Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30905
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አዳብና በገፈርሳ (በጀፎረ) ገርጊስ! እና ጢያ የመጡት ሙየቶች ! ጉድኮ ነው!!

Post by Horus » 04 Oct 2022, 03:16

ክስታኔ ጎርጊስ አይልም፣ ገርጊስ ነው የሚለው። ይህ ገፈርሳ አዲሳባ ቡራዩ ያለው አይምሰላችሁ ! ሶዶ ጉራጌ አገር ነው ! አሁን ሰዉ ቦታው ለምን ገፈርሳ ተባለ ትሉ ይሆናል።

ገፈርሳ የጉራጌኛ ቃል ነው፣ የአረብኛም ቃል ነው ። በክስታኔ ጉራጌ ቋንቋ ገፈረ ማለት ተወ፣ ለቀቀ ማለት ነው ። አል ጃፋር፣ አል ጋህፋር ማለት መተው ማለት ነው በአረብኛ ።

በመላ ጉራጌ ባህል ለጋራ ጥቅም፣ ግጦሽ፣ ጨዋታ፣ ለቅሶና ሌላም ተግባር የሚተው ሰፊ ቦታ አለ ። ክስታኔ ድሮ ጌፎለ (ጌፎረ) ይለው ነበር ። ባክያርድ እንደማለት ነው። አሁን ዋራን ወይም ግፍትጌ ይሉታል ። ሰባት ቤቶች ጀፎረ የሚሉት ዝነኛ የጋራ ቦታ እንግሊዞች The Common የሚሉት ነው ።

በኦሮሞኛ ሰፊክስ (ቃል ማሰሪያ ገፈረ (ሳ) ይሉታል ለጋራ ጥቅም የተተወ ባዶ ቦታ ማለት ነው ። ያ ነው የገፈርሳ ትርጉም !!! ይህ ጎርጊስ ቤተ ክርስቲያም የሆነ ጀፎረ አጠገብ ተሰራ ማለት ነው ። ያ ነው ገፈሳ ጎርጊስ!

ሌላ እዚህ ቪዲዮ ውስጥ እራሳቸውን ክስታኔም ኦሮሞም አድርገው የሚያዩ ጥቂት ወጣቶች አንዴ ጉራጌኛ አንዴ ኦሮኦምኛ ሲጨፍሩ ይታያሉ። በቃ ያ ነው ጉራጌ ማለት! ግን አንድ ጎረምሳ በግድ ልጅቷን ሎሚዬ ልካተቀበልሽ ለማለት ሲሞክር ያስቆሙታል ! አዳብና ዱርዬ ልጃገረዶችን የሚያሸማቅቅበት በአል አይደለም። ያልስለጠነ አዳብና አይወጣም!

ሌላ ቪዲዮ ላይ ሙየት የሚባሉ በመስቀል ዛር ይያዛቸዋል ተብለው እንደ ላሊበላ የሚዘፍኑና ስጦታ የሚሰጣቸው ትንሽ ማይኖሪቲ አሉ ! እነሱም አዳብና ላይ ቀርበው ይታያሉ ፣ የወሎ ላሊበላዎችን ይመስላል ባህላቸው !!!

Last edited by Horus on 04 Oct 2022, 03:38, edited 5 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30905
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዳብና በገፈርሳ ገርጊስ! ጢያ የመጡት ሙየቶች ! ጉኮ ነው!!

Post by Horus » 04 Oct 2022, 03:27

እነዚህ ሙየት የሚባሉ ትንሽ ማይኖሪቲ ቤተሰብ ናቸው ። እንደ ምታዩት በመልካቸው የማረቆና የዝዋይ ዙሪያ ጉራጌ ኦሮሞ ድብልቅ ሕዝብ ናቸው! ሙየት ማለት በመስቀል ዛር አይነት መንፈስ የሚዛቸውና ከልጃገረዶች ስጦታ የሚሰጣቸው ናቸው ። ሳይኮሎጂስቶች አጥንተዋቸዋል ። ይህው በደስታ ባህላቸውን እየተደስቱ ነው !! ጉራጌ ማለት ያ ነው! ሌላውን ሰው ካከበርክ ትከበራለህ አትረበሽም !


Post Reply