Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12530
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must Read : የጎብየ ሕዝብ ስለ ትግራይ መከላከያ ምን አለ ?

Post by Thomas H » 04 Oct 2022, 09:47

Kassa HaileMariam

«ተሰናብተውን፤ መርቀን ነው የሸኘናቸው»
የጎብየው ወዳጄ

ከራያ ሜዳ እስከ ዓፋር በረሃ በርካታ የድሮ ወዳጆች አሉኝ:: ከእነዚህ ወዳጆቼ ውስጥ አንድ የጎብየ ወዳጄ ዛሬ ኔትወርክ ወዳለበት ወርዶ ደወለልኝ፤ በጣም ገረመኝ ደስም አለኝ:: ከ1980ዎቹ መገባደጃ በኋላ አልተገናኘንም::
«... ለመሆኑ ስልኬንስ ከየት አገኘኸው?...» ስለዉ፤
«...እንዴ እነእንትና እኮ ከእኛው ዘንድ ነበር የሰነበቱት፤ ስላለፈው ስናወጋ የት እንዳለህ ነገሩኝ፤ ስልክህንም ሰጡኝ...» አለኝ፤ የትግራይ ሰራዊት አባላት ናቸው:: ወደ ኋላ ሂደን የደጉን ጊዜ ትዝታዎችን አንስተን፤ እንዲሁም ስለወቅቱ ሁኔታ ብዙ አወጋን::
ሰሞኑን ከእነሱ ጋር ስለሰነበቱት የትግራይ ሰራዊትና አመራር አባላት ካጫወተኝ ውስጥ አንድ አባባሉን ለማጋራት ፈለግኩ::
«... ወላሂ ልጆቻችን ናቸው፤ ... ከአፋቸው ፍቅር ሰላም እንጂ ክፉ የማይወጣቸው፤ ... አሰራራቸው አካሄዳቸው ሁሉ የአላህን መንገድ የተከተለ፤ ወገኖቻችን ናቸው:: የሰው ንብረት የማይሹ፤ ያለቻቸውን ሊያካፍሉህ የማይቀደሙ፤ ወላሂ የሰውም ሰው ናቸው:: በመጨረሻም መክረው አስተምረው ተሰናብተውን መርቀን ነው የሸኝናቸው::
እንዳው መንግስትን አደራ እምለው፤ እንደአምናው እንዳይዋሹን ነው:: እራሳቸው ተሰናብተውን ለቀው ወጥተው እያሉ፤ አባረን አስወጣናቸው እንዳይሉን አደራ! በንፅህና ተሰናብተውን ሂደው እያሉ፤ አገር አወደሙ ሴት ደፈሩ እያሉ ባልዋሉበት ስማችውን እንዳያጠፉ አደራ እላለሁ:: እዚህ አገሬው ሁሉ እንዳይታዘባቸው...» እያለ ስለቀድሞ የትግራይ ታጋዮችና ስለአሁኖቹ የትግራይ ሰራዊት አባላት ስነምግባር፤ በአድናቆት ግርምት ነበር ያጫወተኝ::
አዎ፤ የአንድ ሰራዊት ስነምግባር ከተሰለፈለት ዓላማ ፍትሓዊነት ይመነጫል! የትግራይ ሰራዊት ለትግራይ ህዝብ ህልውና ሲል፤ በተለያዩ ባዕዳውያን ሃይሎች ቅንጅት በሕዝቡ ላይ የተሰነዘረውን የዘር ማጥፋት ጦርነት በመመከት ላይ የሚገኝ፤ ፍትሓዊ ጦርነት የሚያካሂድ ሕዝባዊ ሰራዊት ነው:: ከዚያ ውጭ በማንም ሕዝብ ጋር ቁርሾ የለውም:: ትግራይ ትስዕር ኣላ!