Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5543
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

መገንባት፣ ማፍረስ፣ እና ክህደት

Post by Naga Tuma » 06 Oct 2022, 14:35

መገንባት እና ማፍረስ ተቃራኒ ሀሳቦች ናቸዉ። ዲሞክራሲ ለእነዚህ ተቃራኒ ሀሳቦች መፍትሄ ሊሆን ይችላል? ኣይመስለኝም።

የራስን እድል በራስ መወሰን ማለት ምን ማለት ነዉ? ከእንግሊዘኛዉ ሰልፍ ዲተርሚኔሽን (self-determination) የተተረጎመ ነዉ። ማን ለመጀመርያ ጊዜ እንደተረጎመዉ ኣላዉቅም።

ትክክለኛ ትርጉም ነበር? እስቲ ከኣማርኛዉ ወደ እንግሊዘኛ መልሰን እንተርጉመዉ እና ትክክለኛ እንደነበር እናረጋግጥ። የራስን እድል በራስ መወሰን to decide one's luck by oneself ማለት የሚቻል ይመስለኛል። ይህ ትርጉም ኣሳማኝ ከሆነ ከእንግሊዘኛ ወደ ኣማርኛ በትክክል ተተርጉሞ ነበር ማለት ይቻላል? ፍርዱን ለኣንባብያን መተዉ ነዉ።

ሀሳቡ የመብት ክርክር ነበር ማለት የሚቻል ይመስለኛል። የመብትን ጥያቄ በግል ድምጽ መስጠት ባላይ ወሳኝ መንገድ ኣለ? ስለዚህ የመብት ጥያቄ በግል ድምጽ መስጠት የመቻል ጥያቄ ነበር። ከዚህ በላይ ሊሆን ይችላል?

በግል ድምጽ በመስጠት መወሰን በሃገር ዉስጥ ነዉ። ሃገር ሲኖር ነዉ። ኢትዮጵያ ሃገር ናት። ኣሜርካ ሃገር ናት። ጀርመን ሃገር ናት። ለምሳሌ ያህል።

ከኣሜርካ በላይ ሃጥኣት በመስራት የተመሰረተ ሃገር ያለ ኣይመስለኝም። ከኣዉሮፓ ፈልሰዉ ኣሜርካ በመስፈር፣ የኣሜርካን ነባር ህዝብ ክፉኛ በመበደል፣ እና ከኣፍሪካ ነበር ህዝብ ዉስጥ ብዙዎችን በጉልበት ኣፍኖ ዉቅያኖስ በማሻገር እና ጉልበታቸዉን ክፉኛ በመጠቀም።

ከጀርመን ሃገር በላይ ሃጥኣት የተሰራበት ምድር ያለ ኣይመስለኝም። በሚልዮኖች የሚቆጠሩትን ክፉኛ በማቃጠል።

ታድያ ስንቶች ኢትዮጵያን ናቸዉ ኣሜርካ እና ጀርመን በኢኮኖሚ ሃብታም ስለሆኑ ኣሜርካዊ እና ጀርመናዊ ሆኖ መኖር የቀናቸዉ። እነዚህም መብቶች ናቸዉ።

የገረመኝ በኣሜሪካ የሚሰራ መሰረቱ ኢትዮጵያ የሆነ ፕሮፌሰር ይህን ሁሉ እያወቀ ወይም ሳያዉቅ በዚህ ጊዜ፣ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ዉስጥ የራስን ዕድል በራስ መወሰን ያሚለዉ ሀሳብ እንዴት ሳይጠጥረዉ መተንፈስ እንደሚችል ነዉ።

መገንባት መሻሻል የሚችሉትን ሁሉ ጨምሮ ማሻሻል እና ማሳደግ ነዉ። ይህ ፌዴራሊዝምን ማሻሻልን ይጨምራል። ለዚህ ነዉ ዲሞክራሲ መፍትሄ የሚሆነዉ። ዲሞክራስያዊ በሆነ መንገድ እንገንባ ሲባል ማፍረስም መብቴ ነዉ ባይ መገንባትን የከዳ ነዉ ማለት ነዉ። ለዚህ ነዉ እንገንባ ሲባል ማፍረስም መብት ነዉ ማለት ክህደት የሚሆነዉ።

ይህቺን ለመለየት ፕሮፌሰር መሆን ኣያስፈልግም።