Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12614
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Shocking : የአማራ ክልል መንግሥት ወሎዬዎችን ምሥራቅ አማራ እንጂ ወሎዬ አይደላችሁም አለ

Post by Thomas H » 31 Aug 2022, 11:10

ገብርዬ አማራው

ወሎ ወለዬ ነው ጥርት ያለ ማንነት አለው ። ምስራቅ አማራ የሚባል ማንነት የለም !
ወሎ ምስራቅ አማራ ከሆነ ጎንደር ሰሜን አማራ ጎጃም ምእራብ ከማራ ተብሎ ይጠራ
እራሳቸውን ለመግለፅ በኩራት እኔኮ ጎንደሬ ነኝ ወይም ጎጃሜ ነኝ የሚሉ ሰዎች ወሎዬውን በስሙ ለመጥራት ለምን ተፀየፉት ። የወሎ ሰው ወለዬ ነኝ ሲል እንደዛ አይባልም ወለዬነት ጎጠኝነት ነው "ምስራቅ አማራ" ነህ ይሉትና ; ዞር ብለው እኔኮ ኩሩ ጎንደሬ ነኝ ይሉሃል ። ኦቦ ኩሩው በጎንደሬነትህ ማን ላይ ነው የምትኮራው ? ወለዬው ላይ ነው 🙁 ጎንደሬነት የሚያኮራ ነገር ሆነ ወለዬነት እንዴት ማፈርያ እንደሆነ እንድታስረዱኝ እፈልጋለሁ !