Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ይህን ጉድ ስሙልኝ! "ዛሬም ድረስ ለሰላም አማራጮች የተዘረጉ እጆች አልታጠፉም። የተዘረጋው እጅ እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን ያድርግ።" የኢፌዴሪ ኦነግ

Post by Abere » 31 Aug 2022, 08:52

ይህን ጉድ ስሙልኝ! "ዛሬም ድረስ ለሰላም አማራጮች የተዘረጉ እጆች አልታጠፉም። የተዘረጋው እጅ እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን ያድርግ።" የኢፌዴሪ ኦነግ

ለኦሮሞ-ብልጽግና የዐብይ አህመድ ውታፍ ነቃዮች አንድ ጥያቄ አለችኝ። በእውነት የወሎ ክፍለ ሀገር ግማሽ አካል የሆነው ሰሜን ወሎ ከተወረረ 1 ሳምንት ሊሆን ነው፤ በአፋር እንድሁ። ዛሬ ደግሞ በወልቃይት ሁመራ - ታዲያ ይህ ኦነግ ኢፊድሪ መግለጫ በዚህ ወቅት መቅረብ የሚገባው ነወይ? የጦር መሪ ጭንቅላት የጤነኛ ሰው ነወይ? ለዚህ ጦር መሪ የሚያስጨንቀው የትግሬ ነፍስ ብቻ ነወይ? የአማራ ነፍስ የእርሱ ጢባጢቤ መጫዎቻ ነው ማለት ነው። ይህን ዐረፍተ ነገር ጨምሩበት

ወገን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሓት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ ያውጣ ” ይላል የኢፌዴሪ ኦነግ።

በሰው ጭንቅላት የሚጫወተው ኦነግ መራሹ መንግስት የትግራይ ህዝብ ወያኔ መሆኑ ጠፍቶት ነው ወይስ እኛ አናውቅም ብሎ ነው። የመከላከያ ሚንስትር አድርጎ የሾመው ሰው ወያኔ እኮ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር ወያኔ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ኦነግ እንደተ አይነት ብልጣብልጥነት ነው?