Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Horus » 05 Oct 2022, 13:45

The AP Story at the bottom ...

እኔ ሆረስ እጅግ ቀደም ብዬ የዚህ ጦርነት ታሪክ መጨረሻ ላይ እንዴት ይጽፋል? ብዬ ሳበቃ 'ተዋግተው ተዋግተው ውጊያ አቆሙ' ተብሎ በታሪክ ይመዘገባል ብዬ ነበር ።

ምን ማለቴ ነው? ጦርነት በአምጽ የሚካሄድ ፖልቲካ ነው ። ማለትም ጦርነት ፖልቲካ ነው። የፖለቲካ አላማዎች ቢያንስ አራት ናቸው፤ (1) ስልጣን/ሃይል፣ (2) ገንዘብ/ሃብት፣ (3) ዝና/ስም/ሬፑቴሽ፣ (4) ክብር/ማንነት ናቸው።

ስልጣን ማለት የመወሰን ሃይል ማለት ነው ። ማን ምን ያገኛል፣ ይደርጋል? ማን ስንት እና እንዴት ያገኛል? ማ ምን መሆን አለበት? መወሰን መወሰን መወስን !!!!! የተቀሩት ግልጽ ናቸው ክብር ወይም ዲግ ኒቲ የማንነት መከበር ማለት ነው ።

ስለዚህ የጦርነት ተግባር እነዚህን አላማዎች በጉልበት ማስፈጸም ነው ። ሰላም ሰላም የሚባለው ባዶ ቃል ነው !!! ቡና ላይ ተቀምጠው የላይኞቹን አራት ፍላጎቶች ማን ምን ይድረሰው ብለው የሚነጋገሩ የሰለጠኑ ሕዝቦችና በእውቀት የሚመሩ፣ በሳይንስ የሚገዙ፣ ሰዎች ናቸው ። ቀድሞውኑ ዉጊያ አይሄዱም፣ ችግራቸውን በንግግር ስለሚጨርሱ ማለት ነው።

ስለዚህ የወልቃይት መሬት የማነው የሚለው የሃብት/ሪሶርስ ባለቤትነት ውሳኔ በአመጽ ለመተግበር እየተዋጋ አንድ ሰው ስለሰላም ሊያወራ አይችልም ።

መጀምሪያ ማንኛው ፖለቲካ አለ ጦርነት መተግበር መመሪያ ያደረገ ስልጡን እንሰሳ ብቻ ነው ስለሰላም ማውራት የሚችል ።

አይ ፖለቲካዬን በጉልበትና አመጽ ነው የምከውን ያለ ሰው ደሞ በአንጻሩ ሌላው ወታደር አቁሙ ይዋጋዋል ። አንዱ ወገን በጉልበት አሸንፎ ስልጣን፣ ሃብት፣ ዝናና ክብር ቢቀማ እንኳን የሁለቱ ተፎካካሪዎች ጥብ አይፈታም ። የተሸነፈው ለግዜው ቤቱ ሄዶ ለሚቀጥለው ዉጊያ ይዘጋጃል ። የፖለቲካ አላማ ፍትሃዊ በሆነ ተስማሚ መንገድ ስላልተቋጨ ማለት ነው።

ለዚህ ነው ታሪክ ተዋገተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ ብሎ የሚደመድመው ። ጦርነት ተዋግቶ ማሸነፍና የፖለቲካ አላማዎችን ፍላጎቶችን ሁለቱ ተገዳዳሪዎች በሚቀበሉት መንገድ ምፍታት እንደ ቀናን ለሊት የተለያዩ ናቸው!

ስለዚህ እስቲ ከናንተ መሃል ትህነግ የሚፈልገው ስልጣን/ ሃይል፣ ሃብት፣ ዝናና ክብር ምን ምን እንደ ሆኑ ነገሩን???????? በተመሳሳይ መንግስት ወይም ብልጽግ ና የሚፈልገው ስልጣን/ሃይል፣ ሃብት፣ ዝናና ክብር ምን ምን እንደ ሆኑ ነገሩን???????? እናም አንዱ ቢያሸንፍ በጉልበት የሚቀማቸውን ስልጣኖች፣ ሃብቶች፣ ዝናዎችና ክብሮች ብትጠቁሙን :lol: :lol: :lol:

The New Africa led negotiation - by Obasanjo , Kenyatta, & Mlambo-Kguka of South Africa.....
https://www.yahoo.com/news/ethiopia-gov ... 10282.html

Abere
Senior Member
Posts: 11064
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Abere » 05 Oct 2022, 14:05

የሎሌነት ጦርነትስ ምን ይባላል? ከገንዘብ/ሃብት ጋር ይገናኝ ይሆን? ወያኔ የተፈጠረው ለባዕዳን አገራት ሎሌነት ነው። ኦነግም አሽከር ወይም ለሎሌነት ነው የተፈጠረው። ወያኔ እና ሻዕብያ አዲስ አበባ ሲገቡ የኦነግ ሰዎች ሻንጣ ተሸክመው አብረው ገብተዋል። ነፍሱን ይማረው እና አሰፋ ጨቦ የኦነጎችን ሻንጣ ተሸካሚነት የአይን ምስክር ሁኖ ነግሮናል።

አንዳንድ ጊዜ ሳስበው አሁን ጦርነት ነው ሽፍትነት(ዘርፎ ማደር) የትኛው መስፈርት እንደሚመጥነው ግራ ያጋባል። ትግሬዎች እህል ማሳ ውስጥ እንደ ገባ ዝንጀሮ የሌላን ህዝብ ሰፈር ይወሩ እና ባለቤቱ ሲመጣ እንደ ዝንጀሮ እየጮኹ ተመልሰው ይሸሻሉ - ኡ ኡ ጆባይደን እየተባለ። አሁንም ይህ 3ኛው ዙር ሽርሽር ሲያልቅ ያንኑ ጩኸት ነው የሚያቀልጡት። ተመልሰው ይመጣሉ ለ4ኛ ዙር። ጠባቂ የለም።

ወያኔ ከምድረ-ገጽ ካልጠፋ ጦርነት ይቆማል የሚል እምነት አይኑርህ።


Horus wrote:
05 Oct 2022, 13:45

ምን ማለቴ ነው? ጦርነት በአምጽ የሚካሄድ ፖልቲካ ነው ። ማለትም ጦርነት ፖልቲካ ነው። የፖለቲካ አላማዎች ቢያንስ አራት ናቸው፤ (1) ስልጣን/ሃይል፣ (2) ገንዘብ/ሃብት፣ (3) ዝና/ስም/ሬፑቴሽ፣ (4) ክብር/ማንነት ናቸው።

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Horus » 05 Oct 2022, 14:17

አበረ፣
ሎሌነትና የፕሮክሲ ጦርነትን የሚነዳው ፍላጎት አራቱንም ቢነካም ዋናው ሃይልና ሃብት ነው ። አላያንስ፣ ትብብር፣ ቅንጅት ከሌላ ሰው ጋር የሚደረገው ሃይል ለማገንታት፣ የሃይል ሚዛን ለመድፋትና ለዚያ አንዱ መሳሪያ የገንዘብ መረዳዳት ስለሆነ ነው ። አሜሪካ የአፍሪካን ቀንድ መቆጣጠሪያ ሃይል ይፈልጋል፤ ያን ካደረገ በኋላ ያካባቢውን ሃብትና ንግድ ይቆጣጠራል። ለዚህ መሳሪያነት ወያኔ ይፈለጋል። ወያኔም ከኤርትራና ኢትዮጵያ ጋራ ያላት ሚዛን ለመድፋት እና ባማራና አፋር ላይ ተቆጣጣሪ ለመሆን ያሜሪካናን አውሮፓ ገንዘብ፣ መረጃና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ትፈልጋለች ። ይህ ሁሉ ለትግሬ የሚጎርፈው የስንዴና፣ ካሚዮናን ነዳጅ ክምር ሌላ ምን ትርጉም አለው? ሃይል፣ ገንዘብ፣ መረጃ፣ ክብር(ሆነር)!! አሜሪካ ከኢትዮጵያ መባረር ማለት ከቬትናም የባሰ ውርደት ነው!አይቀበሉትም!

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Horus » 05 Oct 2022, 14:35


Abere
Senior Member
Posts: 11064
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Abere » 05 Oct 2022, 15:47

ሆረስ፤

አንድት ጥያቄ አለችኝ ከፓለቲካ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ሊቃውንት እይታ:: አንድ መንግስት ወይም ቡድን ምንም እኳን አሸናፊ መሆኑን እርግጠኛ ሁኖ ከስነ-ምግባር አንጻር ለድርድር ተቀመጥ ሲባል እሽ ማለት አለበት ወይስ የለበትም? እምቢ ቢል ምን የፓለቲካ ኪሳራ ያመጣበታል? እሽ ቢልስ ምን የፓለቲካ ፋይዳ አለው። እደራደራለሁ እያለ ተቃራኒውን ሳይደራደር በጦር ብቻ ያሸነፈ ቡድን ከታሪክ ለአብነት የሚቀርብ ምሳሌ ይኖር ይሆን? በመሰረቱ እኔ የወያኔ እና የኦነግ ብልጽግና ጥል አህያ ለአህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም አይነት ነው። ይህ ሁሉ ሽር ጉድ ወያኔ ከአማራ ክልል በከፊል ስለተባረረ ነው - የሞኝ ምስጢር የባቄላ ወፍጮ ነው። እኔ መቸም በኢትዮጵያ ዘላቂ ግጭት እንጅ ዘላቂ ሰላም ወያኔ እና ኦነግ እያሉ አይኖርም። በፍጹም። እነኝህ የግጭት ኢንዱስትሪዎች ናቸው - የግጭት ግብዐታቸው ከውጭ የሚመጣ ነው። There has to be a big shock to dust off these criminal thugs.

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Horus » 05 Oct 2022, 16:20

አበረ፣
አንድ ኩነት (ኢቬንት) ትግሩሙ ምንድን ነው ስንል እያንዳንዱ ተመልካቸ ከቆመበት ቦታ ሆኖ ነው የራሱን ትግሩም የሚያገኘው የሜሰጠው ። ይህ ድርድር ሆነ ድልድል ከትህነግ አንግል፣ ከቢይ አንግል፣ ካማራ አንግል፣ ከኦሮኦ አንግል እያልን ካላነው የምናገኘው ትግሩም ዝብርቅ ይሆናል ።

የአቢይ መንግስት ምንግዜም ድርድር መደገፍ አለበት ። ሃይል ያለው እሱ ስለሆነ ዞሮ ዞሮ የሚያሸንፈው ጦርነት የመጨረሻ ምርጫው ነው። ሰውና ሃብት ግዜ ስለሚበላ። ደሞም ዞሮ ዞሮ አገር መሪና ተቆጣጣሪ ስለሆነ ምንግዜም ለድርድ መቀመጥ አለበት። ይህ ሲያደርግ ገሚሱ በአጎብዳጅነት ገሚሱ በካዲነት ወይም ፈሪነት ይወቅሰዋል። ያ ደሞ ያለ ነው ። ጥያቄው በዚህ ድልድል ወያኔ ምን አይነት ስልጣን፣ ሃብትና ድርሻ ያገኛል የሚለው ነው ውጊያው ያለበት ደረጃ የሚወስነው ።

ትግሬ ሌላ የጦርነት ዙር ለማድረቅ አቅም አለኝ ብሎ ካመነ ጥያቄዎቹን ከፍ ያደርጋል ማለትም በትግሬ ላይ ያለውን ስልጣም እና በፌዴራል መንግስት ውስጥ የሚኖእውን ስልጣን በተመለከተ ማለት ነው ። የመዋጋት አቅሙ ደክሞ ከሆነ ብዙ ንትርክ የሚሆነው ስለ ደህንነት፣ አለመከሰስ፣ ካገር መውጣት፣ ይፎቅ ቤቶ መመለስ አይነት ይሆናሉ። ይህ ሁሉ ስብሰባ ሲክሄድ ሁሉም ለሚቀትለው ትግል መደራጃ ግዜ ያገኛል ማለት ። ጦርነትም ድርድርም ፖለቲካ ናቸው። ጥያቂያቸው አንድ ነው ።

ሰላም ከትግሬ ይልቅ አቢይን ይጠቅመዋል ። አቢይ ግዜውን ትግሬ ተራሮች ውስጥ ሲያባክን በመላ ኢትዮጵያ ሁሉንም ነገር እየተበላሸበት ነው ። ትግሬ ከልጆቹ መሞት ሌላ ምንም አይሆኑም። አለም ስንዴና መዳኒት ይልካል። ያለም ወሬ ትግሪ ትግሬ ይላል፣ ያ ደሞ የወያኔ ጫት ማለት ነው ! የዝና ሱስ!!!

የዚህ ሁሉ ጥቅል ድምር ቅንስ ውጤት 'ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ' ነው ። ነገር ጠረጴዛ ዙሪያ ለሚቀመጡ ለምን ሁለት አመት ሰው ይዋጋል?

እንደ ሁለትኛ አለም ጦርነት ተሸናፊ ተምበርክኮ ጦር አፍርሶ፣ መሬት ቆርሶ ላሸናፊው የሚገዛበት የተለየ ጦርነት ነው። ይህው ጀርመን ጃፓን ጣሊያን እስከ ዛሬ ይህ ነው የሚባል ጦር የላቸውም።

በነገራችን ላይ የትግሬ ጦር መፍረስም አንዱ ትልቁ ያቢይ ካርድ ይመስለኛል ። ትግሬዎቹ ደሞ ኦርሞም አማራም የራሳቸውን ልዩ ጦር ያፍርሱ የሚል ማለቂያ የሌለው ስብሰባ እንደ ሚሆን ጠብቅ !!!

ለዚህ ነው የዚህ ሁሉ መፍቻ ቁልፍ የጎሳውን ቂጣ ማፍረስ ነው የምንለው !

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Horus » 05 Oct 2022, 19:44

Herman Cohen said, "During upcoming #Ethiopia-Tigray mediation talks in #SouthAfrica, key question will be continued existence of #TPLF as ruling political entity in Tigray. Addis is unlikely to offer more than amnesty and safe passage out.
1:18 PM · Oct 5, 2022"

I said a while ago .... " ትግሬ ሌላ የጦርነት ዙር ለማድረቅ አቅም አለኝ ብሎ ካመነ ጥያቄዎቹን ከፍ ያደርጋል ማለትም በትግሬ ላይ ያለውን ስልጣም እና በፌዴራል መንግስት ውስጥ የሚኖእውን ስልጣን በተመለከተ ማለት ነው ። የመዋጋት አቅሙ ደክሞ ከሆነ ብዙ ንትርክ የሚሆነው ስለ ደህንነት፣ አለመከሰስ፣ ካገር መውጣት፣ ይፎቅ ቤቶ መመለስ አይነት ይሆናሉ። "

Therefore, if Cohen right about Abiy's playing hands, that means TPLF has lost the battles and the war is won by Abiy.

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12617
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Fiyameta » 05 Oct 2022, 20:48

Like Tazabi said, the TPLF, by accepting the AU-led peace talks without preconditions, which they had previously rejected, are now asking for a negotiated surrender. When the ENDF swiftly seized Kola Tembien, an area the TPLF consider their safe haven, it caught its Western backers by surprise, leading them to seek a negotiated surrender to save face.


Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Horus » 06 Oct 2022, 12:57

እኛ አበሾች ስንተርት ሌባ ላመሉ ቅቤ ይልሳል እንላለን! ደደቢት ወያኔ የዛሬ 4 አመት ከነፈሰው ንፋስ ጋር ለዘዴ እንኳን ቢሆን አብሮ ተጉዘው ለውጡን እኛም አለንበት ቢሉና ያ ሁሉ የነበራቸውን ሃይልና ገንዘብ ለውጥ ተብዬው ላይ ቢያፈሱ ዛሬ አዲሳባ ሸገር ካፌ ከዚያም ኮሪፍቱ እስፓ እያሉ ይንፏለሉ ነበር።

ግን ፍሬ ከዛፉ ርቆ አይወድቅም እንዲሉ ጦርነት መጫወቻችን ነው የሚለውን የጂል ዘፈን ላለም ፈረንጅ ለማሳየት 2 አመት ለጦር ተዘጋጅተው፣ 2 አመት ተዋግተው፣ ብርሃን ኮርኔቲ አልባ ዘመነ ጭለማ ተመልሰው ፣ ያ ሁሉ ከሆኑ በኋላ ጥቂት የሰላምና ደህንነት ፍርፋሪ ካቢይ ለማግኘት ያለም ተራራ ሲቧጥጡ ማየት ማስገረም አይደለም ያሳዝናል! የድድብናቸው ልክ ማለት ነው ።

ጦርነቱ አመሉ! ሌባ ላመሉ ብዬዋለሁ!! የትግሬ ወያኔ ተዋግቶ ተዋግቶ ውጊያ አቆመ ተብሎ ይዘፈናል:lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30841
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ! (AP)

Post by Horus » 06 Oct 2022, 22:15

የአፍሪካ መግለጫ በአንድ ነገር አልተመቸኝም ። አንድም ቦታ የኢትዮጵያን መንግስት በስም አይጠቅስም ይህም ይሆነ ትህነግ ፣ የትግሬ ጦር፣ ወይም የትግሬ መንግስት ላለማለት ነው ። ይህ በፍጹም ትክክል አይደለም ። "the twp parties' ነው የሚላቸው ። እሺ አሁን የኢትዮፌዴራል መንግስት ከማን ጋር ነው ድርድር የሚያደርገው ።
(1) የኢትዮጵያ መንግስት ድርድር የሚያደረገው ከትግሬ መንግስት ጋር ከሆነ ዛሬ ላይ ህጋዊ የትግሬ መንግስት አለ ወይ? በሕገ ወጥ ምርጫ አይደለም ወይ ደብሬ ፕሪዚዳንት የሆነው?
(2) ከትህነግ ጋር ከሆነ ብልጽግ ና ከመጣ በኋላ ትህነግ የሚባል ህጋዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ የተመዘገበ ፓርቲ በኢትዮጵያ አለው ወይ?
(3) ድርድሩ ከትግሬ ጦር ጋር ከሆነ ይህ የጎሬላ ሪቤል ቡድን ስለሆነ እንዴት ከዚትዮጵያ መንግስት እኩል 'ዘ ቱ ፓርቴስ ' የሚል የተደራዳሪነት እስታተስ ይሰጣቸዋል?

እናም ይህ ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር የሚያደርገው የትግሬ ቡድን ምን ስልጣን አለው? ስምምነት ቢደረገስ ለዚህ ስምምነት ተጠያቂ የሚያደርገው ምን ህጋዊነት አለው?

እንዴት ተብሎ ነው ኢትዮጵያ ስም የለሽ ተደራዳሪ ፓርቲ የሚለውን ስም የተቀበለውችው?

ከዚያ በተረፈ አንድ ነገር ልበል !!!

በጦርነት የተሸነፈ ቡድን በድርድር ትሪቲ አያሸንፍም ። ከጦርነት በኋላ የሚደረግ ድርድር ሁልግዜ የጦርነቱን ውጤት በወረቀት ላይ አስፍሮም ወደ ስምምነት መለወጥ ነው አላማው! ማለትም ኢትዮጵያ ትክክለኛ ተደራዳሪዎች ካሏት ማለት ነው ። አንድ ቡድን ወይም አገር በጦርነቱ ወስጥ ያላገኘውን ሚዛን በድህረ ጦርነት ድርድር ሊያገኝ አይችልም! የፖለቲካ ሎጂክ ይቃረናል!

እና ትህነግ ምንም አይነት የተለየ ድርሻ ሊያገኝ አይችልም! ወልቃይትና ራያን በጦር መያዝ አልቻለም፣ አሁን በድርድር ወልቃትና ራያ ሲሰጠው አይችልም።

እናሳ ምንድን ነው የዚህ ድርድር ፋይዳ ለትግሬ? መብራትና ዉሃ ማስገባት ነው በቃ!

Post Reply