Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33101
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

News & Images Of:በአዲስ-አበባ ተደራጅተው ዘረፋና ውንብድና በመፈፀም የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 14 ዓጋመ የሽብር ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ዋሉ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 25 Sep 2022, 11:42

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

ተደራጅተው ከባድ የዘረፋና የውንብድና ወንጀል በመፈፀም የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 14 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ እና አካባቢው ተደራጅተው ከባድ ዘረፋና ውንብድና በመፈፀም የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 14 የሽብር ቡድን አባላትን ባደረገው ከፍተኛ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል ገለፀ፡፡
የከተማው ነዋሪ በስጋት እንዲኖር ከሽብር ቡድኑ ተልዕኮ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ ተላላኪዎችን የመመንጠሩ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ግብረ ሐይሉ አስታውቋል፡፡
የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን ተደራጅተው ከከፈቱብን ዘርፈ ብዙ ጦርነት አንዱ በከተማ የተሸሽጉ ተላላኪዎችን በመጠቀም በለስ ከቀናቸው በገሃድ ካልሆነላቸውም በድብቅ የነዋሪውን ሰላም በማወክ ህብረተሰቡ የደህንነት ዋስትና እንዳይሰማው በማድረግ በመንግስት ላይ ያለውን ዕምነት ማሳጣት ዋነኛ ተልዕኳቸውን ነው ፡፡ ምንም እንኳን በተለያዩ ጊዚያት እኩይ ተግባራቸውን ለማሳካት ቢፍጨረጨሩም በህብረተሰቡ መረጃ ሰጭነትና በፀጥታ ሐይሉ ብርቱ ጥረት በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ይገኛል ፡፡
የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ሐይሉ ሰሞኑን ባካሔደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በአዲሰ አበባ በለሚኩራ ክፍለከተማ እና በሌሎች ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ከባድ ዘረፋና ውንብድናን ጨምሮ የሞባይል ቴክኖሎጂን በመጠቀም በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ሲያዘዋውሩ ከነበሩ አስራ አራት ተጠርጣሪዎች መካከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ
1ኛ ፡-ኤርያስ ሐጎስ
2ኛ ፡- ደሳለኝ ሓዱሽ
3ኛ፡- አያሌው ሐይሌ
4ኛ፡- ታደሰ ጣፈጠ
5ኛ፡- ሐብቶም ወልዱ የተባሉት የዘረፋ ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች 10 የዘረፋና ከባድ ውንብድና ወንጀሎችን የፈፀሙ ሲሆን ግለሰቦቹ ስለፈፀሙት ወንጀል በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠባቸው ከመሆኑም ባሻገር ወንጀል መፈፀማቸውን አምነው ቦታውንና አፈፃፀሙን ለምርመራ ቡድኑ መርተው አሳይተዋል፡፡
ወንጀሉን ለመፈፀም ይጠቀሙበት የነበረ አንድ ሽጉጥ፤ሶስት የብረት መቁረጫ ፤አንድ የብረት መፈልቀቂያ እና ሁለት ከፍተኛ ሐይል ያለው የፓውዛ መብራት እንዲሁም በርካታ ሐሰተኛ መታወቂያዎች ጨምሮ የሚንቀሳቀሱበት ኮድ 1- 17267 የሆነ ሚኒ ባስ ታክሲ በፖሊስ ቁጥጥር የዋለ ሲሆን በተጠርጣሪዎቹ ላይ አስር የምርመራ መዛግብት ተደራጅቶ ምርመራ የማስፋት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በሌላ በኩል መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ከተማ ላይ በማድረግ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በገንዘብ ለማጠናከር ተልዕኮ ተቀብለው ሚስጥራዊ የግንኙነት መስመር በመዘርጋት የሽብር ተልዕኮአቸውን የሚያስተላልፉበት ቻናል 29 የሚባል የቴሌግራም አካውንት በመክፈትና ስማቸው በቀላሉ እንዳይታወቅ በቀለም በማደብዘዝ ሚስጥራዊነቱን ጠብቀው ወንጀሉን ቢፈፅሙም የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ሀይል ባደረገው ብርቱ ክትትልና ጠንካራ ምርመራ ስማቸውንና ለሽብር ዓላማ ማሳኪያ ይጠቀሙበት የነበረውን የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን ማወቅ እንደቻለ ግብረ ሐይሉ አስታውቋል።
ቻናል 29ን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባሩን ሲፈፅሙ ከተገኙት ውስጥ
1ኛ፡- ቤላ ገብረዮሃንስ አብርሃ
2ኛ፡-ግርማይ ተክላይ አብርሐ
3ኛ፡- ፂዮን በርሔ ረዳ
4ኛ፡- ኢክራም አህመድ ሰይድ
5ኛ፡-ትርሐስ እቁባይ ይበይን
6ኛ፡- ሚካኤል ዘርዓይ ወልደ ጊዮርጊስ
7ኛ፡- እሌኒ ተስፋዬ ካሳ
8ኛ፡-ገብረ ህይወት በርሔ ገብረ ሚካኤል
9ኛ፡- ገብረ አምላክ ገብረ መድህን አረጋዊ የተባሉት ተጠርጣሪዎች
ቤላ ገብረ ዮሃንስ አብርሃ በተባለ ግለሰብ ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ለሽብር ቡድኑ ተላልፎ መሰጠቱን ግብረ ሀይሉ ደርሶበታል፡፡
በዚህ የወንጀል ድርጊት ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርምራ እየተጣራባቸው ሲሆን በአጠቃላይ በአስራ አራቱም ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ተግባሩን በማስፋት ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ግብረ ሐይሉ ገልፆል፡፡
ታሪካዊ የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን ልዩ ልዩ ተልዕኮ ሰጥተው ያሰማሯቸውን ተላላኪዎች የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ሀይሉ በሚያደርጋቸው የተሳካ ኦፕሬሽን ሴራቸውን በመቀልበስና ውጤት በማስመዝገብ በቁጥጥር ሥር እያዋላቸው ይገኛል ፡፡
በተለይም በዓላት ሲቃረቡ በድብቅ ተደራጅተው ህገ-ወጥ ተግባርን ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱትን በመቆጣጠር ረገድ የተሰራው ሥራ የተሳካ መሆኑን ግብረ ሀይሉ አስታውሶ ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ ከሐይማኖት አባቶች፤ ከበጎ ፍቃደኛ ወጣቶችንና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶች በማድረግ የፀጥታ ሃይሉ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውሷል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን አከርካሪው ተመቶ ወደ ግብዓተ መሬቱ ሲቃረብ ተላላኪዎቹ መንፈራገጣቸውን እንደማያቆሙ ታውቆ ህብረተሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ እና ለፀጥታ ሀይሎች የሚያደርገውን ቀና ተባባሪነት በመቀጠል የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሀይሉ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡