Ethiopian Broadcasting Corporation
5 h
·
"ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቤታችንን በብርሃን ሊያበራ እና የትውልድ ቅብብሎሽ መሻታችንን እውን ሊያደርግ የተለፋበት ታላቅ ፕሮጀክት ነው" - ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን
የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑንም በመድረኩ ላይ ተናግረዋል
***************
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቤታችንን በብርሃን ሊያበራ እና የትውልድ ቅብብሎሽ መሻታችንን እውን ሊያደርግ የተለፋበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በ77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ለለፉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አድናቆትና ምስጋና ይገባቸዋልም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የገነባችውን ግድብ በሚመለከት በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር በሚደረግ የሦስትዮሽ ድርድር ጉልሕ ተፅዕኖ በማያደርስና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ልዩነቶችን ለመፍታት አሁንም ፅኑ አቋም እንዳላት አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑንም በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፤ ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ የሚደረግ ሌላ አካሄድ ተቀባይነት እንደማይኖረውም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የተናገሩት፡፡
አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል ያሉት አቶ ደመቀ፣ አፍሪካዊያን ጥያቄያችን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ሁልጊዜም ይህን ጥያቄ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡የአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን የሚችለው በፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ተገቢው ውክልና ሲኖራት መሆኑንም አስምረውበታል፡፡
Please wait, video is loading...