረዲን ኢብራሂም፡
- ሹም ሙሳ ኣሕመዲን፡
- ቃዲ ኢብራሂም ዓብዱ . . . ወዘተ ናቸው።

የሳሆ ህዝብ ኣባቶች፡ በጥንት ግዜ በውጊያ የተጎናጸፉትን ድል በኩራት ያስታውሳሉ። ‘ማህዮ’ ከተባለው ስፍራ ወረድ ብሎ በሚገኘው ‘ዲማ’ በተሰኘው ስፍራ ከቱርኽ ጋር ተዋግተዋል። ንጉስ ልብነ ድንግል የሳሆ ህዝብን ለማስገበር ሙሉ ሰራዊቱን በማሰማራት “ድኾኖ”ን ወሮ ነበር። የሳሆ ህዝብ ግን “ሓዳስ” በተባለው ወንዝ አካባቢ አሸንፈውታል።

በዚህ ጦርነትም የልብነ ድንግል ሰራዊት በፍጹም ተደምስሶ ተበታተነ። ዕለቱም ዕለተ ሓሙስ ነበር፡ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ የሳሆ ህዝብ “ሚዐ ሓሙስ” ማለትም “ገደኛዋ ሓሙስ” በማለት ድል የተቀዳጁባትን ዕለት ይዘክራታል።

በ1872 የትግራዩ ራስ አርአያ የሳሆ ህዝብን ለማስገበር ሞከረ። አሁንም ሳሆ “ሓዳስ” በተባለው ወንዝ ዳርቻ ደመሰሱት። በ1879 በብላታ ገብሩ የተመራው የራስ አሉላ ሰራዊት ወረራ በማካሄድ ሳሆን ለማስገበር ሞከረ። “ሩብሩብያ” በተባለው ስፍራ ከባድ ውጊያ ተካሄደ። የትግራዩ ሰራዊት ተርበድብዶ ተሸነፈ። ራሱ አሉላ ሳይቀር ዳግም ሰራዊቱን አግተልትሎ ወረራ አደረገ። አሉላም ቢሆን በሳሆ ተሸንፎ በባዶ እግሩ በመሮጥ ሸሽቶ ከሞት አመለጠ።

የሳሆ ህዝብም ከአሉላ ሰራዊት ስፍር ቁጥር የሌለው መሳርያና ንብረትን ማረከ። በመቀጠልም የሳሆ ህዝብ፡ የራስ አሉላን ሰራዊት “ከሪቡሳ” በተባለ ስፍራ ድባቅ መቱት። ሳሆዎች “ኣሓይ ጉማይ ዓለማለ” የሚል የውግያ መፈክር አላቸው። ትርጉሙም “ጥንብ አጋድሜልሃለሁና (ግዳይ ጥዬልሃለውና)፡ ና ና ኣሞራው ተከተለኝ” እንደማለት ነው።

ሳሆዎች ንጉስ ዮሃንስን ለመውጋት ከጣልያን መሳርያ ቢቀበሉም እንኳ፡ የኋላ ኋላ ግን ለጣልያኖችም “እምቢ ኣንገዛም!” በማለት ብረታቸውን በጣልያን ላይም አቅንተዋል። በተለይም “ቶርዓ” የተባሉት ሳሆዎች የደጃዝማች ባህታን እምቢታ ዋና ደጋፊዎች ነበሩ።

ማንኛውም ለጣልያን እምቢ ኣልገዛም ይል የነበረ ኤርትራዊ፡ ዋልታና ማገር እንዲሁም ደጀኑ የሳሆ ህዝብ ነበር።

የጣልያን መንግስት ሳሆዎችን ሊቆጣጠራቸው የቻለ ከ 15 ዓመታት ውጊያ በኋላ ቀስ በቀስ በተንኰልና በሸፍጥ ነው ታግዞ ነው የተቆጣጠራቸው።

ተከታዩ አብነት፡ በመጨረሻው የጣልያን ዘመን የሳሆ ህዝብ የአልገዛም ባዪነት ትግል ምን ይመስል እንደነበረ ቁልጭ አድርጎ ስለሚያሳዬን እሱኑ እንመለከታለን።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 11 - የሳሆው ጀግና - አቡበከር አሕመድ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:
Last edited by Meleket on 03 Nov 2022, 03:17, edited 1 time in total.


Post Reply