Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Jirta
Member
Posts: 1505
Joined: 30 Sep 2018, 07:07

ለጊዜውም ቢሆን በአፍሪካ ስልጣን የሁሉም ነገር ምንጭ ነው።

Post by Jirta » 01 Oct 2022, 03:15

ለጊዜውም ቢሆን በአፍሪካ ስልጣን የሁሉም ነገር ምንጭ ነው።
ሥልጣን ካለህ የማይንቀሳቀስ የባንክ ገንዘብ ትዘርፋለህ
ሥልጣን ካለህ የማይንቀሳቀስ ቋሚ ንብረት አጥረህ ትሸጣለህ
ሥልጣን ካለህ ሌሎች የጀመሩትን ህንጻ ትወርሳለህ ትሸጣለህ
ሥልጣን ካለህ ሁሉ ያንተ ይመስልሃል ሰብስበህ አትጠግብም
ሥልጣን ካለህ አንተ ያልከው ብቻ ያለማስረጃ ያለ መረጃ ትክክልይ ነው
ሥልጣን ካለህ ትርክቱን ታሪክ፣ ተረቱን እውነት ታደርጋለህ
ሥልጣን ካለህ የሰፈሩ ሹክሹክታ የሀገር መመሪያ ደንብ ይሆናል
ሥልጣን ካለህ ባደባባይ ጥንቆላ ማካሄድ ትችላለህ
ሥልጣን ካለህ እግዚአብሔርንም ዛፍም ባንድ ላይ ታመልካለህ
ሥልጣን ካለህ ከፈጣሪ በፊት ነበርኩ ብትል እንዴት ብሎ የሚጠይቅህ ያለ አይመስልህም
ሥልጣን ካለህ የጠላህውን ሀገር ትወዳለህ
ሥልጣን ካለህ ባለ ሀገሮችን ወራሪ ማለት ትችላለህ
ሥልጣን ካለህ ያል ህግ ንጹሃንን ታርዳለህ/ታሳርዳለህ
ሥልጣን ካለህ ባንክ ታዘርፋለህ
ሥልጣን ካለህ ህገወጥ መሣሪያ ታስታጥቃለህ ህዝብ ታሳርዳለህ
ሥልጣን ካለህ የተቀደሰውን ታጎድፋለህ (ማርከስ እንኳን አትችልም)
ሥልጣን ካለህ ካለፈውም ካሁንም ከሚመጣውም አትማርም
ሥልጣን ካለህ ሁሌም እየገደልክ እያሰርክ የምትኖር ይመስልሃል
ሥልጣን ካለህ ለዘለአለም የምትኖር ይመስልሃል
ሥልጣን ካለህ የምትወርድ አይመስልህም
ሥልጣን ካለህ በሠራዊትህ ትመካለህ ፈጣሪን ትረሳለህ
ሥልጣን ካለህ የምትዋረድ አይመስልህም
ሥልጣን ካለህ ህዝቡ ያላንተ የሚኖር አይመስልህም
ሥልጣን ካለህ ከፈጣሪም ከፍ ብለህ ለመመለክ ያምርሃል
ሥልጣን ካለህ ታሪክ አጥፍተህ ያንተን ታሪክ ለመጻፍ ትታገላለህ
ሥልጣን ካለህ ከህግም ከሀይማኖትም በላይ ነህት አይገዙህም
ሥልጣን ካለህ በአፍሪካ የማይኖሩህ ነገሮች ቢኖሩ ሃፍረት፤ ይሉኝታ፤ ጥበብ፤ አለመጥገብ፤ እንደምትሞት እንደምታልፍ አለማወቅ፤ አለመገንዘብ፤ የህዝብ አክብሮት፤ እናም ሰው መሆንክን መርሳት ነው፡
ብቻ ሥልጣን ይኑርህ እንዳዋረድካቸው እስክ ትዋረድ አንተ ፈጣሪ ነህ ከፈጣሪም በላይ ነህ።