ከባድ የአእምሮ ሕመም ያለበትና ባሳለፍነው ክረምት አንጎሉ ተከፍቶ የታከመው አብይ አህመድ አንዳንድ የጦር መሪዎቹ ይሄ ጦርነት ይቅርብን ሲሉት አሻፈረኝ በማለት በትግራይ ላይ ነሐሴ 18/2014 የከፈተው ውጊያ ብዙ ሥራዎች የተሠሩበት ነበር፡፡
ጦርነቱን አሸንፈን ወያኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዱቄት አድርገን አዲስ ዓመትን ከመቀሌ፣መስቀልን ከአዲግራት በቀጥታ የቴሌቭዥን ሥርጭት እናከብራለን ብሎ ብዙ ዝግጅት አድርጎ ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ የአዲስ ዓመቱ ዕለት ሌሊት የሚተላለፍ ዶክመንተሪ ማዘጋጀት ነበር፡፡የዶክመንተሪው ስክሪፕት የተፃፈው፣በዶክመንተሪው ላይ የሚገቡት ቪዲዮዎች የተመረጡት በራሱ በአብይ ነው፡፡ዝግጅቱን የሚሠራው ደግሞ ካክተስ የተባለው ድርጅት ነው (Cactus Advertising & Marketing)፡፡
አብይ እኩለ ሌሊት ላይ እየመጣ ይሄንን አውጡ፤ያንን አስገቡ እያለ ሲያስቸግራቸው የነበሩ የካክተስ ሠራተኞች ተማርረው እንደነበር ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ከተከፈላቸው ገንዘብ በላይ በሆነ ደረጃ የሰውየው ባሕርይ አስቸጋሪ በመሆኑ ተማረው እንደነበር ረጆ ሚድያ ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡፡
የተዘጋጀው ዶክመንተሪ አብይ እንዴት ያለ ጀግና የጦርና የፖለቲካ መሪ፣የፕሮጀክት አስተዳዳሪ፣የተዋጣለት ዲፕሎማትና አገር ወዳድ መሆኑን ማሳየት ዋናው ግቡ ነበር፡፡የትግራይን ጦርነት እንዴት ባለ ታጋሽነትና አገር ወዳድነት ሲመራው እንደነበር፣ግን ጁንታው ሊያርፍ ስላልቻለ ወደ ውጊያ እንደገባ፣በመጨረሻም እንዳሸነፈ የሚገልጽ ነበር፡፡
የተያዘው ዕቅድ ልክ ጦሩ መቀሌን እንደያዘ ዶክመንተሪው እኩለ ሌሊት ላይ በሁሉም የብልጽግናው ቴሌቭዥኖች ሊተላለፍ ነበር ፡፡ሆኖም መቀሌ ይገባል የተባለው ሠራዊት ጭራሽ፣ቆቦንም፣ጎብዬንም፣ዶሮ ግብርንም አልፎ በኋላ ማርሽ ወደ ወልዲያ እግሬ አውጪኝ አለ፡፡እነሆ ከዚያች ቀን ጀምሮ አንደኛው የአብይ ግንባር ግንባሩን ተብሎ ከአልውሃ ምላሽ አልተመለሰም፡፡በፀሊሞይ ግንባርም ተስፋው ጨልሟል፡፡
ልክ እንደ ዶክመንተሪው መቀሌ ሲያዝ በከተማዋ አደባባዮችና ስታድየሞች ሊለበስ የነበረውን ግማሽ ሚሊዮን ቲሸርት ዱባይ ሄዶ ከመታተሙ በፊት ዲዛይኑን ያዘጋጀውም ይሄው ካክተስ የተባለ ድርጅት ነው፡፡
ካክተስ የተሰኘው ድርጅት የተራራ ኮፊ፣የባገራሽ ኮፊ፣የቡክ ወርልድና የላይም ቲሪ ባለቤቶች ንብረት ሲሆን በአቶ ያሲር ባገርሽ የሚተዳደር ነው፡፡ከኢሕአዴግ መንግሥትም ጋር አብሮ ይሠራ የነበረው ይሄው ካክተስ አሁን ደግሞ የአብይ አህመድ ደም አፍሳሽ ጦርነት ደም ቀጂ ሆኗል፡፡ እንዲህ ያለውን መረን የለቀቀና መርህ የለሽ አካሄድ ለምን እንዳደረገው ሲጠየቅ ‹‹እኔ ሥራዬን ነው የምሠራው›› ይላል አሉ፡፡
ይህ አይነት አካሄድ አንድ ታሪክ ያስታውሰናል፡፡አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ኤርትራንና ግብጽን ለምን ሰለላችሁ ብሎ የከሰሳቸውን የቀድሞ የደህንነት ኃላፊዎች ለፍርድ ሲያቀርብ አንድ ግርማ ተገኝ የሚባል በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ ኃላፊነት የነበረው ግለሰብ ለምስክርነት ይልካል፡፡
ግርማም ወንጀል ነው ያለውን በሙሉ በነዚህ ሰዎች ላይ መሰከረ፡፡
Please wait, video is loading...
‹‹ታዲያ ያኔ ይሄ ሁሉ ወንጀል ሲሰራ ለምን አላስቆምክም…›› የሚል መስቀለኛ ጥያቄ ቀረበለት፡፡እርሱም ‹‹ለእንጀራዬ ብዬ ነው›› ሲል መለሰ፡፡
ተከሳሾቹም ‹‹አሁንም ለእንጀራው ሲል ነው እየመሰከረብን ያለውና ይህ የሀሰት ምስክር ሆኖ ይመዝገብልን›› በማለት ተከራከሩ፡፡
የካክተስም ጉዳይ ይሄው ነው፡፡ለእንጀራው ሲል ከአብይ ጋር የንጹሃንን ደም ያቃዳል፡፡
4 comments