Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የትግራይ መንግስት መግለጫ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ሕዝቦች

Post by sarcasm » 30 Aug 2022, 11:46

የትግራይ መንግስት ወቅታዊ መልእክት
=========================


የተከበራችሁ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች

የትግራይ ህዝብ የራሱን ዕድል በራሱን የመወሰን እና ዲሞክራስያዊ መብት ይከበርልኝ ስላለ ብቻ፣ በፋሽስት ኣብዪ ኣህመድ ቡድን እና ሸሪኮቹ ግልፅና ህዝብ የማጥፋት የጆኖሳይድ ዘመቻ በማወጅ፣ በዓለም ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍና በደል፣ እንዲደርስበት ኣድርጓል። የኣምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ስርኣት፣ በዚህ ህዝብ የማጥፋት የጆኖሳይድ ዘመቻ ከፋሽስት አብይ ኣህመድ ቡድን ጋር ዘምተው፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ስፍር ቁጥር የሌለው ግፍና በደል ኣድርሰዋል። እነዚህ ወራሪዎች በትግራይ ሴቶች ላይ በሰው ልጆች ሊፈፀም ይቅርና ሊታሰብ የማይችል ዘግናኝ፣ ከፆታዎ ጥቃት ባሻገር፣ የሆነ ግፍና በደል ፈፅመዋል። የትግራይ ህፃናትና ወጣቶች በጥይት እንዲረግፉ፣ በአጋጣሚ ያመለጡም እንዲበታተኑ በማቀድ ሰርተዋል። በድምሩ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ከገፀ-ምድር እንዲጠፋ፣ የኣዲስ ኣበባና የኣስመራ ስርዓት የሚቻላቸውን ሁሉ ኣድርገዋል። ኣሁንም ቢሆን ካለፈው ጥፋታቸውን ሳይማሩና እስከ ኣሁን ድረስ እየፈፀሙት ያለውን ክህደትና በደል ሳያንሳቸው፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ተጨማሪ ጥፋት ለማድረስ ዝግጅታቸውን ጨርሰው ወደ ተግባር ተሸጋግረዋል።

የተከበርክ የኤርትራ ህዝብ

የአዲስ ኣበባ ፋሽስታዊ ስርዓትና አምባገነኑ የኤርትራ ስርዓት ካሁን በፊት ጀምረው ያልጨረሱትን የትግራይ ህዝብ የማጥፋት ዘመቻ ለመቀጠል በሙሉ ኣቅማቸውን እየሰሩ ይገኛሉ። የዚህ ኣካል የሆነ ፋሽስታዊ የኣብዪ ኣህመድ ቡድን ከነሓሴ 18/2014 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ትግራይ አቅጣጫ ሰፊ ወረራ እያካሄደ ሲሆን ተንደርድሮ የገባውን የጠላት ሃይል፣ በጀግናው የትግራይ ሰራዊት በሚገባ እየተመከተና እንደየኣመጣጡ ዋጋውን እንዲያገኝ እየተደረገ ነው። በዚህ ግንባር የገባው ወራሪ ሓይል ያሰበውን ሊሳካለት ስላልቻለ በምዕራብ ትግራይ ነቁጦ የነበረ ሌላ የፋሽስት ቡድን ሓይል ወደ ኤርትራ ኣሸጋግሮታል። ይህ ደግሞ ከኣምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት በመሆን በኤርትራ ኣቅጣጫ ሌላ የወረራ ግንባር ለመክፈት እንደሆነ ግልፅ ነው።

የኢሳያስ መንግስት ያለፈውን ወንጀልና ክሕደት አልበቃ ብሎት፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ሌላ ተጨማሪ ጥፋት ለመፈፀም እያደረገው ያለው ዝግጅት የሚያሳይ ነው። የኣምባገነኑ ኢሳያስ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲባል፣ በሁሉም መለክያ ወንድማማቾች የሆኑ ህዝቦች ወደማያባራ ቂምና በቀል እንዲገቡ፣ የኤርትራ ህዝብ ሊፈቅድ ኣይገባም። ይህ ደግሞ ለትግራይ ህዝብ ከማሰብና በጎ ከመመኘት ብቻ ሳይሆን ከዘላቂ የኤርትራ ህዝብ ጥቅም ኣኳያ በመመዘን ያለው ጉዳይ ነው።

ስለሆነም፣ የኤርትራ ህዝብ በፋሽስት ኣብዪ ኣህመድና ኣምባገነኑ ኢሳያስ ኣፈወርቂ እየቀረበልህ ያለውን የጥፋት ድግስ፣ መልክ እንዲይዝና በፅኑ ልትቃወም ይገባል። ለዘላቂ ጥቅማችሁና ህልውናችሁ ብላችሁ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ታሪካዊ ወንጀል እንድትቃወሙት፣ ካልቻላችሁ ደግሞ ፍፁም ተባባሪ ልትሆኑ ኣይገባም። የኤርትራ ሰራዊትም ለራስህና ለህዝብህ መሰረታዊ ጥቅም ስትል፣ የእነዚህ የጥፋት ድግስ በፅኑ ልትቃወም ይገባል። የኣምባገነኑ የኢሳያስ ኣፈወርቂ የስልጣን እድሜ ለማራዘም ሲባል በማንኛውም መንገድ ለማይጠቅምህ ጦርነትና ውግያ እየገባህ ህይወትህን እና መጭው ዕድልህ ወደ ከባድ ኣደጋ ማግባት የለብህም።

በተለያዩ የዓለም ኣከባቢ በስደት የምትገኝ ኤርትራውያን፣ እስካሁን ስታደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ፣ በይበልጥ ኣጠናክራችሁ እንድትታገሉና ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ጦርነት አበክራቹ ልትቃወሙት ይገባል። የኣምባገነኑ ኢሳያስ አፍወርቂ የቂም-በቀል ጥማትን ለማርካት ሲባል ለሁለቱም ወንድማሞች ህዝብ ወደ ማያባራ ደማዊ እልቂት እንዲገቡ የሚደረገው እንቅስቃሴ ፍፁም ልትቀበሉትም ኣይገባም።

እኛ ከገፀ-ምድር ለማጥፋት ከተነሱ ኣሃዳውያን እና ፋሽስት ሃይሎች ጥምረት ፈጥረው ከተነሱና ጆኖሳይድ ካወጁብን የኢሰያስ ስርዓት እንጂ፣ የኤርትራ ህዝብ መብትና ጥቅም ለማደናቀፍ ፣ ፍላጎትና ዓላማ የለብንም። ይህ ደግሞ የኣሁኑ ወቅታዊ ኣቋማችን ብቻ ሳይሆን፣ ባለፉት ከ40 ዓመታት በላይ በተግባር እያረጋገጥነው የመጣንና፣ በዚህ ምክንያትም ብዙ ዋጋ የከፈልንበት፣ የማይናወጥ ህዝባዊ ኣቋማችን ነው።

የተከበራቹ የኢትዮጵያ ህዝቦች

የኣብይ ኣሕመድ ስርዓት፣ የትግራይ ህዝብ ከመሰረቱ ለማጥፋት የጀመረው የጀኖሳይድ ዘመቻ አሁንም አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ ያለፈው ጥፋት አልበቃ ብሎት አሁንም በደቡብ ትግራይ በኩል ወረራ በማስቀጠል ሌላ ክሕደት እየፈፀመ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩልም በምዕራብ ትግራይ የነበረ ሓይሉ ወደ ኤርትራ እንዲዞር በማድረግ ከባእድ አገር ከአምባገነን ኢሳያስ ኣፈወርቂ በመሆን ትግራይን ለመውረር ዝግጅቱ አጠናቋል።

ይህ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው ወረራ የአማራ ተስፋፊ ሓይል ጥማትና ፍላጎት ለማርካት ሲባል የሚፈፀም መሆኑን ግልጽ ነው፡፡ የአሃዳውያን ፍላጎት ለማሟላት ሲባል በማይመለከትህና በማይጠቅምህ ጦርነት ልትገባ አይገባም፡፡ ልጆችህም፣ ዓላማቸው የትግራይ ህዝብ ማጥፋትና የትግራይ መሬት መውረርን ማእከል ባደረገ ጦርነት ገብተው እንዲረግፉ መፍቀድ የለብህም፡፡

ይህ ስርዓት ህዝብ ከህዝብ እያፋጀ እና እያዳማ ስልጣኑ እንዲያራዝም ሊፈቀድለት አይገባም፡፡ ራሱ ከባእድ የኤርትራ ሓይል ግንባር በመፍጠር የትግራይ ህዝብ ለማጥፋት ቀንና ሌሊት እየጣረ እያለ፣ መልኩ ቀይሮ “ታሪካውያን ጠላቶቻችን” የሚል አደንዛዥ ሐሳብ በመጠቀም ህዝብ ለማደናገር ላይ ታች እያለ ይገኛል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ አዲስ አጀንዳ ለመፍጠር እየቀረበ ያለ ፕሮፓጋንዳ እንጂ ከኣብይ ኣሕመድ በላይ የባዕድ አገር ስርዓት ተላላኪም ሆነ ቡድን በኢትዮጵያ የለም፡፡ የኣብይ ኣሕመድ ስርዓት የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ ከኤርትራ ጀነራሎች ስር አሰልፎ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋት ሙሉ ዓቅሙ ተጠቅሞ እየሰራ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ህዝብና መንግስት ስማቸውና ተግባራቸው ያልሆነ ጥላሸት ለመቀባት ላይ ታች ሲል ማየት የተለመደ ተግባር ሆኗል፡፡

የትግራይ ህዝብ ከዓፋር ህዝብ ሆነ ከኣማራ ህዝብ የጥቅም ይሁን ሌላ መሰረታዊ ጥላቻ የለዉም፡፡ ከማንም ህዝብም ቢሆን ምንም ዓይነት ጥላቻና ቂም ያለው ህዝብ አይደለም፡፡ በመሆኑም ፋሽሽት የአብይ አህመድ ቡድን የዓፋር እና የአማራ መሬት የጦርነት አውድማ ለማድረግ አልሞ እያካሔደው ያለው ወረራ፣ በተለይ የዓፋርና የአማራ ህዝቦች በሚገባ ልትታገሉት እና ልትቃወሙት ይገባል፡፡ የኣገውና የቅማንት ህዝቦች ዛሬም እንደ ትላንቱ በአቋማቹ ፀንታቹ ለወራሪው ሓይል ልትታገሉት ይገባል፡፡

የኦሮሞ ህዝቦች እንዲሁም ሌሎች ብሔርና ብሔረሰቦች ይህ ስርዓት የራስን እድል በራስ የመወሰን እድል እና ሕገ መንግስት የሚፃረር ስለሆነ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሔደው ያለው የጀኖሳይድ ዘመቻ፣ የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ሂዶ ሂዶ የሁሉም ብሔርና ብሔረሰቦች ፀር መሆኑ በመገንዘብ ቀጣይነት ያለው ለህልውናቹ ስትሉ ይበቀሃል ልትሉት ይገባል፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ ተጥሎ ያለው ከበባና ክልከላ እንዲሰበር እና ወንጀለኞች ወደ ሕግ እንዲቀርቡ በሚደረገው ርብርብ ከትግራይ ህዝብ ጎን ሁናቹ ድጋፋቹ እንድታጠናክሩም የትግራይ ህዝብና መንግስት ጥሪያቸው ያቀርባሉ።

የኢትዮጵያ መከላከልያ ሰራዊትም ለራስህ እና ለህዝቦችህ መሰረታዊ ጥቅም ስትል ለዚህ ወረራ በፅኑ ልትቃወመው ይገባል፡፡ ከባዕድ ወራሪ ሓይል በመሆን በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረስከው ጭፍጨፋና የጀኖሳይድ ዘመቻ ይብቃ አይደገምም ልትል ይገባል፡፡ የፋሽሽት አብይ አህመድ ቡድን ስልጣን ለማራዘም፣ለተስፋፊው የኣማራ ክልል አመራሮች ብለህ በማይጠቅምህ ጦርነትና ውግያ እየገባህ እንደ ቅጠል ልትረግፍ አይገባም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦችም በመከላከያ ሰራዊት ያሉ ልጆችህ ለማይረባ ዓላማ ሲሉ በየጥሻውና ሸንተረሩ ከንቱ እንዳይቀሩ፣ ያለፈውን ሓዘን ይበቃል ብለህ ፈጥነህ ልጆችህን አድን፡፡
የትግራይ ህዝብና መንግስት ጠላቶች የብልፅግና ስርዓት እና ተስፋፊው ኣሃዳውያን ሃይሎች እንጂ ማንም ህዝብ አይደለም፡፡
ይህ የዛሬ እምነት ብቻ ሳይሆን በጦርነት ጊዜና ከጦርነት በኋላም ደጋግመን እያረጋገጥነው የመጣን ሲሆን፣ የጠላቶቻችን ሃይል ለማዳከም ወደ ኣማራና ዓፋር ኣካባቢዎች በተንቀሳቀስንበት ወቅት በተግባር ያረጋገጥነው እምነታችንና አቋማችንም ነው፡፡

ስለዚህ ከመብቱ ውጭ ሌላ ተጨማሪ ጥቅምና ፍላጎት ያልጠየቀ ለኣማራ ተስፋፊ ሓይሎች ፍላጎት ለማሟላት ሲባል፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀው የጀኖሳይድ ዘመቻ እያካሔደው ያለውን የሞትና የሽረት ጦርነት በመረዳት ድጋፋቹ እንድታሳዩ፣ይህ የፋሽሽት ቡድን እያካሔደው ያለውን ወረራ እንዲቆም እና ወደ ነፈገው የሰላም ድርድር እንዲመለስ ጥረት እንድታደርጉ የትግራይ ህዝብና መንግስት ጥሪያቸዉ ያቀርባሉ።

ህልውናችንና ደህንነታችን በክንዳችን!!

ትግራይ ትስዕር!!

የትግራይ መንግስት
ነሓሰ 24/2014 ዓ/ም
መቐለ
Please wait, video is loading...

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12681
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የትግራይ መንግስት መግለጫ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ሕዝቦች

Post by Fiyameta » 30 Aug 2022, 12:03





Begging their master behind the scene to do their cruel, dirty work.... FAILED! We will never forgive, nor forget! :x :x









GOOD NEWS... KARMA IS NOT DONE YET. :mrgreen: :mrgreen:








Post Reply