Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12606
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Shocking : ለኢሬቻ የምኒልክ ሐውልት በኦሮሚያ ባንዴራ አሸበረቀ

Post by Thomas H » 29 Sep 2022, 21:55

የምኒልክ ሐውልት በኦሮሚያ ባንዴራ አሸብርቆ መታየት የኦሮሞዎችን ቁስል ማጣጣል ነው





ለነፍጠኞች ይሄ ትልቅ ድል ነው:: ጭራሽ የምኒልክ ሐውልት ላይ የኦሮሚያ ባንዴራ መታየት የለበትም እያሉ ነው







Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11713
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: Shocking : ለኢሬቻ የምኒልክ ሐውልት በኦሮሚያ ባንዴራ አሸበረቀ

Post by Noble Amhara » 29 Sep 2022, 21:59



Opdo's Gada Flag (🖤❤️🤍) is actually from Amhara region traditional kemis :lol: : :mrgreen: :mrgreen:

sun
Member+
Posts: 9324
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: Shocking : ለኢሬቻ የምኒልክ ሐውልት በኦሮሚያ ባንዴራ አሸበረቀ

Post by sun » 29 Sep 2022, 22:05

Thomas H wrote:
29 Sep 2022, 21:55
የምኒልክ ሐውልት በኦሮሚያ ባንዴራ አሸብርቆ መታየት የኦሮሞዎችን ቁስል ማጣጣል ነው


ለነፍጠኞች ይሄ ትልቅ ድል ነው:: ጭራሽ የምኒልክ ሐውልት ላይ የኦሮሚያ ባንዴራ መታየት የለበትም እያሉ ነው

So what is the problem here, when the egalitarian and democratic Irrechaa is all about positivism, happiness, being together, healing wounds, enjoying life together and seeing the bright light just in front of your nose regardless of who you think of yourself and who you really are.



Thomas H
Senior Member
Posts: 12606
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Re: Shocking : ለኢሬቻ የምኒልክ ሐውልት በኦሮሚያ ባንዴራ አሸበረቀ

Post by Thomas H » 29 Sep 2022, 22:35

So what is the problem here, when the egalitarian and democratic Irrechaa is all about positivism, happiness, being together, healing wounds, enjoying life together and seeing the bright light just in front of your nose regardless of who you think of yourself and who you really are.


አንተ ደግሞ ዝም ብለህ egalitarian and democratic Irrechaa እያልክ ትቀባጥራለህ :: ነፍጠኞች አዲስ አበባ እንዳይገቡ ለምን ተከለከሉ ?
"አዲስ አበባ አትገቡም ተብለን ተባረርን
ገለታው ዘለቀ
ቤተሰብና አብሮ አደጎቼን ለመጠየቅ ሰሜን ሸዋ መሃል ሜዳ ከተማ ውዬ አደርኩና አዲስ አበባ መመለሻዬ ደረሰ። ስለሆነም ትናንትና የአውቶቡስ ትኬቴን ቆርጬ ዛሬ ማለዳ ወደ አውቶቡስ ተራ አቀናሁ። የአውቶቡሱ ረዳት ትኬት የቆረጥነውን ሁሉ ቦታ ቦታችንን እንድንይዝ አድርጎ ገና ጎህ ሳይቀድ አውቶቡሱ ወደ አዲስ አበባ መጓዜ ነው ለማለት ዳፉ.... ዳፉ ....ዳፉ......ማለትን ያዘ።
አውቶቡሱ መንቀሳቀስ ሲጀምር ረዳቱ እንዱህ አለ።
ጉዟችን በኤፌሶን፣ በሸዋሮቢት በደብረ ሲና አድርጎ ነው።
ረዳቱ እንዳለውም ያንን ጠመዝማዛ ዳገታማ መንገድ ተያያዝነው። ታዲያ በመጓዝ ላይ ሳለን ከእኔ ፊት ከተቀመጠች አንዲት ወጣት ዘንድ ስልክ አቃጨለ። ይህቺ ወጣት ስልክ አንስታ ስታወራ ድንጋጤ ስለታየባት የአካባቢውን ሰው ትኩረት ሳበች።
ምን ተፈጠረ ? አለ አንዱ
አይ ወደ አዲስ አበባ መግባት አይቻልም አሉ አለች እያዘነች።
ሁላችንም ተደናገርን። ወሬው እየዘለለ ሄዶ ሹፌሩ ዘንድ ቢደርስም ከፍጥነቱ ቅንጣት አልገታውም። ይህቺ ይህንን ክፉ ዜና ያመጣች ወጣት ደጋግማ እየደወለች ታረጋግጣለች። ይሁን እንጂ አውቶቡሱ አሁንም ጉዞውን ቀጥሏል።
አይደረስ የለም ሽኖ ከተማ ልንገባ ስንል ለፍተሻ ቁሙ ተባልን። አውቶቡስ ሲቆም አንድ ሁለት ወታደሮች ወደ ውስጥ ገቡና
ወሎ አለ....ወሎ አለ.... ሲሉ ጠየቁ።
ሁላችንም የመጣነው ከመንዝ መሃል ሜዳ ስለሆነ ተሳፋሪው በአንድ ድምፅ
የለም፣ የለም፣ የለም፣ ከመንዝ ነን አሉ።
አስር ጊዜ ወሎ ወሎ የሚሉት ከወሎ የመጣ መኪና ጥያቄ የለውም ይመለሳል ለማለት መሰለኝ።አፍንጫን ሲመቱት አይን ያለቅሳል እንዲሉ በርግጥ ይህ አባባላቸው ያበሳጨን ብዙዎች እያጉረመረምን ሳለ፣ ውረድ..... የሚል ቀጭን ትእዛዝ ተሰጠን።
ሁላችን ከአውቶቡሱ ወርደን ተፈተሽንና ጉዞ እንድንቀጥል ስለተፈቀደ ጉዞ ስንጀምር ብዙ ሰው አዲስ አበባ የመግባት ተስፋው ለመለመ መሰለኝ ጨዋታ ደራ። ይሁን እንጂ ረዳቱ ግን ጭንቀት ይታይበት ነበር።
ሾፌሩ ያንን አውቶቡስ እያበረረ ሲሄድ አለልቱ ስንደርስ ለፍተሻ ቆምን። አንዳንድ ህፃናት የያዙ ሴቶች እባክህ አምላካችን በሰላም አግባን እያሉ ሲያማትቡ ይታያል። በመሃል አንድ ወታደር ገባና.....
ወሎ አለ፣ ወሎ አለ፣ ወሎ አለ እያለ ያማትራል።
ሁሉም በአንድ ድምፅ መሃላ እየጨመሩ
ወሎ የለም፣ ከመሃል ሜዳ ነው....ከመሃል ሜዳ ነው ይላሉ።
እነዚህ የኬላ ጠባቂዎች ይህንን የወሎን ስም እንደገና ሲጠሩ ስንሰማ ተንጫጫን። ትንሽ ሳንቆይ ውረዱ ተባልንና በጨዋነት ወረድን። በዚህ ጊዜ ከተሳፋሪዎች መሃል የአዲስ አበባ መታወቂያ የያዙት በኬላው ጠባቂ አዛዥ ጫማ ስር ወድቀው ፅኑ ልመና ገቡ።
የተቀሩት ህጋዊ መታወቂያ ያለን ነን.... ንፁህ ጨዋ ዜጎች ነን.... ወንጀለኛ ካየን አጋልጠን የምሰጥ ነን.....እያሉ ይማፀናሉ።
እኔም በበኩሌ ፓስፓርት መያዜንና ፓስፓርት ደግሞ ለዚህ ለሃገር ቤት የውስጥ ዝውውር ቀርቶ በመላው አለም ለመጓዝ የሚያስችል ከፍተኛ መታወቂያ ነው እያልኩ ለማስረዳት ብሞክር ከቶውንም ጠቀሜታ እንደሌለውና ርባና የሌለው ነገር እንደሆነ አንዱ ወታደር ገለፀልኝ።
ተሳፋሪዎች ልመና ባበዙ ጊዜ የኬላው ሃላፊ ተቆጣ። ሹፌሩን አሽቆጠቆጠው። ሌላው ወታደር አንዲት ጥቁር ላስቲክ የለበሰች የሽቦ ዱላ አምጥቶ መደብደብ ሲጀምር አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ መኪናችን ውስጥ ገባን።
ሾፌሩ እሳት ጎርሶ መሪውን ወደ መጣንበት አዞረ። እንዳዞረ ትንሽ በማቆሙ አንዳንዶቻችን ዘለን ወረድን።
እኔ በበኩሌ ጥያቄ አቀረብኩ።
አንድ የትራፊክ ልብስ የለበሰ ሰው አገኘሁና።
ለመሆኑ ጥፋታችን ምንድን ነው አልኩት።
መልስ አልሰጠኝም።
እሺ ይሁን ለመሆኑ መቼ ነው ወደ አዲስ አበባ መግባት የምንችለው? ብዬ በትህትና ጠየኩ። አጭር መልስ ሰጠኝ። ከመስከረም 23 በኋላ......።
አንዱ ወታደር ወዲያው ወደ አውቶቡሱ ገብተን እንድንቀጥል ዱላውን እያወዛወዘ ትእዛዝ ስለሰጠን ወደ መጣንበት ጉዞ ጀመርን። ብዙዎች ተጓዦች ወዴት እንደሚሄዱና ምን እንደማያደርጉ ጨንቋቸው ይታያል።
በጉዟችን መሃል የዞኑን አስተዳደር ማደሪያ ፈልግ፣ እንዲህ ስንጠቃ ዝምታውስ ምንድን ነው? እንበል የሚል ድምፅ አየለና ከነአውቶቡሳችን ወደዚያው ስናቀና እንደኛው አዲስ አበባ አትገቡም የተባሉ አያሌ መኪኖችንና ተጨማሪ ህዝብ አገኘን። የዞኑ አስተዳደር ከጠዋት ጀምሮ ይህ ችግር እንዳለ እንደሚያውቅ ገልፆ እዚህም እዚያም ግንኙነት ፈጥረን ችግሩን ለመቅረፍ እየጣርን ነው አለ። ለነገ ጠዋትም ቀጠረን።
እኔ ለራሴ በአማራነቴ እንደዚህ ውርደት ተሰምቶኝ አያውቅም። አዲስ አበባን ለማቅናት እኮ መንዜዎቹ ቅድም አያቶቼ የአንበሳውን ድርሻ ይዘዋል። ግን ሁል ጊዜም አዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም የለም፣ አዲስ አበባ የሁላችን ናት የሚለውን መርህ ከፍ አድርጌ እኖራለሁ። ዛሬም ነገም ይሄው ነው እምነቴ።
አዳነች አበቤ ሆይ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ እንዳልገባ አድርገሽ የተወሰኑ እቅዶቼን አበላሽተሻል። አሁንም አዲስ አበባ የሁላችን ናትና ልትከለክይን አትችይም። መስቀል በአል ሲከበር፣ ጥምቀት ሲከበር አዲስ አበባ አትግባ የሚባል ነገር እንደሌለ ሁሉ ኢሬቻም ሲከበር ልዬ ነገር ሊኖር አይችልም። እናንተ የኦሮሞ አክራሪ ሃይሎች እሚያኗኑረንን አስቡ። መንዜን አዲስ አበባ እንዳይገባ አድርጋችሁ አትቀጥሉም። ታቀቡ። መታቀብ ጥሩ ነው። ጥጋብ ጥሩ አይደለም። አንድን ህዝብ በማንነቱ ዝውውር መከልከል ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። አንድን ህዝብ እንደ ህዝብ እንቅስቃሴውን መገደብ ከባድ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ወንጀል ነው።
የሆነው ሁሉ ሆኖ አማሮች አዲስ አበባ አትገቡም እየተባሉ ሲጉላሉ፣ ሲያለቅሱ፣ ሲያማርሩ ባየሁ ጊዜ በልቤ የአማራ መንግስት በቁም ሞቷል አልኩ። ትክክል ነኝ በእውነት።

ከGeletaw Zeleke ገጽ የተወሰደ።

Thomas H
Senior Member
Posts: 12606
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Re: Shocking : ለኢሬቻ የምኒልክ ሐውልት በኦሮሚያ ባንዴራ አሸበረቀ

Post by Thomas H » 29 Sep 2022, 23:12

SUN/RON እንደዚህ ብለህ ታውቃለህ ?
ወያላ: ቦሌ ቦሌ ቦሌ ቦሌ ቦሌ ቦሌ
SUN/RON: አንቴ ኦሮፕላን ማረፋ ትኤዳሌ
ወያላ: አልሄድም ቦሌ ቡልቡላ ነው
SUN/RON : ሚን ለዮ ኦሮፕላን ማረፍያ እና ቦሌ ቡልቡላ አንዲ ኮ ኖ

Post Reply