Page 1 of 1

የጉራጌ ጋብቻ አፈጻጸም 5 ደረጃዎችን ላስተዋውቃችሁ በቪዲዮ!!!

Posted: 01 Oct 2022, 01:28
by Horus
ደረጃ አንድ አዳብና (ትውውቅ)፡
ይህ በያመቱ ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 በየሜዳው፣ ገበያው፣ ቤተ ክርስቴን በልዩ ልዩ እስፖርቶች ፈረሰ ጉግስ፣ አጋት (ትከሻ) እላፊ፣ ዝላይ፣ ወዘተ የሚከወን መጠጫጫ መድረክ ነው

ደረጃ ሁለት፣ ቸግ (ፍጥምጥም)
ቸግ ለአማችነት ፈቃድ ሽማግሌ ወደ ሴቷ ቤት ተልኮ እሺታ ከተገኘ የሚደረግ ትልቅ የፍጥምጥም ድግስ ነው !! የወንድ ቤተሰብ ለሴት አባትች ትሎሽ የሚሰጥበት በአል ነው ።

ደርጃ ሶስት፣ እንሾሽላ (ስንብት)
የሙሽሮቹ ቤተሰቦች ልጃቸውን የሚሰናበቱበት (እሱም ሆነ እሷ ትዳር ይዘው ከቤተሰብ መውጣታቸው ስለሆነ) ከሰርጉ 2 ወይም ሶስት ቀን ቀደም ብሎ በየሙሽራው ቤት የሚደረግ ትልቅ በአል ነው ።

ደርጃ አራት፣ ሸባል (ሰርግ)
ዛሬ ነው እንጂ ድሮ አገር ቤት ሰርግ ካለ ያገሬ ጎረምሳ መጋበዝ አይጠበቅብትም፣ ከሰርግ ቤት ሰርግ ቤት እየዞረ ይበላል ይጨፍራል !


ደራጃ አምስት ፣ አንገት ኧግዳን (መልስ)
መልስ የሚደገሰው በሴቷ ቤት ነው ። መልስ እንዳሁኑ ዘመን በማግስቱ አይደለም ፣ ባልሳሳት ከሳምንት ወይም 15 ቀን በኋላ ነው ።

የአዳብና ቪዲዮ እያያችሁ ነው ። ከታች የቸግ፣ እንሾሽላና ሸባል ቪዲዮዎች አሳያችኋለሁ!!!

Re: የጉራጌ ጋብቻ አፈጻጸም 5 ደረጃዎችን ላስተዋውቃችሁ በቪዲዮ!!!

Posted: 01 Oct 2022, 01:39
by Horus
አዳብና


Re: የጉራጌ ጋብቻ አፈጻጸም 5 ደረጃዎችን ላስተዋውቃችሁ በቪዲዮ!!!

Posted: 01 Oct 2022, 01:59
by Horus
ቸግ የዛሬ ሁለት ሳምንት

Re: የጉራጌ ጋብቻ አፈጻጸም 5 ደረጃዎችን ላስተዋውቃችሁ በቪዲዮ!!!

Posted: 01 Oct 2022, 02:13
by Horus
የጉራጌን ታታሪነትና ስኬት የመጨረሻው ምሳሌ የሳሙኤል ታፈሰ ልጅ እንሾሽላ !!

Re: የጉራጌ ጋብቻ አፈጻጸም 5 ደረጃዎችን ላስተዋውቃችሁ በቪዲዮ!!!

Posted: 01 Oct 2022, 02:25
by Horus
ሸባል (ሰርግ) ...
መልስ ቪዲዮ የለኝም)