Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11064
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

3ኛው ዙር ባለህበት ቁም ትዕዛዝ ለወሎ ፋኖ ሊደርሰው ይችላል--->- ትህነግን የማዳን ዘመቻ።

Post by Abere » 04 Oct 2022, 15:18

3ኛው ዙር ባለህበት ቁም ትዕዛዝ ለወሎ ፋኖ ሊደርሰው ይችላል--->- ትህነግን የማዳን ዘመቻ።

እንደ እኔ የወሎ ህዝብ የተረፈው በተመላላሽ ወራሪ ህይወት እና ሃብቱን በከንቱ ማጣቱ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ውሃ የሚቋጥር ነገር ከዚህ ጦርነት ያገኛል ብየ አልገምትም። ለምን? የኦነግ-ብልጽግና መንግስት አቋም ከዚህ በፊት በነበሩት 1ኛ እና 2ኛ ዙር የወያኔ ወረራዎች መንግስት ነኝ ባዩን አካል አቋም በግልጽ ያመላክታሉ። የወያኔን ህገ-መንግስት የተቀበለ ቡድን የተሻለ ይደርጋል ብሎ የሚያስብ ሞኝ ነው - የፒፒ ኮሙኒኬሽን እንደ በፊት መርዶውን ይዞ ብቅ ይላል።ግን የሰሜን ወሎ ህዝብ ወይም አማራ ፋኖ ይህን ከወድሁ አውቆ ወይም ጠርጥሮ የእራሱ ጽኑ አቋም ሊኖረው ይገባል። የታገልከው የስልጣን ታኮ ለመሆን ሳይሆን ማንነትህን በትግልህ ለማስመለስ ነው። ከዚህ ያነሰ ግብ ወይም አላማ ሊኖርህ አያስፈልግም። ነገ ወያኔ መጥቶ የጦርነት ሽርሽር ጫጉላውን ወሎ ላይ ያደርጋል። ስለዚህ ጫጉላውን ከማይጨው ባሻገር ትግራይ ውስጥ ያደርግ ዘንድ ማይጨውን አሻግራችሁ ሸኙት።

Abere
Senior Member
Posts: 11064
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: 3ኛው ዙር ባለህበት ቁም ትዕዛዝ ለወሎ ፋኖ ሊደርሰው ይችላል--->- ትህነግን የማዳን ዘመቻ።

Post by Abere » 05 Oct 2022, 16:03

" 3ኛው ዙር በተለመደው መንገድ ተፈጽሟል። አሁን ትንሽ ዕረፍት እንወስድ እና ፋኖን አሳደን ተጨማሪ 20,000 እስር ቤት አስገብተን ስንጨርስ 4ኛውን ዙር ወያኔ እንድትጀመር ፊሽካ ይነፋላታል።" 7ኛው ውሸት :mrgreen:

Post Reply