ገፈርሳ የጉራጌኛ ቃል ነው፣ የአረብኛም ቃል ነው ። በክስታኔ ጉራጌ ቋንቋ ገፈረ ማለት ተወ፣ ለቀቀ ማለት ነው ። አል ጃፋር፣ አል ጋህፋር ማለት መተው ማለት ነው በአረብኛ ።
በመላ ጉራጌ ባህል ለጋራ ጥቅም፣ ግጦሽ፣ ጨዋታ፣ ለቅሶና ሌላም ተግባር የሚተው ሰፊ ቦታ አለ ። ክስታኔ ድሮ ጌፎለ (ጌፎረ) ይለው ነበር ። ባክያርድ እንደማለት ነው። አሁን ዋራን ወይም ግፍትጌ ይሉታል ። ሰባት ቤቶች ጀፎረ የሚሉት ዝነኛ የጋራ ቦታ እንግሊዞች The Common የሚሉት ነው ።
በኦሮሞኛ ሰፊክስ (ቃል ማሰሪያ ገፈረ (ሳ) ይሉታል ለጋራ ጥቅም የተተወ ባዶ ቦታ ማለት ነው ። ያ ነው የገፈርሳ ትርጉም !!! ይህ ጎርጊስ ቤተ ክርስቲያም የሆነ ጀፎረ አጠገብ ተሰራ ማለት ነው ። ያ ነው ገፈሳ ጎርጊስ!
ሌላ እዚህ ቪዲዮ ውስጥ እራሳቸውን ክስታኔም ኦሮሞም አድርገው የሚያዩ ጥቂት ወጣቶች አንዴ ጉራጌኛ አንዴ ኦሮኦምኛ ሲጨፍሩ ይታያሉ። በቃ ያ ነው ጉራጌ ማለት! ግን አንድ ጎረምሳ በግድ ልጅቷን ሎሚዬ ልካተቀበልሽ ለማለት ሲሞክር ያስቆሙታል ! አዳብና ዱርዬ ልጃገረዶችን የሚያሸማቅቅበት በአል አይደለም። ያልስለጠነ አዳብና አይወጣም!
ሌላ ቪዲዮ ላይ ሙየት የሚባሉ በመስቀል ዛር ይያዛቸዋል ተብለው እንደ ላሊበላ የሚዘፍኑና ስጦታ የሚሰጣቸው ትንሽ ማይኖሪቲ አሉ ! እነሱም አዳብና ላይ ቀርበው ይታያሉ ፣ የወሎ ላሊበላዎችን ይመስላል ባህላቸው !!!