Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! በሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

Post by Abere » 25 Sep 2022, 16:39

መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! ከበሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

እኔ ለመቀሌ ለ2015 ብርሃ መስቀል መልካም ምኞቴ።

የኢትዮጵያዊነት ፍቅር በልቦናቸው ይብራ። የወያኔ ትህነግ እና የኦነግ-ብልጽግና የጨለማ ስራ ተከስቶ በፊታችሁ ይታያችሁ። የጨለማ ስራ በብርሃን ይገለጣል። የጨለማ ስራ ማለት፥- ሃሰት፤ስርቆት፤ ግድያ፤ ከንቱ ዝሙት፤ ቅናት፤ምቀኝነት ፤ ጦርነት የመሳሰሉት ዕኩይ ስራዎች ናቸው። እነኝህ በብርሃን ማንነታቸው ይከሰታል - እነኝህ የጥል እንጅ የፍቅር ጓደኞች አይደሉም። በትግራይ የአንድ አዛውንት ዕድሜ ያህል እነኝህ ጸረ-ፍቅር ወይም አማራ ጠል የነበሩ የዲያብሊስ ስራዎች ናቸው። የትግራይ ህዝብ ብርሃኑ የሚገለጽለት አማራ ሲወድ ሲያፈቅር ብቻ ነው። ከአማራ ህዝብ ጋር መቆም አለበት። መቀሌ ነጻ የምትሆነው የአማራን ህዝብ ትግል በመደገፍ እና ከአማራ ጋር በይቅርታ መኖር ብቻ ነው። ያ እስካልሆነ ድረስ እኔ ለትግራይ የሚታየኝ የድቅድቅ ጨለማ የባርነት ዘመን ነው። ገዥውም ኦነግ ኦሮሙማ ነው። በቅናት፤በክፋት እና በበቀል ስሜት የሚነዳ የመንጋ ወይም ኬኛ አስተዳደር። ጦርነት ግጭቱን የውታፍ ነቃዩን ጩኸት ባሻገር ሌላ የሚሰማ እውነት አለ - ስለ ጅቡ ኦሮሙማ የሚናገር።

Horus
Senior Member+
Posts: 30666
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! በሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

Post by Horus » 25 Sep 2022, 18:50

አበረ፣
ይህ ዉጊያ ሲጀመር ብዬ ነበር። አቢይ አህመድ ይህ ነው የሚባል ትጽኖ በትህነግም ሆነ በትግሬ ጉዳይ ሊኖረው ከፈለገ ገብቶ በመላ ትግሬ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ማቆም አለበት ብዬ ነው ። ደሞ ያቢይ አላማ ያ ከሆነና ያን ካደረገ ክዚህ በኋላ የትግሬ ችግርና ቀውስ ባለቤት ይሆናል። የሚመስለኝ አቢይና ኢሳያስ ትግሬ ገብተው መንግስት ካላቆሙ የትህነግ ጠብ ጫሪነት ስለማይቆም ባንድ በኩል ካየሀው ሌላ ምን አማራጭ አላቸው? ገብቶ ትግሬን መያዙ ኤርትራን በግጁ ያስደስታል። አማራም ከትግሬ ዝርፊያ ያርፋል ። ግን ትግሬዎቹ እስከ መጨረሻው ያቢይ ራስ ምታት እንደ ሚሆኑ ጠብቅ ። ለዚህ ሁሉ ቀጥተኛውና ስር ነቀሉ መፍትሄ አንተም እኔም ስንል እንደ ነበረው ፓርላማ ተብዬውን ሰብስቦ በነጋሪት ጋዜጣ እነዚህ ክልል የትባሉ የወያኔ መዋቅሮችን ማፍረስ ነው ። ያ የማይሆነው አሁን ላይ ክልል ፈላጊ ዋናው ኦሮሞ ነው። ትህነግ አገር ለመሆን ክልልና አንቀጽ 39 ይፈልጋል የሚባለው አሁን ግዜ አልፎበታል ። ያ ላሜሪካኖች ምንም ጥቅም ስለሌለውና ሩሲያ ምንግዜም ስለማትፈቅድ ትግሬ አገር የሚሆንበት እድል ተዘግቷል ። አሁን ያ የግብጽ ብቻ ህልም ነው ። ስለዚህ ዛሬ ክልል የትግሬ ቁልፍ ጥያቄ አይመስለኝ፣ ኦሮኦ\ሞች ግን በጣም ይፈልጉታል ፣ እነሱ ገና አዳዲስ ኦሮሞ መር ክለስተር ክልሎች ፈጥረው ትግሬ ታላቅ ትግሬ ይል እንደ ነበረው ኦሮሞችም ያ ህልም እንዳላቸው ስለምናውቅ ማለት ነው ! የድርድር ሚዛን መያዣ የሚባለው ፌክ ነው ። ምንድን ነው የድርድሩ ጭብጥ? ትግሬ አቢይ ይውረድ እያሉ ነው። አቢይ ትግሬ ትጥቅ መፍታት አለበት እያለ ነው ። እናሳ ምንድን ነው ሌላው መለስተኛ መደራደሪያ?

Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! በሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

Post by Abere » 26 Sep 2022, 10:03

ሆረስ፤

ባቀረብከው ሃሳብ እኔም እስማማበታለሁ። መቀሌን መያዙ ብቻ በቂ እርምጃ አይሆንም -ጊዜያዊ ነው። ትግሬ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ለዐብይ መንግስት እራስ ምታት ሁነው ይቀጥላሉ። ኦነግ ክልል ስለፈለገ ሌሎች ሊሰቃዩ አይፈልጉም። ስለዚህ ዘላቂው መፍትሄ አንተ የጠቀስከው ነው።< ፓርላማ ተብዬውን ሰብስቦ በነጋሪት ጋዜጣ እነዚህ ክልል የትባሉ የወያኔ መዋቅሮችን ማፍረስ ነው ።> ከዚህ ውጭ የጦርነቱ ውጤት እዘጭ እዘጭ ብቻ ሁኖ ይቀራል።

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! በሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

Post by Wedi » 26 Sep 2022, 10:13

Horus wrote:
25 Sep 2022, 18:50
ይህ ዉጊያ ሲጀመር ብዬ ነበር። አቢይ አህመድ ይህ ነው የሚባል ትጽኖ በትህነግም ሆነ በትግሬ ጉዳይ ሊኖረው ከፈለገ ገብቶ በመላ ትግሬ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ማቆም አለበት ብዬ ነው ። ደሞ ያቢይ አላማ ያ ከሆነና ያን ካደረገ ክዚህ በኋላ የትግሬ ችግርና ቀውስ ባለቤት ይሆናል። የሚመስለኝ አቢይና ኢሳያስ ትግሬ ገብተው መንግስት ካላቆሙ የትህነግ ጠብ ጫሪነት ስለማይቆም ባንድ በኩል ካየሀው ሌላ ምን አማራጭ አላቸው? ገብቶ ትግሬን መያዙ ኤርትራን በግጁ ያስደስታል።
አይ Horus መቀሌን መያዝ እና መቀሌን ማስተዳደር እኮ የተለያዮ ነገሮች ናቸው፡፡ መቀሌን ለመያዝ ለማይዝ እማ እኮ አብይ ሙሉ ትግራይ ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ ማስተዳደሩ አልሆንለት ብሎ ጥሎ ወጣ እንጅ!!
Last edited by Wedi on 26 Sep 2022, 11:00, edited 1 time in total.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! በሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

Post by Sam Ebalalehu » 26 Sep 2022, 10:50

wedi አሁን ነገሮች ይለወጣሉ። አጎትችህ ይቀፈደዳሉ። ከዚያ በሃላ አብረን እናያለን " ማስተዳደር" ከባድ መሆኑን አለመሆኑን።

Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! በሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

Post by Abere » 26 Sep 2022, 11:14

መቀሌን መያዝ ወይም ትግራይን መቆጣጠር ጊዜያዊ ነው ማለት የጦርነቱ ድብድብ የዕረፍት ሰአት ፊሽካ ተነፍቶ ለድጋሜ ዙር የተጫዋች ቅያሬ ተደርጎ እንደገና ይቀጥላል ማለት ነው። ክልል የሚባለው የጫወታው ኳስ ፈንድቶ ካልተቀደደ ትግሬ ብቻ ሳይሆን በርካታ ተጫዎቾች ሜዳውን ያተራምሱታል። ያን ጊዜ የኦሮሙማ እና የወያኔ ስታድየም ይደረመሳል። ይህ ሳይሆን ክልል የሚባለው አሁን የኦነግ የግል ትኩሳት ብቻ የሆነው ቢሰረዝ ይሻላል። ወያኔ 0 ለ 5 በሆነ ውጤት ከኦነግ-ብልጽግና ጋር ለዕረፍት ቢወጣ ኦነግ አሸነፈ ማለት አይደለም። የመንጋ ጭፈራ ነው።

Abere wrote:
26 Sep 2022, 10:03
ሆረስ፤

ባቀረብከው ሃሳብ እኔም እስማማበታለሁ። መቀሌን መያዙ ብቻ በቂ እርምጃ አይሆንም -ጊዜያዊ ነው። ትግሬ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ለዐብይ መንግስት እራስ ምታት ሁነው ይቀጥላሉ። ኦነግ ክልል ስለፈለገ ሌሎች ሊሰቃዩ አይፈልጉም። ስለዚህ ዘላቂው መፍትሄ አንተ የጠቀስከው ነው።< ፓርላማ ተብዬውን ሰብስቦ በነጋሪት ጋዜጣ እነዚህ ክልል የትባሉ የወያኔ መዋቅሮችን ማፍረስ ነው ።> ከዚህ ውጭ የጦርነቱ ውጤት እዘጭ እዘጭ ብቻ ሁኖ ይቀራል።

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! በሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

Post by Za-Ilmaknun » 26 Sep 2022, 12:52

Wedi wrote:
26 Sep 2022, 10:13
Horus wrote:
25 Sep 2022, 18:50
ይህ ዉጊያ ሲጀመር ብዬ ነበር። አቢይ አህመድ ይህ ነው የሚባል ትጽኖ በትህነግም ሆነ በትግሬ ጉዳይ ሊኖረው ከፈለገ ገብቶ በመላ ትግሬ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ማቆም አለበት ብዬ ነው ። ደሞ ያቢይ አላማ ያ ከሆነና ያን ካደረገ ክዚህ በኋላ የትግሬ ችግርና ቀውስ ባለቤት ይሆናል። የሚመስለኝ አቢይና ኢሳያስ ትግሬ ገብተው መንግስት ካላቆሙ የትህነግ ጠብ ጫሪነት ስለማይቆም ባንድ በኩል ካየሀው ሌላ ምን አማራጭ አላቸው? ገብቶ ትግሬን መያዙ ኤርትራን በግጁ ያስደስታል።
አይ Horus መቀሌን መያዝ እና መቀሌን ማስተዳደር እኮ የተለያዮ ነገሮች ናቸው፡፡ መቀሌን ለመያዝ ለማይዝ እማ እኮ አብይ ሙሉ ትግራይ ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ ማስተዳደሩ አልሆንለት ብሎ ጥሎ ወጣ እንጅ!!
It is possible that administering that Region could be a huge problem for the Gov't. However, all other options are nearly committing a suicide. TPLF could be mounting a gorilla warfare for sometime. But this is much less of a menace than fighting a conventional war against a million militia that is armed and supported by the West, UN, Egypt and Sudan. Jal Abiy has to be so determined and follow the bandits to the gate of hell and finish them off once and for all and, fix the political sphere that is enabling for the breading of such extremism. Otherwise, if this war drags on and the existing tribalism keeps growing, he will be swept outta his wobbling throne by none other than his own OLF :mrgreen:

Horus
Senior Member+
Posts: 30666
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መቀሌ ነጻ ለመውጣት ዋዜማ ላይ ነች ይባላል። ከዘመነ ትህነግ ወደ ዘመነ ኦነግ-ብልጽግና ማለት ይሆን?! በሰበሱ አይቀር ጥምብት ነው ማለት ይሄ ነው።

Post by Horus » 26 Sep 2022, 13:15

Za-Ilmaknun wrote:
26 Sep 2022, 12:52
Wedi wrote:
26 Sep 2022, 10:13
Horus wrote:
25 Sep 2022, 18:50
ይህ ዉጊያ ሲጀመር ብዬ ነበር። አቢይ አህመድ ይህ ነው የሚባል ትጽኖ በትህነግም ሆነ በትግሬ ጉዳይ ሊኖረው ከፈለገ ገብቶ በመላ ትግሬ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ማቆም አለበት ብዬ ነው ። ደሞ ያቢይ አላማ ያ ከሆነና ያን ካደረገ ክዚህ በኋላ የትግሬ ችግርና ቀውስ ባለቤት ይሆናል። የሚመስለኝ አቢይና ኢሳያስ ትግሬ ገብተው መንግስት ካላቆሙ የትህነግ ጠብ ጫሪነት ስለማይቆም ባንድ በኩል ካየሀው ሌላ ምን አማራጭ አላቸው? ገብቶ ትግሬን መያዙ ኤርትራን በግጁ ያስደስታል።
አይ Horus መቀሌን መያዝ እና መቀሌን ማስተዳደር እኮ የተለያዮ ነገሮች ናቸው፡፡ መቀሌን ለመያዝ ለማይዝ እማ እኮ አብይ ሙሉ ትግራይ ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ ማስተዳደሩ አልሆንለት ብሎ ጥሎ ወጣ እንጅ!!
It is possible that administering that Region could be a huge problem for the Gov't. However, all other options are nearly committing a suicide. TPLF could be mounting a gorilla warfare for sometime. But this is much less of a menace than fighting a conventional war against a million militia that is armed and supported by the West, UN, Egypt and Sudan. Jal Abiy has to be so determined and follow the bandits to the gate of hell and finish them off once and for all and, fix the political sphere that is enabling for the breading of such extremism. Otherwise, if this war drags on and the existing tribalism keeps growing, he will be swept outta his wobbling throne by none other than his own OLF :mrgreen:
ወገኖች፣
አሁንኮ ብዙ ነገር ግልጽ እየሆነ ነው ። አሁን ባለው ሞዴል መሰረት አንድ ብሄረሰብ የራሱን አገር በድንበር አጥሮ ይዞ ማ ዕከላዊ መንግስትን እስከ ማስወጣት ደርሷል ። የቴሪቶሪያል ልዕልና ትግል ነው ። ጥያቄው የመሬት ባለቤትነት ነው ። ያገሩን መሬት ለጎሳዎች ከፋፍሎ ባለቤት ያደረገው ስርዓት መሬት የመንግስት ነው ወይም የኢትዮጵያ ነው የሚለው ፌክ ምክኛት ነው ። የትግሬ መሬት፣ ያማራ መሬት፣ የኦሮሞ መሬት የሚለውን መሰረት ከፈረሰ የሚቀሩት ችግሮች ሁሉ የተለያዩ ጎሳ ግለሰቦች እንዴት ማንኛውንም ሪጅን ውስጥ መኖርና መስራት ይችላሉ የሚለው ቀላል ያስተዳደር ሳይንስ ይሆናል ማለት ነው ።

አሁን ያለው የክልል መንግስት በራሱ ክልል መሬትና ድምበር ላይ ልዑል እስከ ሆነ ድረስ አቢይ አህመድ የትግሬን ችግር ሊፈታ አይችልም። ተመሳሳይ ችግር ነገ ሱማሌ ኦሮሞ አማራ ደቡብ ይፈነዳል ። መንግስት አማራጭ ያጣው የዘውግ ሞዴል መጨረሻ ጫፍ ላይ ስለ ደረሰ ነው ። አሁን ወይ ይፈርሳል ወይ ክልል ሁሉ እራሱን የቻለ አገር እንዲሆን መተው ነው !!! ይህን መራራ ሃቅ ነው ምድረ ብልጽኛ የጉቦ ንጉስ ማየት የማይፈልገው። ክልል የነሱ መሬት መሸጫና መክበሪያ ብቸኛ ቢዝነስ ሞዴላቸው ስለሆነ ማለት ነው።

Post Reply