Natnael Mekonnen
ከአሸባሪው የህወሓት አመራር ታደሰ ወረደ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የማነ አብርሃም ካሳዬ እና አለም አምቤ አረኣ የተባሉ ከአሸባሪው ህወሓት አመራር ታደሰ ወረደ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች፤ የሶማሌላንድና የሱዳን ዜግነት ካላቸው ሁለት ሴቶች ጋር ቦሌ ወረዳ 3 ኤድናሞል አካባቢ ቪድዮ ሲቀርጹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ምንጮች ገልፀዋል፡፡
እንደ ምንጮቹ ገለፃ፤ ግለሰቦቹ ከአሸባሪው ህወሓት መረጃ የመሰብሰብ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው የሚጠቁሙም ፍንጮች ተገኝተዋል፡፡ በተለይ የማነ አብርሃም ካሳዬ የተባለው ሰሚት ኮንዶሚኒየም የሚኖር የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጥ ግለሰብ፤ ታደሰ ወረደን ጨምሮ ከሌሎችም የአሸባሪው ቡድን አባላት ጋር የነበረውን የስልክ ግንኙነት የሚያረጋግጥ መረጃ ተገኝቶበታል፡፡ በተደጋጋሚም ወደ ሱዳን ካርቱም ይመላለስ እንደነበር ታውቋል፡፡
ከሶማሌላንድ እና ከሱዳን ካርቱም መስከረም 19 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ የገቡት የሁለቱ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ሴቶችም ከየማነ አብርሃም ካሳዬ እና አለም አምቤ አረኣ ጋር እንዲገናኙ ያመቻቸው በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሰራ ግለሰብ መሆኑን እነ የማነ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተደረገ ምርምራ መታወቁን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
-
- Senior Member+
- Posts: 33225
- Joined: 26 Feb 2016, 13:04