"ለቁርስ ይሁን ለምን ይሁን ይዘውት የወጡትን ዳቦ ቁጭ ቁጭ ላለው ወታደር ሲያበሉ፤ ውኃ ሲያጠጡ እኔ በዐይኔ አይቻለሁ" የሚሉት የወልድያ ነዋሪ የተማሪዎቹን ሁኔታ "በጣም አንጀት የሚሰብር" ሲሉ ገልጸውታል። ሌላ የወልድያ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው "ትራንስፖርት የለም። ተማሪዎቹ በእግራቸው ለቀው ወጥተዋል" ሲሉ የተመለከቱትን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
በወልድያ ከተማም ይሁን በዙሪያዋ በሚገኙ አካባቢዎች የጦር መሳሪያ የተኩስ ልውውጥ ድምጽ እንደማይሰማ የዐይን እማኞች ይናገራሉ። ይሁንና የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች የሚያደርጉት ውጊያ ነሐሴ 18 ቀን 2014 እንደገና አገርሽቶ ወደ ቆቦ ሲደርስ በወልድያ ነዋሪዎች ዘንድ ሥጋት መፈጠሩን አምስት የዐይን እማኞች ገልጸዋል።
Please wait, video is loading...