Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ተክለ ጉራጌ፤ 4ቱ የክትፎ አይነቶች

Post by Horus » 29 Sep 2022, 01:39

የጎመን ክትፎ
የትንሹ መስቀል ወይም ደንጌሳት ቀን የሚበላ ነው ። ጎመን ክትፎ አሁን ሆቴል ውስጥ ልክ እንደ ብርንዶና ስልስ ይገኛል።

ብርንዶ
ይህ እጅግ በከፍተኛ ደረጃ በመላ ኢትዮጵያና አለም የታወቀው እና ከዶሮ ወጥ ቀጥሎ የመላ ኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ የሆነው ቀይ (ጥሬ) ክትፎ ነው! ብርንዶ ባማርኛ ቀይ ጥሬ ስጋ ማለት ሲሆን በጉራጌ ቀይ ክትፎ ማለት ነው። ብርንዶ የትልቁ መስቀል ቀን ምግብ ነው!

ስልስ
ስልስ በአማርኛ ጥብስ ክትፎ ወይም ለብለብ የሚባለው ሲሆን ቀይ ጥሬ ስጋ እንደ ብርንዶ ከተከተፈ በኋላ በትንሹ በሳት ተገርፎ ማለት ነው ። ስልስ ከትልቁ መስቀል እስከ መስቀል መዝጊያ እንደየቤቱ ይበላል ።

ትኩል
ትኩል ቅቅል ክትፎ ነው ። ትኩል ከጉራጌ ቤት ውጭ የሚታወቅ ወይም ሆቴል ቤት የሚገኝ አይመስለኝ ። አሰራሩ፣ ስጋ ጎረድ ጎረድ ተደርጎ እስከ ሚገነትር ድረስ ይቀቀላል። ሙክክ ብሎ አይበስልም። ከዚያ ወጥቶ ይበርድና ድብን ብሎ ደቅቆ ይከተፋፍና እንደገና ይቀቀላል። ከዚያም ዉሃው በሙሉ ከተወገደ በኋል እንደ ክትፎ በቅመም በቅቤ ያብዳል ። ትኩል ተበልቶ አይጠገብም ። ትኩል የመስቀል መዝጊያ ምግብ ነው ። ወተክል መቀቀል ማለት ነው ።

የኬር አመት ይሁንልን!!!
ሆረስ ዘክስታኔ


Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ተክለ ጉራጌ፤ 4ቱ የክትፎ አይነቶች

Post by Meleket » 29 Sep 2022, 03:03

Horus wrote:
29 Sep 2022, 01:39
ተክለ ጉራጌ፤ 4ቱ የክትፎ አይነቶች
የጎመን ክትፎ
የትንሹ መስቀል ወይም ደንጌሳት ቀን የሚበላ ነው ። ጎመን ክትፎ አሁን ሆቴል ውስጥ ልክ እንደ ብርንዶና ስልስ ይገኛል።

ብርንዶ
ይህ እጅግ በከፍተኛ ደረጃ በመላ ኢትዮጵያና አለም የታወቀው እና ከዶሮ ወጥ ቀጥሎ የመላ ኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ የሆነው ቀይ (ጥሬ) ክትፎ ነው! ብርንዶ ባማርኛ ቀይ ጥሬ ስጋ ማለት ሲሆን በጉራጌ ቀይ ክትፎ ማለት ነው። ብርንዶ የትልቁ መስቀል ቀን ምግብ ነው!

ስልስ
ስልስ በአማርኛ ጥብስ ክትፎ ወይም ለብለብ የሚባለው ሲሆን ቀይ ጥሬ ስጋ እንደ ብርንዶ ከተከተፈ በኋላ በትንሹ በሳት ተገርፎ ማለት ነው ። ስልስ ከትልቁ መስቀል እስከ መስቀል መዝጊያ እንደየቤቱ ይበላል ።

ትኩል
ትኩል ቅቅል ክትፎ ነው ። ትኩል ከጉራጌ ቤት ውጭ የሚታወቅ ወይም ሆቴል ቤት የሚገኝ አይመስለኝ ። አሰራሩ፣ ስጋ ጎረድ ጎረድ ተደርጎ እስከ ሚገነትር ድረስ ይቀቀላል። ሙክክ ብሎ አይበስልም። ከዚያ ወጥቶ ይበርድና ድብን ብሎ ደቅቆ ይከተፋፍና እንደገና ይቀቀላል። ከዚያም ዉሃው በሙሉ ከተወገደ በኋል እንደ ክትፎ በቅመም በቅቤ ያብዳል ። ትኩል ተበልቶ አይጠገብም ። ትኩል የመስቀል መዝጊያ ምግብ ነው ። ወተክል መቀቀል ማለት ነው ።

የኬር አመት ይሁንልን!!!
ሆረስ ዘክስታኔ

ታታሪው የጉራጌ ማኅበረሰብ፡ የሥራ ትጋቱ ኣብነታዊ መሆኑን እናውቃለን እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች

ከዚህ በተጨማሪውም ወዳጃችን Horus እንዳስቀመጠው፡ የጎመን ክትፎ፡ ብርንዶ፡ ስልስና ትኩል የተባሉ የክትፎ ኣይነቶችን ፈልስፎ ምርጥ ምግብ ለዓለም ኣስተዋውቋል፡ ታታሪው ጉራጌ።

በመሆኑም ለዛሬ ጉራጌ ፈልቆባታል ተብላ በኣፈታሪክ በሚነገርባት በኤርትራዋ የጉራዕ መንደር ኣጠገብ በምትገኘው በትኩል የፈለቀውን የወዲ ትዅልን ሙዚቃ ጋብዘናችኋል። ሙዚቃዎቹ እንደ ጉራጌ ክትፎ እጅግ መንፈስን የሚያረኩና ደስታን የሚፈጥሩ እንደሆነ ይታወቃል። ለዛሬ "ኣዳነዬ ኣንዳነዬ . . . ዓዲ ተቐልቀላና!" የሚለውን ዜማ ፈልጋችሁ ኣድምጡት፡ ኣውዳመት ነውና እትዬ ወደ ኣገርቤት ይምጡና የጥንት የጠዋቱን እየተጨዋወትን በደስታ እናሳልፍ ማለት ነው ትርጉሙ። ወዲ ትኹል እንዳንጐራጐረው! :mrgreen:

ቤነገራችን ላይ ወዲ ትዅል (ተኽለ ክፍለማርያም)፡ "ይከኣሎ!"፡ "ጉዳመኛ ኣምበላዪ" ወዘተ ዬተሰኙ በርካታ ዕጹብ ድንቅ ኤርትራዊ ጀግንነትን የሚያበስሩ ዜማዎችን ያዜመ፡ ኤርትራዊ የነጻነት ታጋይ ነው!

ኬር
:mrgreen:

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ተክለ ጉራጌ፤ 4ቱ የክትፎ አይነቶች

Post by Horus » 29 Sep 2022, 09:36

መለከት፣
ትኩል በኤርትራ ትግርኛ ቋንቋ ትርጉሙ ምንድን ነው? ይልቅስ ለእንጀራ ያለን ቃል አንድ ነው ። በኤርትራ 'ጣይታ' ትሉታላችሁ ። በጉራጌ 'ጣቤታ' እንለዋለን። ጣይታ እና ጣቤታ ጣፊ (ታፕ) ወይም ጤፍ ከሚለው የመጣ ነው። ያው ፒታ ከቅርብ ምስራቅ እስከ ህንድ የሚታወቀው ፒታ ዳቦ ነው ። እንጀራ በመሰረቱ ጥፍጣፋ ዳቦ ነው! ኬር
Last edited by Horus on 29 Sep 2022, 15:30, edited 1 time in total.

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ተክለ ጉራጌ፤ 4ቱ የክትፎ አይነቶች

Post by Meleket » 29 Sep 2022, 10:14

ትግርኛው ከግእዙ የተዋሰው ቃል ይመስላል፡ ኣንዱ መዝገበ ቃላታችን እንዲህ ተርጉሞታል

ትኩል

1. ትኹል፡ ሽኹል፡ ዝተተኽለ፡ ዝተሸኽለ፡ ትኹል (ተኽሊ) ( -ትኩል ዕፅ ውስተ ቤተ ሐማ። መዓርግ ትክልት ውስተ ምድር። ዕፅ እንተ ትክልት ኅበ ሙሐዘ ማይ)። [የተተከለ፡ የተቸከለ፡ እንደ ተክል መሆኑ ነው]

2. (ብ። በዓላት፡ ሕጊ . . . ) ቀዋሚ፡ ቍም፡ ዘይሳተት፡ ዘይተሳታቲ (ዲ. በዓላት ትኩላት)። [በዓላትንና ሕጋጋትንና . . . ወዘተን በተመለከተ ቀዋሚ ወይ ቋሚ፡ የማይናወጥ፡ የማይንሸራተት ወይ የማይቀየር እንደማለት ነው]

3. ሥሩዕ፡ ዝተሠርዐ፡ ዝተወሰነ ዝተረተበ (ዲ. ዲያቆናት እለ ትኩላን ለመልእክተ ቤተክርስቲያን) [ሥርዓት ያለውና፡ በቅጡ የተወሰነ እንደማለት ነው]

ዲ. የ1865ቱ የአውጉስት ዲልማንን ምሳሌ ለማመልከት የገባ ይመስላል።

ትንሽ ከትኩል ቢለይም እንኳ ቃሉ ኣንድ ሌላ መዝገበ ቃላትም "ተክሉ" የሚለውን የግዕዝ ቃል ድዑል በጊዕ ብሎ ተርጉሞታል በትግርኛ። በግ ብሎ ነው የተረጎመው። ያልካት ኣራተኛይቱ ክትፎ እዚህ ላይ ሳትመጣ ኣትቀርም! :mrgreen:

እርግጥ ነው ቋንቋ እየተዋዋሰ፡ እያደገም እየሞተም እየተወለደም ይሄዳል፤ በመሆኑም በትግርኛና በአማርኛ እንዲሁም በጉራጌኛ በወዘተኛም ጭምር ብዙ ተመሳሳይ ቃላት ሊኖሩ ይችላሉ፡ ብለን እንገምታለን፡ በቅጡ ከተጠኑ። . . . !

ኬር!
:mrgreen:

Horus
Senior Member+
Posts: 30914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ተክለ ጉራጌ፤ 4ቱ የክትፎ አይነቶች

Post by Horus » 29 Sep 2022, 15:19

መተከል፣
በጣም አመሰግናለሁ! በጣም ትክክል ነው ያቀረብከው ትርጉምና ስረቃል ። ልነግርህ የምወደው 'ተክለ ጉራጌ' ልክ ከላይ በግዕዝና ትግርኛ ያቀረብከው ነው ። እኔ ተክለ ጉራጌ ያልኩት የጉራጌ ኢንስቲቲዩት ለማለት ነው ። በተለይ በክስታኔ ጉራጌኛ 'ተክላለት' ማለት ተቋም፣ ድርጅት፣ ዝግጅት፣ መሰረት፣ የቆመ ፣ ኢንስቲቱሽን ማለት ነው ።ልክ አንተ እንዳልከው ማለት ነው ። ተክል፣ ትክል፣ ትክል ድንጋይ፣ ወዘተ ። አው ተክሌ እኛም ጋ ተራ ስም ነው ። ያ ተክለ ጉራጌ ያልኩት ነው ።

ትኩል (ቅቅል) የሚለው ግን ስረቃሉ ሌላ ይመስለኛል አላውቀውም ። ስጋ መቀቀል፣ ንፍሮ መቀቀል የምንጠቀመው 'ወተክል' ኤቲሞሎጂው የተለየ ይመሰለኛል ።

ሌላው ቀርቶ ቂጣ መጋደር፣ እንጀራ መጋገር እኛ 'ዋብስል' ነው የምንለው ። ስለዚህ ለመጋገርና ለመቀቀል የተለያዩ ቃላት ናቸው ። ስጋ (በሰር) ዪቲክሉት (ይቀቀላል)፤ ጣቤታ (ጣይታ) ያበስሉት (ይጋገራል)! በሰር ስጋ ነው፣ ባረብኛም በሰር ይመስለኛል። ኧዲ በሰር ኧቲክሉ ማለት እኔ ስጋ እቀቅላለሁ ማለት ነው።

የሚቀጥለው ቪዲዮ ውስጥ የጎመን ክትፎ ተመልከት። ኬር መስቀል!

Post Reply