Page 1 of 1

ቅጫ

Posted: 02 Oct 2022, 02:06
by Horus
በሰባት ቤት ጉራጌ ለፍርድ መቀመጫው ቦታ ዬጆካ ይባላል ። ያ የሸንጎና የጉራጌ ሴናተሮች መሰብሰቢያ ቦታ ነው ። ያስተዳደርና ፍትህ ስርዓቱ የቅጫ ሴራ ይባላል። ቅጫ ምን ማለት ነው? ቅጫ ፣ መቀጫ፣ ቅጣት ወዘተ የሚሉት የፍትህ ጽንሶች ቃል ነው ።

የሰባት ቤት ቅጫ በክስታኔ ቅጥ ይባላል። ቅጥ እኩል፣ ትክክል ፣ (ኢኳል) ማለት ነው ። ሁለት እኩል የሆኑ ነገሮች ቅጥ ለቅጥ ናቸው፣ እኩል ለኩል ናቸው። ስለዚህ ክስ ወይም ካሳ ማለት አንድን ስህተት ከስህተቱ፣ ከወንጀሉ ቅጥ፣ እኩል በሆነ ብያኔ ፍትሃዊ (ጀስት) ማድረግ ማለት ነው። ስለዚህ ቅጣት (ቅጫት) ማለት ፈረንጆች እንደ ሚሉት ፓኒስህመንት ሳይሆን ቅጣት አንድን የተዛነፈ ነገር ቀጥ ማድረግ፣ ትክክል ማድረግ፣ ጀስት ማድረግ፣ ካሳ ማድረግ (መተካት) ማለት ነው ። ካሳ ማለት ምትክ ማለት ነው።

ስለዚህ ሰባት ቤቶች የቅጫ ሴራ ሲሉ ቀላል ነገር አይደለም፤ The Justice System ማለታቸው ነው ። ቅጫ ማለት ጀስቲስ ማለት ነው !!!



Re: ቅጫ

Posted: 02 Oct 2022, 20:37
by Horus