Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 03 Nov 2022, 05:06

ታለሜዋ ኣሁንማ "ሰላም ሊሰፍን ነው" ስትባዪ ግዜ ይበልጥ እያንጠባጠብሽ መቕዘን ጀመርሽ በፎቶ ሾፕ! በይ አሁን ቁርጥሽን እወቂ ወደ "ዲማርኬሽንና ሕገመንግስት" ሆኗል ትልቁ ጎዳና። :mrgreen:

ፎቶ ሾፕሽ ላዪ ያወላገድሽው ኤርትራዊው ጨዋታ እንዲህ ነው፦

ዶ/ር ኣብዪ፡ "ልቢ ትግራይ የሚባለውን መንገድ ማየት አለብኝ።"

የኤርትራ ህዝብና የኤርትራው ብረዚደንት፦ "ታድያ ምን ችግር አለው፡ "ዲማርኬሽኑን" ስናደርግ እናሳይሃለን። ብቻ ፈጠን ፈጠን በል።" :mrgreen:

ለማንኛውም እነዚህኞችንም ብታነቢ እየተዝናናሽ ቁምነገር በመገብየት ትጠቀሚያለሽ

ይሄኛው ሃገራችን ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ ከመላኳ በፊት የተጣፈ ነው ዕለቱን አስተውዪው እቴዋ https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=17&t=159593

ይሄኛው ደግሞ ሃገራችን ልዑኳን ወደ አ/አ በላከችበት ወቅት መሆኑ ነው https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=17&t=160263&

ተዝናኚ! የኛ የኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ነጻ እዪታን ለማጋራት ያህል ነው!
:mrgreen:
Fiyameta wrote:
03 Nov 2022, 03:13
. . .

ይሄኛው ሁለተኛው ፎቶ ሾፕሽ ደግሞ፡ ምንም ከነባራዊው ሁኔታ ጋር የማይሄድ መሆኑን ተገንዝበናልን፡ እዛ የትግርኛው ትረካችን ላይ ያስገበሽው ነው። መቼም ጥላቻዬ ከወያኔ ከወያኔ ውስጥም ከጁንታ ጋር ነው ትይና፡ እንዲህ አድርገሽ ደግሞ ከመላው "ትግራዋይ" ጋር ጥልሽን ትገልጫለሽ። ምነው እቴ ኢትዮጵያውያን ይታዘቡኛል ኣትዪም እንዴ? ደግሞስ ኤርትራውያን እነ አቶ ወልደአብ ወልደማርያምና ሌሎቹ እንዲያው በደፈናው ከትግራይ የፈለቁ ኤርትራውያን ይታዘቡኛል ኣትይምን? ምኗ ተራ ካድሪት ነሽ እቴ
:mrgreen:
Fiyameta wrote:
03 Nov 2022, 03:17
. . .

አሁን ከኤርትራውያን ሊቀ ሊቃውንት አንዱ ክቡር ታጋይ ዶ/ር ኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ ወደ ጻፉት ብርቅ ታሪክ እናቀናለንና፡ ሌላ ስፍራ ሄደሽ ተጸዳጂ! መቼም በያጥሩ መጸዳዳት አሁንም አልተውሽም "ኮለኔል ታሪኩ" ቢያዩሽ ያፍሩብሻል፡ ኧረ ይጠየፉሻልም!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 04 Nov 2022, 02:37

ምዕራፍ 11 - የሳሆው ጀግና - አቡበከር አሕመድ

አስቀድመን የደጃዝማች ማሕራይን ታሪክ አይተናል። ይሄኛው ግዜ የሚለዬው በትንሽ ነው። የሳሆው ጀግና አቡበክር አብዛኛውን ግዜው ኤርትራ ውስጥ ሆኖ ሲንቀሳቀስ ታይቷል።

ከቀይ ባሕር ማዶም አልፎ አልፎ አንዳንድ ተባባሪዎቹ መታዬት ጀምረው ነበር። አቡበከር በአባቶቹ ተራራማ ሃገር እንደ አራስ ነብር እየተጐማለለ ጣልያኖችን ፋታ ነሳቸው።
እስቲ የሚከተለውን ሰነድ እንዪ። መልእኽቱን ወደ አስመራ የላከው ሙላሳኒ የተባለ ዓድዃላ ላይ የነበረ ጣልያን ነው። እንዲህ ይነበባል፦

“ከትላንት በስትያ ከዓድዋ የተነሳው፡ ቸሩ ደረስ የተባለው ሰላያችን እንደነገረን፡
- ባሻ ንጉሰ
- አንድ ርስቱ የሚባል ሰውና
- ገረንስአ ዓንደብርሃን
እንዲሁም ሌሎች ታጣቂዎች፡ ወደ ኤርትራ አቅጣጫ ሲጓዙ ታይተዋል . . . ሰላዩ ሁሉንም በአካል ስለሚያውቃቸው፡ መረጃው ትክክለኛ ነው ለማለት ይቻላል። እንደ ሰላዩ ኣባባል፡ ከናኩራ እስር ቤት ካመለጡት መካከል 8 ሳሆዎች አሁን ደግሞ ከትግራዩ ራስ ኣምልጠዋል። የትግራዩ ራስም፡ እነዚህ እምቢተኞች ወደ ኤርትራ እንዳይገቡ መንገድ ለመዝጋት በሁሉም አቅጣጫ ብርቱ ጥበቃ እንዲደረግ መመርያ ኣስተላልፏል። ማንኛውም መተላለፊያ መንገድ ብርቱ ጥበቃ እየተካሄደበት ነው።” (ማርቲኒ ዲያርዮ 10-4-1900 ገጽ 107)።

ይህ ታሪካዊ ሃቅ የሚያሳየን፡ ብዙ ኤርትራውያን አያት አርበኞች የናኩራን እስር ቤት ጣጥሰው ይወጡ እንደነበረ፡ ነገር ግን ከጣልያን አገዛዝ በምንም የማይሻሉት ምንሊክና የትግራይ አገልጋዮቹ ከጣልያኖቹ ጋር በመሻረክና በመመሳጠር ስፍር ቁጥር ዬሌለው ችግርና መሰናክል ይፈጥሩባቸው እንደነበር ነው።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 12 - የሳሆ ህዝብ ረዢም የኣይበገሬነት ትግል ጣልያኖችን ሲያጥወለውላቸው” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 05 Nov 2022, 02:14

ምዕራፍ 12 - የሳሆ ህዝብ ረዢም የኣይበገሬነት ትግል ጣልያኖችን ሲያጥወለውላቸው


ማንኛውም አለ ዬተባለ የሽፍቶች መፍጨርጨር ልክ ገብቷል። ተቃዋሚዎች በሙሉ ተደምስሰዋል። ከእንግዲህ ወዲህ ኤርትራ ውስጥ የሚያሰጋን ምንም ዓይነት ኃይል ዬለም። የኤርትራን ህዝብ እንዳያንሰራራ አድርገን አከርካሪውን ሰብረነዋል።

ጣልያኖች “ከእንግዲህ ጀምረን ወጥነነው ወደ ነበረው ወደ ዘር የማጥፋት “ጄኖሳይድ” ትልማችን ትግባሬ መግባት እንችላለን፡” እያሉ በሚያስቡበት ወቅት፤ አንድ በወኔ የተሞላ የአንገዛም ባዪነት እንቅስቃሴ በሳሆዎች በኩል እንደተነሳባቸው አወቁ።
ይህ የእምቢተኛነት እንቅስቃሴ፡ በሰነዳቸው ውስጥ “አቡበከር ማሕሙድ” ብለው በሚጠሩት አርበኛ ይመራ የነበረ ነው። ጣልያኖቹን ይበልጥ ያሰጋቸው፡ የአቡበከር እንቅስቃሴ ከግዜ ወደ ግዜ በሰው ብዛት ሆነ በትጥቅ እየጎለበተ የመሄዱ ጉዳይ ነበር። እስቲ ለአብነት ይሆነን ዘንድ፡ መጀመርያ ላይ ስለ አቡበከር እንቅስቃሴ ስለተጻፈው አንድ ሰነድ እንመልከት፦

“ከአራት ዓመታት ፍጹም የሰላምና የእርጋታ ሁኔታ በኋላ፡ ይሄው አሁን የመጀመርያው የተኩስ ድምጽ እዬተሰማ ነው። ሰላም ከሚያደፈርሱት መካከል አንዱ የዓሳውርታው አቡበከር ነው። መጀመርያ ላይ እሱን አደብ ለማስገዛት ብዙ ሰራዊትን ማሰማራት አስፈላጊ ሆኖ አልታዬንም ነበር። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን፡ የመሳርያ ትጥቁ እየተበራከተ ሄዷል። እንደምንሰማውም የ ‘ኮርባርያው
- ደጃዝማች በይንና
- ቄስ ዘርኡም . . . ከአቡበከር ሰራዊት ጋር ተቀላቅለዋል። አቡበከር በግምት ከ40-50 ታጣቂዎች እንዳሉት እንገምታለን። መሳርያና ትጥቅም ስላከማቸም ብዙ እየተዳፈረን ነው። ‘ማህዮ’ በተባለው የንግድ መስመር፡ ለስለላ በተሰማሩ የሰራዊታችን ክፍሎች ላይ ተኩስ ከፍቶባቸዋል።” (ማርቲኒ ዲያርዮ 25-6-1901፡ 498)

ጣልያኖች ይህን የመሰለውን የአልገዛም ባዪነት እንቅስቃሴ፡ ባለ በሌለ የስለላ መረባቸው አማካኝነት በትኩረት ይከታተሉት ነበር። በተለዪም በሳሆዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ የሌላ ብሄሮች አርበኞች መካተት መጀመራቸው በጣልያኖች ዘንድ በስጋት ላይ ስጋት ጋረጠባቸው። ከግዜ ወደ ግዜ እየተስፋፋና እየበረታ የሄደው ተቃውሞም ጣልያኖችን ናላቸውን አዙሮ አጥወለወላቸው።

በመሆኑም ጣልያኖች የሳሆን እንቅስቃሴ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመደፍጠጥ ቡራከረዩ አበዙ። ይሁን እንጂ ልክ እንደ ደርጉ

የመሬቱ አቀማመጥ እጅግ ስላዳገተን፡ ተራራማና ገደላማ ሆነብን እንጂ . . .” እያሉ ሽንፈታቸውን በተራራውና በሸንተረሩ ላይ ሲያላክኩ ተሰሙ። እስቲ ይህን ከላይኛው መልእኽት የቀጠለውን ዘገባ ከማርቲኒ ደብተር እንመልከት፦

“የዓሳውርታ ስፍራ እጂግ የማይመች፡ ተስፋቢስና ምንም ፋይዳ ዬሌለው ይሁን እንጂ፡ እንቅስቃሴያቸውን ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ መጨፍለቅ ሳያስፈልገን ኣይቀርም።

ዛሬ ማለዳ ከምጽዋ አንድ የቴለግራም መልእኽት መጥቷል።

ዖኖኸባ ከተባለው ቀጠና 11 ሰዓት ላይ ከማለዳው 11:30 ላይ፡ ወደ ዓዲ ናህባይ የተባለ ስፍራ የተንቀሳቀሰው የሰራዊታች ኣባል ፊተውራሪ ረዳ፡ ‘ትዅል ዖኖኸባ’ ላይ በእምቢተኞች ላይ ተኩስ ከፍቷል። ትልንቲ (አስር አለቃ) ቦርሳረሌ ከነ 12 ምርጥ ታጣቂዎቹ፡ አስር አለቃ አንድረዩኒ ከነ 5 ምርጥ ታጣቂዎቹ፡ አንዱ በቀኝ አንዱም በመሃል ጥቃቱን በእምቢተኞች ላይ ከፍተዋል። እኔና አስር አለቃ ደሮስም ከነ 16 ምርጥ ታጣቂዎቻችን በስተግራ በማጥቃት፡ በቁጥር 20 የሚሆኑትን እምቢተኞች ገጥመናቸዋል። እንቢተኞቹ ከሁለት ተከፍለው፡ ገሚሶቹ በስተሰሜን ገሚሶቹም በስተምስራቅ ተሰውረዋል። ሰላዮቻችን እንደነገሩን የአቡበከር ቡንድ ነው ያሉት፡ “ዓላምቦ” ወደ ተባለው ስፍራ አቅጣጫ እያመራ ብርቱ ተኩስ ከፍቷል። ባንዳ ደሮሲና አባሎቼ እንዲሁም ሌሎቹ የሰራዊታችን ክፍሎች በጋራ የመልስ ተኩስ አድርገውለታል። በ ‘ዓላምቦና ኩመይል’ በኩል ጥበቃ በእጥፍ እንዲጨምር ትእዛዝ ኣስተላልፊያለሁ።”

ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ በማለት ጣልያኖች ከነ ሰራዊታቸው አቡበከር ማሕመድን ለመደምሰስ ተነስተዋል። ታድያ ኣቡበከር ምኑ ሞኝ ነው እንደብስኩት የሚቆረጠምላቸው? አቡበከር ሆየ አሳውታ አይደለም እንዴ? አሳውርታ ማለት እኮ በአንድ በኩል የአራስ ነብር ልጅ ማለት ነው። አሳኣውርቶች አባታችን ከአንዲት ነብር ነው የወለደን ብለው የሚኩራሩበት ወግ አላቸው። እውነት ለመናገር በጀግንነታቸው የሚያሳዩት የነብርን ጠባዪ ነው።

ጣልያኖችም ይህን የአሳውርቶች ወግና አፈታሪክ ከማንም በላይ ያውቁታል። በመሆኑም በሳሆዎች ጀግንነት ይርዱና ይሸማቀቁ ነበር። በዚች ጥቂት እምቢተኖች ላይ ያነጣጠረች በምትመስል ዘመቻ፡ ጣልያኖች ይህን ያህል የተጨነቁበት ምክንያትም፡ የሳሆዎች ተዋጊነት እጅግ ስላርበደበዳቸው ነው። በዚሁ ዕለት በተጻፈው እየጠቀስነው ባለው ዘገባ ላይ ስለ ነበረው ውጊያ የሚገልጸው ወደ አስመራ የተላከው መልእክት የመጨረሻ ክፍል እንደሚከተለው ይነበባል፦

“ 9 ሰዓት፡ የብርጌድ መሪው ፍራንሳ ለረዳትነት በተጠራው መሰረት ከነ ሰራዊቱ ወደኔ መጥቷል።

አመጣጡ የተዳከሙትንና በውሃ ጥም የተጠቁትን የሰራዊታችን አባሎች ለመተካት ነው። ውሃና ምግብ ይዣለሁ። አስርአለቃ ኩነታን ከነ 25 ጓዶቹ ጠርቸዋለው። የውሃ እጥረት አለን። ወደ ታችኛው የ‘ሱሮ’ አካባቢ አንድ ኩባንያ (የመቶ) ሰራዊት መላክ ሳያስፈልገን አይቀርም። መቆፈርያ፡ ስንቅና ውሃ የሚያመላልሱ በቅሎዎችም ያስፈልጉናል። ‘ወይዓ’ ከተባለው ስፍራ በስተደቡብ አቅጣጫ ነው በቅሎዎቹን የምንፈልጋቸው። ብላታ ሓይልዝጊ የተባለው የሰራዊታችን አባል ቀላል የሚባል የመቁሰል አደጋ አጋጥሞታል። ከ 4ኛ 5ኛ የመቶዎችም (ሻምበሎችም) ሁለት ሁለት ሰዎች ቆስለውብናል። ገረስላሰና ገረኪዳን የተባሉት አባሎቻችንም በከባድ ቆስለዋል።

ከእምቢተኞቹ መካከል አንድ ተገድሏል። አንዲት ሴትዮም ተይዛለች [ተማርካለች]። በአሁኑ ሰዓት ተኩሱ ኣቁሟል። ፍራንሳም በበኩል፦
- አንድ እምቢተኛ ሲቆስል
- ጥቂት የሚባል የገብስ ዱቄትም ተማርኳል እያለ ነው። በደም የተጨማለቀ ኮትም ተገኝቷል። የተገደለው እምቢተኛ መሳርያም ተማርካለች። ‘ግብጣን’ ጋረለ” (ማርቲኒ ዲያርዮ 1901፡ ገጽ 498)

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 13 – ድል ያልተመዘገበበት 20 ለ 200 የተደረገ ውጊያ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 07 Nov 2022, 03:34

ምዕራፍ 13 – ድል ያልተመዘገበበት 20 ለ 200 የተደረገ ውጊያ

በኤርትራ የኢጣልያ መንግስት አስተዳዳሪው ፈርዲናንዶ ማርቲኒ፡ የሚመለከተውን ሪፖርት እንዳነበበ፡ እጅግ ተቆጥቷል። ልክ ከራሱ ጋር እንደሚነጋገር እብድም በጭንቀት እንዲህ እያለ ደብተሩ ላይ ከትቧል፦

“ሊገባኝ እንደቻለው፡ ውጊያው የ 5 ሰዓታት ውጊያ ነው የነበረው። በኛ ማለትም በወገን በኩል
- 1 ቁስለኛ
- 1 ደግሞ ሞቶብናል

በእምቢተኞቹ በነ አቡበከር በኩል ደግሞ
- 3 ቁስለኞች
- 1 (ምናልባትም 2) ሞተውባቸዋል

ታድያ ይህ ለኛ ድል ሊባል አይችልም። የወገን ኃይል 200፡ እምቢተኞቹ ደግሞ 20 ብቻ እንደነበሩ ስናጤን . . . በምንም ዓይነት መመዘኛ ድል አድርገናል ልንል አንችልም። እርግጥ ነው የቦታው አዳጋችነት ግምት ውስጥ መግባት ይገባዋል። በምጽዋ በኩል ያለውን አስራለቃ ብርኑቺ (ሓኪም)፡ ወደ ውጊያው ቦታ እንዲሄድ፡ የካራቢነሪ ግብጣን ሃይልም ወደ ውጊያው ቀጠና እንዲያቀና ትእዛዝ አስተላልፊያለሁ። ምጽዋ ውስጥ ካሉት የባህር ዳርቻዎችን ከሚጠብቁት ሃይሎችም፡ የአንድ (የመቶ) ሻምበል ሃይል በከፊል፡ ሰገነይቲ ላይ ካሉት ሰራዊታችን የ5ኛው (የመቶ) ሻምበልን አባላት በሙሉ ከነ ሙሉ ትጥቃቸውና ስንቃቸው ውሃም ጭምር ይዘው ወደ ውጊያው ቀጣና እንዲጓዙ ኣዝዣለሁ።” (ማርቲኒ፡ ሲያርዮ 1901፡ ገጽ 498)

ይሄ ሁሉ የጣልያን ሃይል ለውጊያ ሽርጉድና ቡራከረዩ ማለት የደርጉን ሁኔታ ፍንትው አድርጎ ያስታውሰናል። ደርግ በመቶ ሽዎች ከነሚቆጠረው ሰራዊቱ ከነ ሙሉ ትጥቅና ስንቁ፡ እጅግ ጥቂት የሆኑትን የነጻነት ሃይሎች ገጥሟል፤ ታድያ በሃገራዊ የነጻነት ስሜቱ ተቀጣጥሎ የሚዋጋን ሃይል ማን ሊበግረው ይችላል። ጥቂትም ቢሆን በሃገራዊ ስሜት የሚመራ ሃይል ከቶውንም ሊሸነፍ ኣይችልም።


በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 14 - የአቡበከር ሃይል ሰፊ ስብሰባ፡ . . . ሚስቱም ተያዘች” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

TGAA
Member+
Posts: 5624
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by TGAA » 07 Nov 2022, 19:12

Meleket wrote:
21 Oct 2022, 09:44
ይህን ጽሁፍ ወንድማችን Abere በኣማርኛ ተርጉመን፡ ለሰፊው አንባቢ እንድናቀርብ በጠዬቀን መሰረት፡ እነሆ ጀምረነዋል። ከምዚ በሚቀጥለው ክፍል የደራሲውን ትረካ፡ እንደወረደ በተወላገደው አማርኛችን ለማቅረብ እንሞክራለን፡ መጀመርያ ግን በዚህ ጽሑፍ ኣሟሽተነዋል። መልካ ንባብ። :mrgreen:
Meleket wrote:
21 Oct 2022, 04:07
ወንድም Abere፡ እዚህ የምትጽፋቸውንና የምታራምደውን አካሄድ በማዬት፡ ኣንተ ለእውቀት ያለህ ኣመለካከት ሁነኛ መሆኑን ተረድተናል። ኣንዳንድ ሰዎች "እኛ ብቻ እንናገር፡ እኛ ብቻ ነን ሃቀኞች፡ እነ እገሌ ሃሰተኞች ናቸው፡ እኛን ብቻ ስሙ" ብለው ስም ሊያጠለሹ ሲሞክሩ፡ ኣንተ ደግሞ “መናገር የሚፈልግ ይናገር፡ እኛ ደግሞ እንስሶች ኣይደለንም ኣእምሮ ያለን ለባዊ ፍጥረቶች ነንና መርምረን እውነቱን ከሃሰቱ ራሳችን እንለያለን" የምትል፡ ጎበዝ የእውቀት ሰውና የህዝብህ ሁኔታ የሚያንገበግብህ ዜጋ እንጂ “እረኞች ፈቅደው ባሰማሩት ቦታ ብቻ እንደሚግጥ ከብት" ማለትም መናኛ ካድሬ ኣለመሆንህን ተረድተናል። በመሆኑም ለአንተና ያንተ ለሆኑት ሁሉ ክብር የዚህን ጽሑፍ የአማርኛ ትርጉምም ለማቅረብ እንሞክራለን

ጽሑፉን የጻፉት ኣባት ኤርትራዊ የነጻነት ታጋይ ማለትም ሻዕብያና ኣባም ናቸው፡ ኤርትራ ውስጥ በርካታ መጻሕፍት ጽፈዋል ተብለው ከሚጠቀሱት ሰዎች መካከል ኣንዱ እኒህ ኣባት ናቸው። የመጻሕፍታቸው ዝርዝር አርእስት እዚህ ይገኛል https://mereja.com/forum/viewtopic.php? ... 8&start=20 ኤርትራዊው የነጻነት ታጋይ ኣባ ይስሃቅ ገብረኢየሱስ በአንድ የአውሮፓ ዩኒቨርሲቲም ለእውቀት መስፋፋት ያደረጉትን ጥረት በማዬት ይመስለናል የክብር ዶክትሬት ማእረግ ተሰጥቷቸዋል። . . . እንደነ ጥላሁን ገሠሠና ቴዲ ኣፍሮ ወዘተ መሆኑ ነው መሰል።

ይሄኛውን ጽሁፋቸው ያጠናከሩት፡ ከ1897 እስከ 1907 ኤርትራን ‘ያስተዳደረው’ ኢጣሊያዊው ፈርዲናንዶ ማርቲኒ “ዲያርዮ አሪትረዮ፡ አርትራዊ ‘ዜናመዋዕል’” በሚል ርእስ የ10 ዓመታት ዕለታዊ መረጃዎቹን፡ በ4 ትልልቅ ቅጾች በጠቅላላ 2626 ገጽ ባዘለው የ19,300 ዝርዝር መረጃዎችን ከሰነደባቸው መጻሕፍት ውስጥ ቀንጭበው ያቀረቡት ነው።

እንደሚታወቀው በተለያዩ አካላት መካከል፡ ቅዱስ ኪዳን (ቃልኪዳን) ወይ ውል እንዳለ ሁሉ “ዘይቅዱስ” ማለትም ቅዱስ ያልሆነ ኢፍትሓዊ ወይ ርካሽ ኪዳን (ውል) ስምምነትም ኣለ። እንደ እርሳቸው አመለካከት በጣልያንና በምኒልክ መካከል የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ ቅዱስ ያልሆነ ኪዳን ተደርጎ ነበር፡ በማለት በማስረጃ አስደግፈው ለመግለጽ ሞክረዋል። ጽሑፉ ኤርትራውያንን ያለመ ነው። እዚህ መረጃ ላይም በርካታ ኤርትራውያን ይኖራሉ ብለን ስለገመትን፡ ታሪኩን ለማያውቁ ኤርትራውያን ይጠቅም ዘንድ፡ በትግርኛ እንዳለ ለመጋራት እንሞክራለን። ለኢትዮጵያውያን አንባቢዎችም ሊጠቅም ስለሚችልም፡ በጥያቄህ መሰረት በተወላገደው ኣማርኛችን ተርጉመን አዲስ ርእስ በመክፈት እዚያ ለማቅረብ እንሞክራለን። እዚህኛው ክፍል ግን በትግርኛው ትርክት እንቀጥላለን።

ቍምነገሩ፡እነ ፕሮፌሶር ኣፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ሚኒልክን በአንድ በኩል ሲያዩዋቸውና ሲገልጧቸው፡ እነ ታጋይ ዶ/ር ኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ ደግሞ ሰነድ አጣቅሰው፡ ምኒልክን በሌላ በኩል ተመልክተዋቸዋል። የጽሑፉ ዓላማ “ኪዳን፡ ቃል ኪዳን፡ ውል፡ ስምምነት” ቅዱስ መሆን ኣለበት፡ አለበለዚያ ኣንድን የህዝብ ክፍል ወይ ኣንድን ህዝብ ወይም ኣንድን አካል ለመደፍጠጥ የሚደረግ “ኪዳን፡ ቃልኪዳን፡ ውል፡ ስምምነት” ርካሽ ነው ለማለት ይመስላል። ለምሳሌ፡ ኤርትራን ለማጥቃት “ሰንዓ-ፎረም” የተባለ ቅዱስ ያልሆነ ኪዳን በቅርብ ግዜ ነበር፡ . . . አሁንም ተመሳሳይ ቅዱስ ያልሆነ ኪዳን በአካባቢያችንና በቀጠናችን ካለ ለማስተዋል ይበጀናል። . . . ኣንድን ብሄር ኣማራ ሊሆን ይችላል፡ ትግሬም ሊሆን ይችላል፡ ኦሮሞም ሊሆን ይችላል ወዘተም ሊሆን ይችላል ለማጥቃት የሚደረግ የቦለቲካ ፓርቲዎች ሆነ የሃገራት ርካሽ-ኪዳን ኣለ ወይስ የለም? ግለሰቦችን፡ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ እንዳሉት አርበኞችን ወይም ፋኖዎችን ለማጥቃት የተደገሰና የተከወነ የቦለቲካ ፓርቲዎች ሆነ የ ሃገራት ቅዱስ ያልሆነ ኪዳን ኣለ ወይስ የለም? ለማጤን ይጠቅመናል። ወዘተ . . .

ይህንና መሰል ጽሑፎችን ማንበብም፡ አንድን አካል ሌሎች እንዴት እንደሚመለከቱት በመገንዘብ፡ ወደፊት ለሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ውይይት፡ የኔ ብቻ ነው ትክክለኛው ኣመለካከት ከማለት ይልቅ፡ ሌሎችስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? በማለት ይዘቱን ኣብጠርጥሮ በመመዘን፡ በኅሊና በመመራት ሚዛናዊ ግንዛቤን በማጉልበት፡ “ቅዱስ ኪዳን”ን በማበራከት “ቅዱስ ያልሆኑ ኪዳኖችን”ም ለማስተዋል ለመንቀፍም ጭምር በር ይከፍታል ብለን እናስባለን፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
:mrgreen:
Abere wrote:
20 Oct 2022, 10:41
ወደ አማርኛ ብትተረጉምልን ምን እንደተጻፈ፥ ከየት መረጃው እንደተጠናቀረ፤ ለምን እንደተጻፈ እውነት ወይም ሃሰት ስለመሆኑ አግቦ ለመስጠት ለብዙሃኑ አንባብያን ይጠቅም ነበር።
Meleket wrote:
20 Oct 2022, 10:16
ኪዳናት ምንሊክን ጣልያንን ኣብ ምጭፍላቕ ህዝቢ አርትራ (ሰነድ 1897 – 1907) ብኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

ታሪኽ ኤርትራውያን ሓርበኛታት፦
* ደግያት ማሕራይ ኣባሰላማ
* ደግያት ኣቡበከር
* ዓሊ ኑሪ . . .


Meleket , you may have already read it but in case you didn't would you cross-refer to what you wrote here -- whether or not it is complementary to the historical analysis you presented here. Thanks. "No medicine for the bite of a white snake: Notes on nationalism and resistance in Eritrea, 1890-1940 by Tekeste Negash
https://www.academia.edu/40543899/No_me ... _1890_1940

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 08 Nov 2022, 05:32

ወዳጃችን TGAA ስለ ጥቆማህ እናመሰግናለን። ተከስተ ነጋሽ የጻፈውን ለማንበብ እንሞክራለን። አርእስቱ እንደሚያመለክተው፡ የታዋቂውን የደጃዝማች ባህታ ሓጐስ ቅኔ ወይ ግጥም ነው የተጠቀመው። ገራሚው ነገር ብዙዎች ይህን ግጥም ሰንጋል እንደገጠመው መጣፋቸው ነው። ነገር ግን በገጣሚነት የሚታወቁት ባህታ እንጂ ሰንጋል ኣይደሉም።

ተከስተ በኤርትራ የነጻነት ትግል ወቅት፡ ስዊዲን ሃገር ሆኖ ይህን ጽፏል። ተጋዳላይ ኣባ ይስሃቕ ደግሞ በነጻነት ትግሉ ውስጥ በአካል በመሳተፍ "ህይወታቸውን ለነጻነት ትግሉ በመስጠት" አልፈው ይህን ጽፈዋል። የሁለቱም ምልከታ በተወሰነ መልኩ ሊስማም ላይስማማም ይችላል ብለን እንገምታለን። በጥቆማህ መሰረትም ይህን የተከስተ ጥናታዊ ጽሁፍ ይዘት ለመቃኘት እድል ስለሰጠሀን እናመሰግንሃለን። ብላታ ገብረእግዚኣብሄር ዬተባሉትን ኤርትራዊ የጣልያን ቱርጅማን፡ ከሃላይ እስር ቤት እንዳመለጡ ተኸስተ ጽፏል፡ እኛ እስከምናውቀው ግን ደጃች ባህታ ሓጐስ ብላታውን በጣም ይወዷቸው ስለነበር ሰገነይቲ ላይ የነበሩ ጣልያኖችን "ቫቤኔ ባህታ" እስኪሉ ድረስ እያጮሉ ሲያስሩ እሳቸውን እንዳላሰሯቸው ነው።

አሁን ግን ለግዜው ወደ ጀመርነው ትረካ እንቀጥላለን።
:mrgreen:
TGAA wrote:
07 Nov 2022, 19:12
Meleket , you may have already read it but in case you didn't would you cross-refer to what you wrote here -- whether or not it is complementary to the historical analysis you presented here. Thanks. "No medicine for the bite of a white snake: Notes on nationalism and resistance in Eritrea, 1890-1940 by Tekeste Negash
https://www.academia.edu/40543899/No_me ... _1890_1940

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 08 Nov 2022, 05:45

ምዕራፍ 14 - የአቡበከር ሃይል ሰፊ ስብሰባ፡ . . . ሚስቱም ተያዘች

የኤርትራ እናቶቻችን እህቶቻችንና ልጆቻችን በሙሉ በዚህች የጣልያን ዘመን የሳሆ ጀግኒት ሊኮሩ ይገባል። ይህ የኤርትራ ሴቶች ወርቃማ ታሪክ አንድ ምዕራፍና ኣካል ነው።

አስቀድመን እንዳየነው፡ ጣልያን በሁሉም የምስራቅ ኤርትራ ማእዘኖች ያለ የሌለ ሃይሉን ክተት በማለት የነ አቡበከርን የእምቢታ እንቅስቃሴ ለመደፍጠጥ ቢሞክርም፡ የማረካቸውን ቁስለኞች ከማሰቃዬት ያለፈ፡ ቅንጣት ታህል ያፈራው ፍሬ አልነበረም። አቡበከርና እምቢተኛ ጓዶቹን ለማደን የተካሄደው የጣልያኖች ልፋት ግን ከንቱ ሆኖ ቀረ።

እስቲ ራሳቸውን ለማጽናናት፡ የዚህ መጠነ ሰፊ የማጥቃት እርምጃቸውን አስመልክቶ ግብጣን ክራቨሪ ወደ አስመራ የላከውን መልእኽት እንመልከት

“የዖኖኽባ ቀጠና፡ ሰኔ 26 በ21ኛው ሰዓት። ትላንት ፍሬ ያፈራ አሰሳ አድርገናል። በተለያዩ ቦታዎች የደም ጠብታዎችን አይተናል። ከውጊያው ስፍራ እስከ አንድ ገደል ድረስ የደም ነጠብጣቦችን ዱካ አግኝተናል። ከዚህ የደም ጠብታ በስተቀር ያገኘነው ነገር ግን የለም። ዛሬ በዚያ ለዥንጀሮ እንኳን በማይመች ብርቱ ገደል ውስጥ አንድ የሞተ ነገር እንዳለ የሚያመለክት መጥፎ ሽታ እየሸተተ ነው።

ያ ትላንት የቆሰለው የ7ኛ የሻምበል አባላችን ሞቷል። ትላንት ቆስላ የተያዘችው ሴትዮም፡ የአቡበከር ሚስት መሆኗን አምናለች። ባሏ በዚያ ብርቱ በሆነው ‘አደላራበ’ በተባለው ስፍራ፡ ለተከታዮቹ ሁሉ የስብሰባ አዋጅ አስነግሮ እንደነበረም ገልጻለች።

ረዳትና ድጋፍ እንዲያደርግልን የተጠቀየው ሰራዊት ከደረሰልን፡ እምቢተኞቹም በተባለው ስፍራ ለመሰብሰብ ከመጡ፡ ልንይዛቸው እንሞክራለን። ይህ ካልተሳካልን ግን፡ ክቡርነትዎ ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክርዎን ይለግሱልን። ስንቅ በጣም አጥሮናል። አብዛኛውን ግዜ ከህዝቡ በመውሰድ ነው የምንመገበው
” በማለት ይገልጣል ግብጣን ክራቨሪ።

ግብጣን ክራቨሪ ምንም እንኳ ፍሬ አልባ ስለነበረውና መቅበዝበዝ ይታይበት ስለነበረው ተልእኾው መልእክት ወደ አስመራ ቢልክም፡ ተግባራቱ ሁሉ “ራስ ሳይጠና ጉተና” እንዲሉ ሁኗል። የስብሰባ ቦታ የተባለው አልተገኘም፡ እምቢተኞቹም ለስብሰባ አልተገኙም። በመሆኑም መልእኽቱን እንዲህ በማለት ይደመድማል፡-

“ ትላንት 9:00 ሰዓት ላይ ‘እምባ ጃውጉደ” ከተባለው ተረተር ስወርድ፡ አምስት እምቢተኞች ተኩስ ከፈቱብኝ። መንገድ ይመራኝ የነበረው የሳሆ ሰውም ታፋው ላይ ቆሰለ። እኛም ተኩሰንባቸዋል። ነገር ግን ምንም ፋይዳ አላገኘንበትም። ከሽመዛና ታጣቂዎች መካከል የቆሰሉት ግን ደግሞ ያልተጠሩት፡ በአስር አለቃ ድሮሲ ስር ይሁኑ። ቁስለኞች ሁሉ ወደ ሃኪም እንደደረሱ ደግሞ ተስፋ አደርጋለሁ።” ግብጣን ክራቬሪ (ማርቲኒ፡ ከማሁ)።

ራሱ ማርቲኒ ሳይቀር ስለ 4ቱ የጣልያን ቁስለኞችና ስለ 1 ሟች ወታደራቸው ቢጠቅስም፡ አስቀድሞ “ከነ መቆፈሪያቸው ይምጡ . . . ወዘተ” በማለት የገለጸበትን ሁኔታ ዳግም ስንመለከት፡ የጣልያን ወታደሮች እንደ ቅጠል ይረግፉ እንደነበር ለመገመት ኣያዳግምት። ይህ ሁሉ ሲሆን አሁንም አሁበከር አልተገኘም!

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 15 - አጉራዘለልነት በትግራይ - አቡበከርና ድብቅ ስፍራው” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 09 Nov 2022, 02:27

ምዕራፍ 15 - አጉራዘለልነት በትግራይ - አቡበከርና ድብቅ ስፍራው

ጣልያኖች እምቢተኞቹን እነ አቡበከርንና ጓዶቹን ለማደን መጠነ ሰፊ ዘመቻ ማካሄዳቸውን አስቀድመን አይተናል። ጣልያኖቹ በሰላማዊው ህዝብ ላይ ምን ዓይነት ግፍን ፈጽመው ሊሆኑ እንደሚችሉም፡ ምንም እንኳ በዘገባቸው ባይገልጡትም ፡ የጣልያኖችንና የማንኛውንም ገዢ ሃይል እኩይ ተግባርና አሰራርን ጠንቅቀን ለምናውቀው ለኛ፡ ምን ዓይነት ግፍ እንደፈጸሙ ለመገመት ያዳግተንም። አርበኛውን አቡበከር በተመለከተ፡ ጣልያኖች አሁንም መረጃ ከማሰባሰብ ውጪ ምንም ሊያደርጉ አልቻሉም ነበር። እስቲ የሚከተለውን መረጃ ከደብተራቸው እንቀንጭብ፦

“ ሰኔ 30 ። ከትግራይ የተላከ መረጃ። በደጃዝማች ገረስላሴና በደጃዝማች ተፈሪ መካከል ውጊያ ተከፍቷል። መንገሻ የተፈሪ ደጋፊ ሲሆን፡ አማራው ንቡረእድ ደግሞ የገረስላሰ ደጋፊ ነው። አይቀሬ ብርቱ ውጊያ'ማ ኣለ፡ መበጣበጣቸውና እርስበእርስ መናቆራቸው የተረጋገጠ ነው። ብቻ የተለግራፍ መልእክት መስመራችንን ኣይንኩብን እንጂ፡ ሚማማሩ ኣይመስሉም።


“ከዓሳዎርታ የተላከ መረጃ። እንደ የዓሳዎርታ ኗሪዎች አባባል፡ “እምቢተኛው አቡበከር፡ አንድ መግቢያ በራፍ ብቻ ባለው “ሳብራ” በተባለው መደበቂያ ምሽጉ ውስጥ ሊኖር ይችላል። አቡበከር እንደሆነ “ሳብራ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ቦታ ላይ ላለመሞት ምሏል” ብለው ያምናሉ፤ ይላል ኣሁንም ግብጣን ክራቨሪ። ይህ ቅጥረኛ ግብጣን ክራቨሪ፡ ጌታውን ለማስደሰት በተቻለው ሁሉ እየተፍጨረጨረ፡ አቡበከርን ለማደን ያለ ያሌለ ወታደራዊ ችሎታውንና አንጎሉን ለመጠቀም ቢሞክርም፡ ለግዜው ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ፍሬ እንዳላፈራ ተገንዝበናል። ኣመሻሹ ላይስ፡ አቡበከርን ይያዘዋል ወይስ ይገድለዋል፡ የሚከተለው ምዕራፍ ላይ እስቲ እንከተለው።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 16 - አቡበከርን ለመያዝ አዲሱ ዘመቻ፡ የህዝብ አጋርነት ግን ለአርበኞቹ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:


Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 09 Nov 2022, 04:21

ታለሜ ህክምናሽን እዚህ ሄደሽ እንድትከታተዪ ምክራችንን እንለግስልሻለን https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308644 እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። :mrgreen:
Fiyameta wrote:
09 Nov 2022, 03:26
Meleket is AGAME JUNTA!
አደራ የማይከፈልበት ህክምና ነው፡ እንዳያመልጥሽ ተጠቀሚበት፡ እዚ'ጋ https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308644

አሁን አትረብሽ፡ ተጋዳላይ ዶ/ር ኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ የጻፉልንን ኤርትራዊ ታሪክ በመዀምኮም ላይ ነን፤ ደስ ካላለሽ ምን ይደረጋል 'ኮሎነል ታሪኩ' የጻፉትን ታሪክ ፈልገሽ አንብቢ እንጂ ታለሜ፡ እሱም ካለ ነው!

ሌላው ደግሞ እስቲ ከቻልሽ ለኢሳቶች ይቺን መልእኽታችንን እንዲያስተላልፉልን ንገሪልን ለነ ሲሳይ፡ ፋሲልና ወዘተ "ፊዚካል ዲማርኼሽን አሁኑኑ" እያልን ነው፤ ይመችሽ ይሆንን ወይስ እሱም እንደ ተጋዳላይ ዶ/ር ኣባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ ጽሑፍ ሽቅብና ቁልቁል ያስብልሽ ይሆንን፧ ያንቺ ነገር እኮ ኣይታወቅም! https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308353
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 10 Nov 2022, 04:04

ምዕራፍ 16 - አቡበከርን ለመያዝ አዲሱ ዘመቻ፡ የህዝብ አጋርነት ግን ለአርበኞቹ

ግብጣን ክርቨሪ አቡበከርን አድኖ ለመደምሰስ ያደረገው ጥረት ሁሉ መና ቀርቷል። ነገር ግን አሁንም አሁንም የበላዮቹ እያዘዙት ነው።

በመሆኑም ግብጣን ክርቨሪ አዲስ የዘመቻ ዕቅድ ለማውጣት ተገዷል። በዚህ እያቀደወ ባለው አዲስ ዘመቻ ምን ያህል ሰላማዊ ሰዎችና ንብረት ሊወድም እንደሚችል አልታወቀም። ሰኔ ሰላሳ ከንጋቱ 1 ሰዓት ላይ ወደ ማርቲኒ የተጻፈው የግብጣን ክሪቨሪ መልእኽትን እስቲ እንመልከት፦

የአቡበከርን እንቅስቃሴ በተመለከተ ምንም ዓይነት የተረጋገጠ መረጃ ለማግኘት አልተቻለም። ‘ነሪ’ የሚመራው ሃይል፡ ትላንት ‘ባስጣፍ’ በተባለው ስፍራ ስለደረሰ፡ ዛሬ ሌሊት አዲስ መረጃ ከተገኘ፡ አዲስ የአደን ተልእኾ ለማድረግ እንሞክራለን።

ይህም ካልተሳካልን፡ ክቡርነትዎም ሌላ መመሪያ ካልሰጡን
-‘ጉወሊ’ የሚመራው ኃይል ወደ ኢራፋለ፡
- ‘ኣሎሪ’ ወደ ምጽዋ፡
- ባንዳዎቹ ወደ ሰንዓፈ
- ‘ኩነታ’ ወደ ዓድቐይሕ
- ‘አንድረይኒ’ም ወደ አስመራ መንገዶች ማለትም በሚጠረጠረው ሁሉ እንዲሰማሩ አደርጋለሁ።

- የነሪ ሃይል እና
- አስር አለቃ ቦርሳሬሊ ደግሞ
ዋንኛ የዖኖኸባን ቀጠናዎችና የኣላምቦን ሜዳማ ስፍራዎች እንዲሁም የኩመይለን የውሃ ጉድጓዶች እንዲቆጣጠሩ ይደረጋል። በተጨማሪም በ 15 ሰዎች የተዋቀረ ተወርዋሪና ተጠባባቂ ሃይልም ይኖራቸዋል።

“ለግዜው እኔ፡ ዕቅዳችንን እንደ አዲስ ለክቡርነትዎ አስረዳ ዘንድ ወደ አስመራ እመጣለሁ። እስከ አሁን ድረስ በርካታ የአቡበከር መደበቂ ምሽጎች ያልናቸውን ፈትሸናቸዋል ደምስሰናቸዋልም።

“ ‘ፈቓት ሓርክ የተባሉት ‘ሚነፈረ’ዎች ግን በዚህ የአደን ዕቅዳችን ውስጥ በፍጹም ወደው በፍላጎታቸው አልተሳተፉም። ከ “ዓሳሊሰን” የተባሉት ህዝቦችም ለድጋፍና ለረዳትነት እንኳ አንድም ሰው አልተቀላቀለንም።” (ማርቲኒ ዲያርዮ 1901፡ ገጽ 505 ።)

‘አስተዳዳሪው’ ማርቲኒ ይህ የግብጣን ክራቨሪን መልእኽትና ዘገባ እንዳነበበ በጣም ተገርሟል። ተስፋ ቆርጦም እንዲህ በማለት በደብተሩ ላይ ከትቧል፦

ወይ ጉድ!! ከአቡበከር ጋር ደም ተቃብተዋል የሚባሉት ‘ፈቓት ሓረኽ’ እንኳ ይህንን ዕቅዳችንንና ዘመቻችንን ካልደገፉት ታድያ . . . ከህዝቡ ድጋፍ መጠበቅ ማለት በፍጹም የማይመስል ከንቱ ድካም ነው ማለት ነዋ! . . . እስቲ አዲስ የተባለውን የዘመቻ ዕቅድ ደግሞ እናየዋለን። የአከለጉዛዩ ‘አስተዳዳሪ’ አንድ አዲስ መረጃ አግኝቻለሁ እያለ ነው። እንደ አባባሉ ከሆነ፡ ለአቡበከር ተብሎ የተላከ መሳርያ ‘ጎባይ’ በተባሉ ደሴቶች ውስጥ ተወሽቆ ተቀምጧል። ዛሬውኑ ይህንን የሚከታተሉ ሰዎችን እንልካለን እያለ ነው።” (ማርቲኒ ድያርዮ 1901፡ ገጽ 505)።

ማርቲኒ፡ የኤርትራ ህዝብን ጠባይ እና ምስጢር ገና አላወቀውም፤ በተለዪም የሳሆ ህዝብ ጠባይ ገና ኣልገባውም ማለት ነውን? ባዕድ ይደሰት በማለት ወንድሙን አሳልፎ የሚሰጥ ህዝብ ይመስለዋልን? ኧዬ ማርቲኒ . . . በአቡበከርና በ’ፈቓት ሓረክ’ መካከል ጠብና ደመኝነት በመኖሩ፡ አቡበከርን የማደን ዕቅዴ ይሳካልኛል ብሎ አስቦና ተስፋ አድርጎ ነበር። ነገር ግን ልጆቹን አሳልፎ የማይሰጠው የ’ፈቓት ሓረክ’ ሚኒፈረ ህዝብ ማርቲንና ለአደን የተሰማራውን የጣልያን ሃይል ባጠቃላይ ‘አፍንጫችሁን ላሱ’ አላቸው።


በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 17 - የአዳኞች ከንቱ ልፋት - የማርቲኒ ንጭንጭ - ህዝቡ ከሽልማት ይልቅ አርበኞቹን መምረጡ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 11 Nov 2022, 01:34

ምዕራፍ 17 - የአዳኞች ከንቱ ልፋት - የማርቲኒ ንጭንጭ - ህዝቡ ከሽልማት ይልቅ አርበኞቹን መምረጡ

ጣልያኖች፡ ዓሳውርቶችን በተለይም ፈቓት ሓረክን፡ ይተባበሯቸው ዘንድ በብዙ ተስፋዎች ለማማለል ሲፍጨረጨሩ ታይተዋል። ፈቓት ሐረክ ግን፡ ከጣልያኖች የማማለያ ሽልማት ይልቅ፡ የሃገራቸውን አርበኞች ስላፈቀሩ፡ በጣልያኖች ማባበያ አልተታለሉም። ማርቲኒም በዚህ ተግባራቸው ተናዶ በመነጫነጭ፡ ሀምሌ 2 ዕለታዊ ፍጻሜዎቹን በሚያሰፍርበት ጥራዙ እንዲህ ሲል ጣፈ፦

“አስቸጋሪውንና ማለፊያ የማይገኝለትን ያን ገደላማ ስፍራ፡ ትንስም ብትሆን መተላለፊያ መንገድ ቢገኝባት በማለት አሰሳው ቀጥሏል። የ ‘ዲ ኢሎሪ’ ኃይልም ቦታውን ሁሉ ዳስሳለች። እርባና ግን ኣልተገኘበትም . . . የፈቓት ሓረኽ መሪዎች ከመንግስት ሊሰጣችው የታሰበን ሽልማት ችላ በማለት ከኛ ጋር ትብብር ከማድረግ “አሻፈረን” ብለዋል።

“ ‘ሳድም’ በተባለው ጠባብ መንገድ ብቻ ባለው ገደላማ ስፍራ፡ በወሩ በ28ተኛው ቀን፡ ሁለት በሬዎችን እየነዱ ይሄዱ የነበሩ ታጣቂዎች ታይተዋል። ተኩስ እንደተከፈተባቸውም፡ መሬት ላይ በመተኛት ከለላ ያዙ! ከዚያም በሬዎቻቸውን ትተው አምልጠዋል። በሬዎቹ የኣአቡበከር መሆናቸው ተረጋግጧል።
- ክራቬሪ”።

“ ያ ሁሉ የተኩስ እሩምታ! እምቢተኞቹ ግን አሁንም አልተያዙም ዝምብለው ያመልጡናል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ፡ በጣላያን ጋዜጦች ላይ እየተጋነነም የሰፈረውን ለማዬት ባልችል ኖሮ፡ ብዙም ባላስጨነቀኝ ነበር። የጣልያን ጋዜጦች፡ ይቺ ግዛታችንን በተመለከተ ሲዘግቡ ሊደፈጠጥ ባልቻለ ተቃውሞ የምትናጥና ያልተረጋጋች በስቃይ ላይ ያለች ኣንደሆነ አድርገው ነው የሚያቀርቧት። ይህ ደግሞ በጣልያኖች ዘንድ የሌለ ፍራትንና ስጋትን ነው የሚያሳድር።” (ማርቲኒ ዲያርዮ፡ 1901 ገጽ 505 ።)

እዚ ላይ ማርቲኒ ሳይታወቀውም ብዙ ሐቆችን አፍረጥርጧል። የኤርትራ ህዝብ ተቃውሞ አውሮፓ ውስጥ ሃገረ ኢጣልያ ድረስ ይሰማ ኖሯል ለካ! ይህም በበኩሉ፦

“የኤርትራ ህዝብን ድምጥማጡን አጥፍቶ በመደምሰስ፡ ገጠሩንም ሳይቀር በጣልያን ገበሬዎች በመሙላት፡ አንድ በጣልያን ገበሬዎች የተዋቀረ ማሀበረሰብ ኤርትራ ውስጥ መመስረት” (የመርማሪ ኮሚሽን አጠቃላይ ሪፖርት 1891፡ 204) የሚል እኩይ ዓላማቸውን የሚያደናቅፍ ነበር። የጣልያን ህዝብም ምንም እንኳ ኳኩለውም “አርትራ” የሚል ቃል ሲያነሱበት፡ ይደነግጥና ይርድ ይርበደበድም ነበር። በመሆኑን ስፍር ቁጥር በሌለው ማባበያና ተስፋዎች እያሞኙ ወደ ኤርትራ እንዲጎርፍ አድርገዋል።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 18 - የጣልያን ወታደሮች ደፈጣ - የድኾኖ በሌሊት መጠቃት - የአቡበከር ህላዌ ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 15 Nov 2022, 05:02

ምዕራፍ 18 - የጣልያን ወታደሮች ደፈጣ - የድኾኖ በሌሊት መጠቃት - የአቡበከር ህላዌ

ጣልያኖች አዲሱን የዘመቻ ውጥናቸውን ለመተግበር ሞክረዋል። ነገር ግን አሁንም ፍሬ አልባ ነበሩ! ያ በስንት የሃሳብ ፍትጊያ ያረቀቁትና ያጠኑት የደፈጣ ትልምን እንዳዲስ ለሁለተኛ ግዜ ለማዘጋጀት ረዠም ያለ ግዜ እንደሚፈጅ አውቀዋል። በተለይም አስር አለቃ ክራቨሪ በብርቱ ቁጣ፡ ህልክ ውስጥ የገባ ይመስላል።

ሳይወድ በግዱ የሳሆ አርበኞችን ጀግንነትና ብልህነትም ገልጿል። “ሓላይ” ከተባለው ቀየ የነበረው ወታደራዊ ካምፕ የተጻፈ አንድ መልእኽት ኣንዲህ ይነበባል፦

“ሓላይ፡ ሓምሌ 7 ። ግብጣን ክራቨሪ ከ “ዖኖክባ” የላከውን መልእኽት ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ። ከክቡርነትዎ ጋር መወያየት ሳያስፈልገግኝ አይቀርም። ይህ ካልሆነ ግን ዓሳውርታን በፍጹም አልለቅም። ምክንያቱም፡ ተልዕኾየን በማንኛውም ሁኔታ ከማሳካት ባለፈ፡ ከዓቡበክር ጋር ገና ያልተወራረደ ሂሳብ አለኝ። ስለሆነም ነው አንድ መንገድ መሪና ሁለት ወታደሮችን ይዜ ይህን መናጢ ለማደን አሁንም አሁንም በየቦታው እየተዟዟርኩ ያለሁት።

ሰኔ 25 ላይ በጥንቃቄና በብልህነት ከተከናወነው የደፈጣ ውጥን በኋላ፡ እምቢተኞቹ መሬታቸው ስለሆነና ከኛ በላቀ ሁኔታ የመሬታቸውን መግቢያና መውጫውን ጠንቅቀው ስለሚያውቁት፡ ተበታትነው ለማምለጥ በመቻላቸው ውጥናችን አልተሳካም። አሁንም ያን የመሰለ እምቢተኞቹን የማደን የደፈጣ ውጥንና ወጥመድ ለማከናወን እጅግ ከባድ ነው። በአሁኑ ወቅት፡ ደከናሞ (ድኾኖ ወይም ሕርጊጎ) ላይ አስር አለቃ በርንርዲ ላይ በሌሊት ጥቃት ሲፈጸም ተባባሪ የነበሩትን ሁለት የ”ዲዖት” አካባቢ ልጆች የሆኑ የአቡበከር እረኞችን በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል። እነዚህ ልጆች፡ ለአምስት ቀናት ወደ “ዅመይል” አቅጣጫና በ “ዲዖት” ተራሮች ላይ አሰሳ ሲያደርግ የነበረው አስር አለቃ በርሳረሊ የቀፈደዳቸው ናቸው። አቡበከር ከነ 10 ታጣቂዎቹ በዚህ በተጠቀሰው ተራራ ሳይኖር አይቀርም። የጀሌዎቹን ስም ሚስቱ ነግራናለች። አሁን አሁን እንኳ እየተሻላት ነው። - አስር አለቃ ኪቲተሊ (ማርቲኒ፡ ዲያርዩ 1901፡ ገጽ 513)

ቆስላ የተያዘችው የአቡበከር ሚስት ነገረችን ይበሉ እንጂ፡ ከስንትና ስንት ስቃይ ካደረሱባት በኋላ መሆኑስ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለበትም። አቡበከርን በተመለከተ’ስ?

“ከሰንዓፈ ‘ሙላሳኒ የላከው መልእኽት። ከመቐለ በ “ማራንጊ (መረንጊ)” የተላከ መልእኽት እንዲህ ተነግሮኛል። ደጃዝማች ሓጐስ ሸሽቷል የሚባለው ውሸት መሆኑ ይገመታል። . . . እንደምናየውም (እንደሚባለውም) አቡበከር በ1902 ተሰውቷል ማለት ነው።

ማርቲኒም በበኩሉ በተደጋጋሚ “በውጊያ መኋል ወደቀ፡ Caduto” ማለቱን ስናስተውል፡ ለአቡበከር ጀግንነት ያለውን አክብሮት ያሳየናል። አቡበከርን ወገኖች ሳይቀር ፡ “አቡበከርን ያፈራ ግዙፍ ጎሳ ወይ ነገድ” በማለት ይጠቅሳቸዋል። ምንም እንኳ ማርቲኒ ባዕዳዊና የገዢዎች መሳርያ ቢሆንም ቅሉ፡ ኣንደ አንድ ምሁር መጠን የሰዎችንና የሃገርን ክብር በደንብ የሚያውቅ ሰው ነበር። ከኤርትራዊው አርበኛ አቡበከር ጋር፡ በዚ አጭር መረጃ አማካኝነት፡ ለግዜው እንለያይ።



በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 19 - ጀግኖች አባቶች!!! 'አንድም ፍቷቸው አልያም እናጠቃለን' ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 29 Nov 2022, 03:27

ምዕራፍ 19 - ጀግኖች አባቶች!!! 'አንድም ፍቷቸው አልያም እናጠቃለን'

የሳሆ ኣባቶች ለወራሪው ጣልያን የነበራቸው ጥላቻና ለመመከት ያካሄዱት የትግል ወኔና መንፈስ ገደብ አልነበረውም። የምትከተለውን ለ ‘አስተዳዳሪው’ ለማርቲኒ ‘ሰቲት’ እስከተባለው ስፍራ የተከተለችውን አንዲት የጀግኖች አባቶች መልእኽት እስቲ እንመለከት። ይህን መልእኽት ያስተላለፈው በዚያን ወቅት በ ‘አስር ኣለቃ’ ማዕረግ የጣልያንን መንግስታዊ አደረጃጀት እያገለገለ በዚያውም ህዝብ ተኰር ጥልቅ ጥናቱንና ምርምሩን ያካሂድ የነበረው እውቁ ሊቅ ካርሎ ሮሲኒ ነው።

“ሚያዝያ 20፡ ሲቶና (ሰቲት)። አንዲት መልእኽት ከ’ሚዳ’ ወደ መንግስት አመራሮች ተላከች። የመልእኽቷ ጸሓፊዎች፦ የዓሳሊሳው ዑስማንና አሕመድ አድም ናቸው። እንደነሱ ኣባባል “ናዅራን ያጠቃናት እኛ ነን” ይላሉ። ‘ከርበብ’ በተባለው ስፍራ የተማረከው የጎሳችን መሪና የአቡበከር ተከታዮች ካልተፈቱ፡ አሁንም አሁንም የማጥቃት እርምጃችንን እንቀጥልበታለን እያሉ ነው። ኮንቲ ሮሲኒ” (ማርቲኒ ዲያርዮ 1902: 575)።

ጣልያኖች ጉድ ነው የሆኑት። ኤርትራውያን መውጭያ በሌለው ደሴት ውስጥ ታስረውም፡ አጥቅተው ሰንሰለት በጥሰው እየወጡ ነው። እንደ አዲስም “ኣሁንም እናጠቃለን” እያሉ ነው። ለመሆኑ የዚህ የማጥቃት እርምጃ መሪዎችና ኣቀናባሪዎች እነማን ናቸው? የአቡበከር ስር እንደሆነ መጨረሻ የለውም።


ቀስ በቀስም ካርሎ ኮንቲ ሮሲኒ፡ ስለ ጀግኖቹ የአቡበከር ደጋፊዎች ማንነት አንዳንድ መረጃዎችን አቅርቦልናል። የሚከተለው መልእኽትን (በ21-4-1902: ዲያርዮ ገጽ 577) እንደተቀበለም ‘አስተዳዳሪው’ ማርቲኒ እንዲህ ሲል አሰፈረ፦ “ወደድንም ጠላንም ናኵራን በተመለከተ ተጨባጭ መልኽእት ነው የደረሰን” በማለት ማርቲኒ “የደረሰን መልእኽት”ና “ወደድንም ጠላንም” “በማለት ያቀረበው መልእኽቱ እንደወረደ እንሆ፦

“ሳልቫደይ ኣሎሪ ባገኘው መረጃ መሰረት፡ ይህን መልእኽት የጻፉት ሰዎች፦
- አሕመድ ኣድም እድሜው 40 ዓመት እና
- የሑመድ ዲሩዓ ዓሳሊሳን ጎሳ ተወላጁ የ30 ዓመቱ ዑስማን ናቸው። ሁለቱም እድገታቸው “ሕጡምሎ” በተባለው ቀዬ ነው። በ1888 መኖርያ ቤታቸውን ተወርሰው፡ እንደሰርቶ ማሳያነት የሚያገለግል የእርሻ ሙከራ በማድረግ ስፍራቸው በሙሉ ታረሰ። ከዚህም በኋላ ከኣባታቸው ጋር ‘ሕርጊጎ’ ወደ ተባለች ቀየ ተቀየሩ። በ1895 እንደ አዲስ አሁንም ወደ ቀድሞ ቀያቸው ወደ “ሕጡምሎ” ተመለሱ። በ1898 ንብረታቸውን ሁሉ በመሸጥ ወደ ዓረብ ሃገር ተሰደዱ። በ1900 ኣህመድ መሳርያ ጭኖ በደንከልያ በኩል ወደ ሳሆ ምድር ወደ ዓሳዎርታ ተመለሰ። ታሕሳስ 11 1900 “ከርተት” ላይ በተደረገው ውጊያም፡ ከአቡበከር ተከታዮች ጋር በመቀላቀል ተሳተፈ። ከዚያ በኋላም እንደገና ተመልሶ ወደ ዓረብ ሃገር ሄደ። አቡበከር አልሄድም ስላለው እንጂ ከእርሱ ጋር ወደ ዓረብ ሃገር ሊወስደው ጋብዞት ነበር። በ 1901 እኒህ ሁለት ወንድማማቾች አስቀድሞ የተጠቀሰውን መሳርያቸውን ለአቡበከር ላኩለት . . . ኑሪ ወደ ትግራይ ሸሽቷል። - ኮንቲ ሮሲኒ” (ማርቲኒ ዲያርዮ 1902፡ ገጽ 577)

ናዅራን ያጠቃ፡ እስረኞችን ከዚያ የህያዋን ገሃነብ ተብሎ ከሚታወቀው እስር እንዲያመልጡ የሚያግዝ፡ አሁንም ዳግም እንደሚያጠቃ በግልጽ የሚናገር፡ መሳርያ ከባህር ማዶ ወደ ኤርትራ የሚያስገባ፡ ውግያ ውስጥ የሚሳተፍ . . . ታድያ በዚያን ወቅት የጣልያኖችን አገዛዝ የሚቃወም ከዚህ የበለጠ ከህዝብ ጋር የተሳሰረ እምቢታና የትግል ስሜት ምን ልናገኝ ነው? አርበኛውን አቡበከር በተመለከተ ከአሁን በኋላ ብዙም አንሰማም። አቡበከር ከጣልያን ሰራዊት ላይ ያካሂድ በነበረው ደፈጣዎች መካከል እንደተሰዋ ከአንዳንድ ትንንሽ መረጃዎች ልንገነዘብ ችለናል። ፈርዲናንዶ ማርቲኒ፡ ለመጀመርያ ግዜ የአከለጉዛይና የሳሆን ምድር በዳሰሰበት ወቅት፡ እንደ ልማዱ የረገጠውንና የዳሰሰውን ታሪካዊ ስፍራ በተመለከተ መዝገቡን አውጥቶ ዝክሩን አስፍሮበታል። አቡበከርን ባፈለቁት የዓሳሊሳን ጎሳ በኩል ታሕሳስ 10 1904 ባለፈበት ወቅትም እንዲህ ሲል በመዝገቡ ትዝብቱን አስፍሯል ፦

“ ‘ሱሩ’ ላይ ጀግኖቹ ዓሳሊሳኖችን አግኝቻለሁ። ዓሳሊሳን፡ አቡበከርን ያፈለቀ ትልቅ ነገድ ነው። አቡበከር ከሁለት ዓመታት በፊት በጦርነት ተሰውቷል። . . . በ1900 “ሓሊለየ” ላይ “ሓላይ” ከተባለው ቀየ በተነሱት ካራበቢነርና ተቃዋሚዎችን መካከል ውጊያ ተደርጎ ከሁለቱም ወገኖች አንድ አንድ ሰው ሞቷል። . . . “ሰርዓ ደግዓ” ላይም ከ12 ዓመታት በፊት፡ በባንዳዎች በተዋቀረው የፊናንስ የብርጌድ ሃይልና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ ነበር። ከሁለት ዓመታት በፊትም በዚያው ቦታ፡ የአቡበከር ተከታዮች ጥቃት ፈጽመዋል። ከሁለት ዓመታት በፊትም “ባጋለ ዓሊተና” በተባለው ስፍራ፡ የአቡበከር ተከታዮች ፡ ወደ “ዳካናሞ” ያቀኑ የነበሩትን የንግድ ከንቮዮች ይጠብቁ የነበሩ ሰራዊትን አጥቅተዋል። ከሁለት ዓመታት በፊትም፡ “ድኮኖ” በተባለችው ቀየ ተመድበው በነበሩ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። . . . ‘ማይ ፍላሕ’ በዚያን ወቅት ታዋቂ ነበር። . . . አቡበከር እዚያ ነው በውጊያ መካከል የተሰዋው። ‘ሱሩ” ልክ ከ“ጉበነ” ጋር በሚቀላቀልበት ስፍራም፡ ተቃዋሚዎች የሚሰባሰቡበት ስፍራ ነው። ዓሳውርታውያን ሓዞዎች ደብሪ መላዎች እና ሚነፈሪዎች እዚያ መሰብሰብያቸው ነው። “ሱሩ” በ1867 መቅደላን ያጠቁት እንግሊዛውያን ያለፉባት ስፍራ በመሆኗ በአውሮፓዊ ታሪክ ውስጥም ትታወቃለች። “ኡኑከቱ”ም ለግዜው የእምቢተኞቹ መሰብሰብያ ስፍራ ነበር። ከሁለት ዓመታት በፊት አቡበከር በዚያ ታይቶ ነበር፡ ወዲያውም በውግያ መሃል ተሰውቷል። (ማርቲኒ ድያርዮ 1904፡ ገጽ 10-11)

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 20 ምንሊክ ኤርትራውያንን ይደግፉ የነበሩ የትግራይ ሰዎችን ያስር ነበር” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 12 Dec 2022, 09:24

ምዕራፍ 20 ምንሊክ ኤርትራውያንን ይደግፉ የነበሩ የትግራይ ሰዎችን ያስር ነበር

የምንሊክ ህልውና በቀጥታ ጣልያን በኤርትራ ከሚኖራት ህልውና ጋር የተያያዘ ነው። የጣልያን በኤርትራ የሚኖራት ህልውና ሊረጋገጥ የሚችለው፡ ማንኛውም የኤርትራውያንና የተባባሪዎቻቸው ተቃውሞ ሲደመሰስ ብቻ ነው። ጭቁን ህዝቦች ከመሰል ጭቁን ህዝቦች ጋር መተባበራቸው አይቀሬ በመሆኑም፡ ትግራይ ውስጥም የምንሊክ አገዛዝ ያስመረራቸው፡ የአጋሩ የጣልያን ጉሽሚያም ያንገሸገሻቸው ሃይሎች፡ ጣልያንን ይቃወሙ ከነበሩት ኤርትራውያን ጋር አይተባበሩም ነበር ለማለት በፍጹም ኣይቻልም። እስኪ የሚከተለውን መረጃ እንመልከት፦

“ከዓዲኳላ የተላከ መረጃ እንደሚገልጸው፡ ባሳለፍነው ሳምንታት ከኛ ጋር ሰላምታ ተለዋውጦ የነበረው ደጃዝማች ገረስላሰ፡ አንድ መረጃ ልኮልናል። ገረስላሰ ራሱ፡ (የአሕስአው አስተዳዳሪ) ግራዝማች ኣበራ አርአያን በመማረኽ ተግባር ላይ ተሳትፏል።

አበራ ኣርኣያ፡ የመሓመድ ኑሪና ወደ ትግራይ የተሻገሩ ሌሎች እምቢተኞች ዋናውና ረቂቁ ደጋፊያቸው ነው። ስለሆነም የአበራ መታሰር እጂግ ወሳኝ ነገር ነው።

“በንጉስ ትእዛዝም ሌላ ተጨማሪ ለውጥ እየመጣ ነው።
ከአበራ (አብርሃ) መታሰር በኋላም ማንኛውም የመሓመድ ኑሪ ተስፋዎች ከንቱ ይሆናሉ።” (ማርቲኒ ዲያርዮ፡ 1902፡ 33።) ለውጥ ብሎ ዝም ነው! . . . እከክልኝ ልከክልህ እስከመቼ ይሆን? ንጉስ ምኒልክ፡ በትግራይ ደንበር አካባቢ ሆነው የጣልያንን አገዛዝ ይቃወሙ የነበሩ ኤርትራውያንንና ትግሬ ደጋፊዎቻቸውን ማሳደድ ሲጀምር፤ ዓሊ ኑሪ’ስ ዝም ብሎ ይጠብቀዋልን? ወደ ኤርትራ ለመግባትስ ምን ሊያግደው ይችላል? የሚከተለውን መረጃ እስቲ ምን እንደሚል እንመልከት፦


በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 21 - መሓመድ ኑሪ ሌላው የሳሆ አርበኛ” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 19 Dec 2022, 09:29

ምዕራፍ 21 - መሓመድ ኑሪ ሌላው የሳሆ አርበኛ

ባለፉት ገጾች 2-3 ግዜ የሳሆውን አርበኛ መሓመድ ኑሪን ጠቅሰነዋል። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ስለዚህ አርበኛ ያለን ዕውቀት ብዙም አይደለም። የአሁን ይሁኑ የድሮ ጠላቶቻችንን በሙሉ፡ ታሪካችንን ለመቅበር ሲፍጨረጨሩ ታይተዋል። “እውነትን ወይ ሕቅን በራሷ በኩል ልትቀብራት ብትሞክር፡ ጭራዋን ሽቕብ ሰቅላ እየቆላች ታሾፍብሃለች” እንዲሉ ነውና፡ የአርበኛው ህዝባችን ታሪክ ህይወት ዘርቶ አሁንም አሁንም መቃብርን እየፈነቃቀለ፡ በጠራራ ጸሃይ እየተነገረ ይገኛል።

መሓመድ ኑሪን በተመለከተ፡ አስቀድመን ካየነው እምቢተኛነቱ ባሻገር እስቲ የሚከተለውን መረጃ እንመልከት፦

“አቆርደት፡ ሰዓት 18፡10፡ . . . “ቺክዲኮላን [በምንሊክ የጣልያኑን ቆንስል] ናዅራ ላይ ያመለጡትን በሙሉ፡ እነ መሓመድ ኑሪ፡ ካሳ፡ ቢታ መሓመድ ዑስማንና አል ከቢር ወዘተን . . . በአሁኑ ሰዓት ትግራይ ውስጥ የሚገኙትን በሙሉ፡ ከትግራይ ወደ ሸዋ እንዲላኩ ትእዛዝ ያስተላልፍ ዘንድ እነግረዋለሁ። ትግራይ ውስጥ የሚገኙት ከምኒልክ ትእዛዝና መመሪያ ውጭ ነው። ከዚያ ባለፈ ግን፡ ያሳለፍነው ዓመታት የጓደኝነታችን ድምር ውጤት፡ ድንበሩ አካባቢ የተኹስ እሩምታ እንዳይሆን ያሰጋል።” (ማርቲኒ ዲያርዮ፡ 1901 ገጽ 327)

የምኒልክንና የጣልያንን ጓደኝነት በተመለከተ አስቀድሞ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች ተደግፎ ተገልጿል። እዚህ ላይ ግን ምንሊክ የኤርትራ ነብሮችን እንዳሻው ለመጨፍለቅ ዓቅም ስላጠረው፡ ማርቲኒ ሆየ ምንሊክን ማስፈራራት ተያይዞታል። ኣቤት የሁለት ቀማኛ ወመኔዎች ጓደኝነት።

“ ‘ኦልየ” ሓሙስ ወደ ሸዋ ያቀናል። መሓመድ ኑሪን በተመለከተ ግን ምንም የታወቀ ነገር የለም ‘ሙላሳኒ’ ”።

ማርቲኒም እንዲህ ይላል “ግድ የለም ደህና! መሓመድ ኑሪን በተመለከተ እኔው ራሴ በጥቂቱም ቢሆን መረጃ ሰብስቤ ኣውቂያለሁ። ይህ የዘለዓለም ሽፍታ፡ ከሌላው ወንጀሉ በተጨማሪ፡ “አስመራ ገብቼ ማርቲኒን እገላለሁ” እያለም ተናግሯል። ከአንዳንድ ታጣቂ ጀሌዎቹ ጋር በዓይደሮሶ (ዓዲሮሶ) አካባቢ ሳይኖር ኣይቀርም። ሁሉንም የወረዳ ኣዛዦች በሁሉም ኬላዎቻቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተነግሯቸዋል።” (ማርቲኒ፡ ዲያርዮ 1902 ገጽ 608)።

ኣየ ማርቲኒ! እሱና ምንሊክ በኤርትራ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ተግባር እንደ ጽድቅ፡ መሓመድ ኑሪ “እገልሃለሁ” ማለቱ ደግሞ እንደ ወንጀል እየቆጠረው ነው ማርቲኒ! ፍትሕ ለመሆኑ ሃገሯ የት ነው? የሰው ልጆች ሁሌም ጥቅማቸውን በተመለከተ ከሆነ፡ . . . “ጥቁሩን ነጭ፡ ቀዩን ደግሞ አረንጓዴ” ማለት አያሳፍራቸውም። የገዢዎችና ዓመጸኞች ዋንኛ መለያ ባህርያቸው ደግሞ “ውሸት” ነች።

በቀጣዩ ክፍል “ምዕራፍ 22 - ከአንዳንድ የጣልያንና የዓድዋው ገረስላሰ ተንኰሎች በከፊል” የሚለውን ክፍል እናያለን። ሰላም ወሰናይ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 27 Dec 2022, 05:14

ምዕራፍ 22 - ከአንዳንድ የጣልያንና የዓድዋው ገረስላሰ ተንኰሎች በከፊል

ልክ በወሩ መሓመድ ኑሪን ትግራይ ውስጥ ይታያል። ደጃዝማች ገረስላሴም መሰሪና ሽፍጠኛ ተግባሩን ጣልያንና ምንሊክን በማገልገል በተግባር ያሳያል። በየዕለቱም ጥቃቅን መረጃዎቹን ሳይቀር ለጌቶቹ ለጣልያኖች ያቀብላል።

“ዓድዋ፡ አስር ሰዓት። ደጃዝማች ገብረስላሴ እንዲህ እያለ ነው። ከአሁን በፊት ከመሓመ ኑሪ ጋር ዕርቅ ለማድረግና መሳርያውን እንዲያስረክብ እንዲሁም እስላሞች ባሉበት አንድ ስፍራ ትግራይ ውስጥ እንዲቀመጥ ፈርጌ ነበር። . . . ዛሬ ለሊቱን ደግሞ መሓመድ ኑሪ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ ከካህናቶች ዘንድ ተጠልሏል። ሶስት ሰዎችም ከሱ ጋር ኣሉ።

ከነሱ ውስጥ አንዱ የልጅ ዓይላይ ወንድም ተስፋዝጊ ነው። አንድ 91 የሚሆን “ጥይት ያለው” ውጅግራ የተባለ መሳርያም ይዘዋል። ምን ማድረግ እንደሚገባቸው በተለግራፍ እገልጽላቸዋለሁ። ታቫኖ፡” (ማርቲኒ፡ 1902፡ 55)

መሓመድ ኑሪ፡ ከደጃዝማች ገረስላሴ ለማምለት፡ ለግዜውም ቢሆን በቤተክርስትያን ይጠለል እንጂ፡ እዛ ለረጅም ግዜ ይቆያል ማለት ዘበት ነው። ሁኔታዎችን ከታዘበ በኋላም የማምለጫ መንገዱን ኣመቻችቷል። መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ ለምን ያህል ግዜ እንደቆየ ግን ምንም ዓይነት መረጃ ለማግኘት አልተቻለም። የሚታወቅ ነገር ቢኖር፦

“ መሓመድ ኑሩ ማምለጡ ነው። ቄስ ዘርኡም ኣዅሱም ውስጥ ታይቷል እየተባለ ነው።” (ማርቲኒ ዲያርዮ፡ 25/3/1903 ገጽ 157) ይላል። ከዚህ በተሻለም ግልጽ በሆነ አባባል፦

“ከደጃዝማች ገብረስላሴ ያመለጠው፡ ያ ቀንደኛው እምቢተኛ መሓመድ ኑሪ፡ ከአምስት ጀሌዎቹ ጋር በጉንደት አካባቢ እያንዣበበ ነው።” (ማርቲኒ ዲያርዮ፡ 1903 ገጽ 232) የሚል ነው።

ከዚህ ባለፈ ሁኔታ ግን ስለ መሓመድ ኑሪ ኣንዲትም መረጃ ኣናገኝም። በጣልያን ኣገዛዝ ወቅት፡ የኤርትራ ህዝብ እንደ አሁኑ ብርቱና የተደራጀ ሃያል ኣመራር ስላልነበረው፡ በየኣቅጣጫው የጣልያንንም ሆነ የምንሊካዊቷን ኢትዮጵያን ጭቆና በመቃወም እየታገለ፡ ለዝንተ ዓለም የሚሆን ታሪክን እንደጻፈ ለመረዳት አስቀድመን ያየናቸው አብነቶች ብቁ ማስረጃዎች ናቸው። የኤርትራ ህዝብ ወራሪዎችንና ገዢዎችን ኣሜን ብሎ የተንበረከከበት ግዜ በታሪኽ ኣልታየም። ኣጭሩ ትረካዊ መረጃችንም በዚህ ይቋጫል።

እምቢተኛውና ታጋዩ የሳሆ ህዝብ፡ በኢትዮጵያ ገዢዎች ኣማካኝነት ከደረሰበት ጭፍጨፋና ባልተለየ መልኩ በጣልያን ዕብሪተኛ ገዢዎችም ተጨፈጨፈ። ጣልያንም ልክ እንደሌሎች ገዢዎች ሁሉ፡ ለህዝብ ያልሆነ ተስፋዎችን በመስጠት ማታለል ኣንዱ የአሰራራቸው መታያ ነበር። ማንኛውም ገዢ ኣካል፡ ተስፋ የሰጠውን ቃል ማሳካት ይቅርና፡ ምን ብሎ ቃል ገብቶ እንደነበር እንኳ አያስታውሰውም። እስቲ ለመጨረሻ ግዜ ይሄን እንታዘብ። ሳሆዎች የተገባላቸው የተስፋ ቃል ከመተግበር ይልቅ፡ ታውጆላቸው የነበረው የምሕረት አዋጅ በመጣሱ፡ እንዲህ በማለት በድፍረት ጥያቄ ሲያቀርቡ ይታያሉ፦

“ሰገነይቲ፡ ሃምሌ 11። በ1895፡ ዓሳዎርታዎች ከዚህ ግዜ በፊት ስለተፈጸሙ ድርጊቶች ባጠቃላይ “ምሕረት” እንደተደረገልን ፡ ሜጀር ጋሊያኖ ኣውጆልን ነበር። አሁን ግን፡ ከዚህ ግዜ በፊት በተፈጸሙ ተግባሮችና ጉዳዮች ምክንያት እየታሰርንና እየተፈረድን ነው። መንግስት ግን ቃል የገባውን ነገር አያስታውስም እንዴ? መንግስት ተስፋ የሰጠውን ቃል ያጥፋል እንዴ? በማለት ስሞታ እያቀረቡ ነው።” (ማርቲኒ ዲያርዮ 1903፡ 232 ።)

የጽሑፉ ምንጭ

ኣንባቢ በቅጽበት እንደሚታዘበው፡ ይህ ኣጭር ጽሑፍ፡ ባብዛኛው መልኩ ከማርቲኒ ዲያሪ የተመሰረተ ነው። ከዕለታዊ ፍጻሜዎች ቀጥተኛ ትርጉም የተመሰረተ በመሆኑም ምስክርነቱ ኣያጠራጥርም። ማንኛውም ለማወቅ የሚሻ ዜጋ፡ ራሱ ከምንጩ ለመቅዳት ይቀለው ዘንድ፡ ዋንኞቹ ገጾችን እዚህ ማግኘት ይችላል።

1. FERDINANDO MARTINI; IL DIATIO ERITREO Editrice Vallecchi.
Volume I Pag.69: 114: 115: 142: 159: 164: 205: 207: 208: 213: 214: 16: 365: 369: 173: 398:
Volume II Pag.33: 47: 55: 97፡ 101፡ 106፡ 107፡ 125፡ 134፡ 141፡ 143፡ 44፡ 45፡ 157፡ 164፡ 232፡ 237፡ 262፡ 326፡ 344፡ 350፡ 356፡ 360፡ 363፡ 364፡ 369፡ 385፡ 388፡ 395፡ 398፡ 409፡ 492፡ 494፡ 498-499፡ 408-409፡ 410 502፡ 504-505፡506፡ 513፡ 516፡ 575-576፡ 554፡ 564፡ 565፡ 600፡
Volume III Pag. 20፡ 48፡ 55፡ 62፡ 116፡ 131፡ 145፡ 157፡ 164፡ 129፡ 159፡ 517፡ 226፡ 132፡ 238፡ 344፡ 350፡ 357፡ 350፡ 357፡ 371፡ 387፡ 406፡ 410፡ 411፡ 447፡ 490፡ 641 ።
Volume IV Pag.63፡ 85፡ 89፡ 306፡ 327፡
2. COMMISSIONE GENERALE DI INCHIESTA Editrice Mantellate. ROMA; 1891 pag
3. GIUSEPPE PUGLIESI CHI E? DELL’ ERITREA Agenzia Rgina; ASMARA. 195 Pag.223,4
4. GUIDO CORTESE; Traccia storica e politica dell’ocupazione Eritrea. ROMA 1934. Pag. 66፡ 67፡ 68፡ 88-89፡ 90፡ 91፡ 97፡ 100፡ 113፡ 115፡ 116


የሃገራችን የኤርትራን ታሪክ እናውቅ ዘንድ ይህን ታሪክ ላቆዩልን ለታጋይ ዶ/ር አባ ይስሃቅ ገብረ ኢየሱስ ላቅ ያለ ኣክብሮታችንን ለግሰናል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኣኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ይህትና ጭምር። ሰላም ወሰናይ!!!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራን ህዝብ ለመጨፍለቅ የምንሊክና የጣልያን ቃልኪዳን (የ1897-1907 ሰነድ) በአባ ይስሃቕ ገብረ ኢየሱስ

Post by Meleket » 23 Aug 2023, 04:46

እላይ ካነበብነው ትረካ ጋር በጥቂቱም ቢሆን ግንኙነት ስላለው ነው እዚህ የዶልነው። ምንሊክ "የክርስትያኖች ሁሉ ኣባት" በማለት ለጠቀሷቸው ለሮም ሊቀ ጳጳሳት "ሊዎን ፲፫" በጦርነት መካከል ስለተማረኩት ጣልያናውያን ስለሚደረግ የምሕረት ተግባር የጻፉት የመልስ ደብዳቤ መሆኑ ነው። wikimedia.org እንዲሁም Revelations እናመሰግናለን።
Revelations wrote:
22 Aug 2023, 22:27
.. ..

.. ..

Post Reply