Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10898
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ምፅአተ-ዓለም በኢትዮጵያ -- የ50,000 ነፍሰ በላ ስብሃት ነጋ በነጻነት እግሩን ዘርግቶ ፀሐይ እየሞቀ በዘረፈው ገንዘብ ሲጦር፤ ሰላም እና ዕርቅ ፈላጊው ዘመነ ካሤ ደግሞ እስር ቤት

Post by Abere » 25 Sep 2022, 14:08

ምፅአተ-ዓለም በኢትዮጵያ -- የ 50,000 ንጹሃን ነፍሰ በላ ስብሃት ነጋ በነጻነት እግሩን ዘርግቶ ፀሐይ እየሞቀ በዘረፈው ገንዘብ ሲጦር፤ ሰላም እና ዕርቅ ፈላጊው ቅን ሰው ዘመነ ካሤ ደግሞ እስር ቤት የሚወረወርበት። ታዲያ እንደት ምህረት እና ሰላም በኢትዮጵያ ይወርዳል። በ8ኛው ሺ ወይም በምጽ አተ ቀሪብ አባያው በሬ ተቀምጡ ጎበዙ በሬ ይገረፋል እድሉ ዕድሜንው ሙሉ ሰው በማስጨፍጨፍ እና የአገር ሃብት በመዝረፍ የሚታወቀው ስብሃት ነጋ ከገደል የአፋልጉን የ20 ሚልዮን ወረታ ማስታወቂያ በመስራት ከቋጥኝ እናገደል ስር ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ የተያዘ ከበላኤ ሰብዕ በላይ የገዘፈ ወንጀል የፈጸመ ሰው ነው። በአንጻሩ ደግሞ ብዙሃን ንጹሃን እራሱን ቤዛ አድርጎ አፍላ ዕድሜን የሚታገለው ዐርበኛ ዘመነ ካሴ ክፉን በክፉ አትቃወሙ - ሰላምን ሃብታችሁ አድርጉ በሚለው ሃይማኖታዊ ቃል መንግስት ነኝ የሚለው አካል ለዕርቀ-ሰላም በሽምግልና ሲፈልገው የሰላም ህጂ ባማድረግ ከጫካ ወደ ከተማ ባህር ዳር እርሱን ለሰላም መስዋዕትነት አቀረበ። ታዲያ ገበሬ አባያ እና ቃለ-በላ ዐባይ ስለሆነ እስር ቤት አስገባው። ይህ ሊገርመን አይችልም - ስብሃትን የሚፈታ፤ ለዘመነ ካሴን ተቃራኒውን የሚያደርግ መሆኑ አጠራጣሪ መሆን የለበትም። የሚደንቀው የዘመነ ካሴ የሰላም ጀግንነት ነው። አድናቆቴ ከበፊቱ እጅግ ጨመረ። ዘመነ ካሴ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ በቀኝ የቆመ ንጹህ ጀግና ነው - በጸገማይ ወይም በግራ ለሚቆሙት ግን አዝናለሁ። ሰላም መቸም ጀምበሩ ሊጠልቅባት አይችልም። አሁንም ዘመነን ፍቱ።