Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ዋናው ጉዳይ የወልድያ የደሴ ህዝብ መሰደዱ ሳይሆን ..ህዝቡ መንግስት ላይ ያለው እምነት መሸርሸሩ ነው። የውጭ ዜጋ ሻዕቢያን አስገብቶ ህዝቡን ከዘረፋ ማዳን ያልቻለ ማን ይተማመናል??

Post by sarcasm » 30 Aug 2022, 09:42

By Finfinne Post

የወልድያውን ተወውና የደሴ ህዝብ በባጃጅ ሳይቀር ንብረቱን ይዞ እየተሰደደ ነው። በከተማው ከፍተኛ መጨናነቅ የትራንስፖርት መተረማመስ እየታየ ነው።
በዚህ ሰአት እድለኛ ከሆንክ ነው ትራንስፖርት አግኝተህ የምትጓዘው እሱንም ከአስር እጥፍ በላይ ከፍለህ ... እዚህ ጋር ዋናው መታየት ያለበት ጉዳይ የደሴ ህዝብ መሰደዱ ሳይሆን ..ህዝቡ መንግስት ላይ ያለው እምነት መሸርሸሩ ነው።

በፕሮፖጋንዳም ሆነ በተግባራዊ ስራዎች የመንግስትነት አቅምን መተማመንን መፍጠር አልተቻለም። ጦርነት ቀርቶ የተራ ቀውስ ድምፅ ሲሰማ ህዝቡ መንግስትን አምኖ ከሚቀመጥ መሸሽ አማራጩ ሆኗል።

ደግሞኮ ህዝብ ብቻ አይደለም የሚሰደደው .. የብልፅግና ካድሬውም ፣ የፀጥታ መዋቅሩም ፣ ነጋዴውም ፣ ሌባውም በአጠቃላይ አረጋጊውም ተረጋጊውም ይሰደዳል።

ይህ በጣም አሳሳቢ ነው። መንግስት ሆነህ መታመን ካልቻልክ .. ቀውሶች ሲፈጠሩ ማረጋጋት ሆነ ጠንካራ አመራር መስጠት ካልቻልክ ምኑን መንግስት ሆንክ 😂 ...

ለማንኛውም የብልፅግና መንግስት ደካማ ካደረጉት አንዱ የውጭ ወራሪ ማስገባቱ ፣ ኢ-መደበኛ የፀጥታ አደረጃጀቶችን መፍጠሩ ፣ ቀውሶችን እያየ እንኳን የማያስተካክል ስርዓት መፍጠሩ

የፀጥታ ተቋማት አደረጃጀቱ ብዛት ላይ ብቻ ማተኮሩ ፣ የማንም ተራ ሰዎችን ኮልኩሉ መሰብሰቡ ፣ የሚዲያና የፕሮፓጋንዳ አቅሙ የወረደ መሆኑ ፣ በአጠቃላይ ወሬ ተኮር አደረጃጀት መፍጠሩ ዋነኛው ነው።

የውጭ ዜጋ ኤርትራውያን አስገብቶ ህዝቡን ከዘረፋ ማዳን ያልቻለ እያየ እንኳን እርምጃ ለመውሰድ አቅሙ ያጠረው ስርዓትን ማን ይተማመናል ???

Please wait, video is loading...