Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ሲሚንቶ ገበያ ላይ አለመኖሩ ተገለጸ | የአንድ ኩንታል የሲምንቶ ዋጋ በዚህ 3 አመት ውስጥ ከ 280 ብር ወደ 1,800 መጠቀ

Post by sarcasm » 30 Aug 2022, 11:59

ሲሚንቶ ገበያ ላይ አለመኖሩ ተገለጸ

#Ethiopia | የሲሚንቶ ምርቶችን ግብይት እና ስርጭት ስርዓት የሚደነግገው መመሪያ ከወጣ በኋላ በብዙ ከተሞች የሲሚንቶ ምርቶች አለመኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከተጠቃሚዎች እና ከምርት አከፋፋዮች አረጋግጣለች።

ይህ የሆነውም በመመሪያው የተላለፈው የሲሚንቶ ምርቶች ጊዜያዊ የመሸጫ ዋጋ ለነጋዴዎች አዋጭ አይደለም በሚል እንደሆነም ተገልጿል።
ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ለሥርጭቱ የተመረጡ አንድ ወኪል ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ እኔ እንዳከፋፍል የተመረጥኩት ከዞን ከተማ 80 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላለው ማኅበረሰብ ነው።

ይሁን እንጂ ሲሚንቶ እንዳመጣና እንዳከፋፍል የተጠየኩት አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ40 ብር የትራንስፖርት ዋጋ ነው።

ከዚህ ቀደም እንኳን ከ80 ብር በታች ስለማይጫን የትራንስፖርት ዋጋውን ስታስተካክሉ ጥሩኝ ብዬ ትቻቸው ወጣሁ ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
በዚህም እርሳቸው አከፋፋይ ሆነው በተመረጡበት የወረዳ ከተማ ለተጠቃሚው የሚደርስ ምንም ዓይነት የሲሚንቶ ምርት እንደሌለ ነው የተናገሩት።
የሚፈልጉ አካላት ከዞን ከተማ ነው ከመመሪያው ውጪ ከሚሸጥ ሲሚንቶ ከ1 ሺሕ 500 ብር በላይ ገዝተው የሚያስመጡትም ሲሉ ተደምጠዋል።
በመዲናዋ የሚገኝ የአንድ ትልቅ ንግድ ድርጅት ተወካይ በበኩላቸው፣ ድርጅታችን ለኮንስትራክሽን ሥራ የሚያስፈልገውን ሲሚንቶ ለማግኘት ከአከፋፋይ በደብዳቤ ቢጠይቅም ሲሚንቶ የለም የሚል ምላሽ ነው ያገኘው ሲሉ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ለግዥ የሚመጡ ተጠቃሚዎችን ሲሚንቶ የለም ሲሉ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።
የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በመመሪያው የተቀመጠው መሸጫ ዋጋ አዋጭ ባለመሆኑ ሲሚንቶ አላስገባንም የሚል ነው። (አዲስ ማለዳ)

Please wait, video is loading...

Educator
Member
Posts: 2015
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: ሲሚንቶ ገበያ ላይ አለመኖሩ ተገለጸ | የአንድ ኩንታል የሲምንቶ ዋጋ በዚህ 3 አመት ውስጥ ከ 280 ብር ወደ 1,800 መጠቀ

Post by Educator » 30 Aug 2022, 12:12

Here goes prosperity.
sarcasm wrote:
30 Aug 2022, 11:59

Post Reply