Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by sarcasm » 19 Aug 2022, 09:52

ስምንት የመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች ለጨረታ ቀረቡ
*************


ስምንት የመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች ለሀገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፍ ተጫራቾች ለጨረታ መቅረባቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ጉዳዩን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ፣ የግሉ ዘርፍ በስኳር ኢንዱስትሪው የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ መንግሥት በዘርፉ ማሻሻያዎች ማድረጉን አመላክቷል።
የግሉን ዘርፍ በስኳር ልማት ያለውን ተሳትፎና ሚና ለማሳደግ እየሠራ ያለው መንግሥት የዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በስኳር ፋብሪካዎች ጨረታ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።
ለጨረታ የቀረቡት ፋብሪካዎች ኦሞ ኩራዝ 1፣ ኦሞ ኩራዝ 2፣ ኦሞ ኩራዝ 3፣ ኦሞ ኩራዝ 5፣ አርጆ ዴዴሳ፣ ከሰም፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።
ጨረታው እንዲወጣ የተደረገው የስኳር አምራች ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ለማሟላት እንደሆነ ተጠቁሟል።
የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ሟሟላት ስኳር በማስገባት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ እንደሚያስቀር እና የስኳር ምርታማነትን ማሳደግ የሸንኮራ አገዳ አምራቾችን ገቢ በመጨመር የኑሮ ሁኔታቸውን እንደሚያሻሽል ተገልጿል።
ለዘርፉ የሚደረገውን የመንግሥት ወጪ በመቀነስ ዘርፉን ለማስፋፋት እና ለማሳደግ የሚያስችል ገቢ ማመንጨት የሚያስችል ዕድል እንደሚፈጥርም ተጠቁሟል።

h[facebook]ttps://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02Q ... AgFRbeT84l[/facebook]

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by Sam Ebalalehu » 19 Aug 2022, 10:26

" Weyane built." Eden are you suggesting EPDRF was a joke. You are right pretty much although I hate the TPLF cadres assumption everything that was done " proficiently" has been the work of TPLF while every failure shared by EPDRF. People hate dishonesty.
I am glad the Ethiopian government chose to privatize it. The sugar factories had been the means used to enrich TPLF and its high ranking officials.
When Meles was appointed Abay Tsehaye to lead the sugar factories, some people thought it was a demotion because at least for awhile Abay was in Seye Abrha group. No, Meles knew what he was doing. He knew where the money is. That exclusively belongs to TPLF the thinking goes.
By the way where did you get the idea the Ethiopian government needs money from the sugar factories to feed its war machine.
ያልተፃፈ ማንበብ ኑሮሽ አደረግሺው።
The sugar companies in Ethiopia were the most corrupt business, and it should have been privatized awhile ago.

Abere
Senior Member
Posts: 11108
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by Abere » 19 Aug 2022, 10:38

The question is why has not Abiy Ahmed leased land to these so called private investors and develop their own sugar plant and cultivate their own sugar can? Why selling off well developed public property to so called scam private investor? This is an obvious corruption and fraud committed by the government using its position. In a country where the market system is broken, the role of the government in consumers protection and national wealth and assets is critical. Instead of running what has been built by previous governments and facilitate business environment to develop new ones selling off ( even when the government's legitimacy is questionable) is broad day theft. Just like PP-OLF deliberately loaded with millions of cash banks in Wollega so that OLF rebels can generously loot them. This is what is happening now in the name of privatization. The coward people of Ethiopia can not ask this question from experience - hungry people don't ask why the price of bread increased by 400% they would prefer go hungry -empty belly.

TesfaNews
Member+
Posts: 6843
Joined: 14 Feb 2020, 22:23
Location: Ras Mesobawian

Re: Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by TesfaNews » 19 Aug 2022, 10:42

Viva Abiy Ahmed he outsmarted agames Nazis

Horus
Senior Member+
Posts: 30908
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by Horus » 19 Aug 2022, 13:53

አበረ፣
እኔ የተለየ ምልከታ አለኝ። እርግጥ ነው ያቢይ መንግስት የራሱ ፋንሲ ማንሲ ዱባይ አይነት ፕሮጀክቶች ለመስራት ብዙ ቢሊዮኖች ዶላር ስለሚፈልግ ካፒታል (ፈንድ) ለማግኘት እነዚህን በመንግሥት የተያዙ ኢንዱስትሪዎች መሸጥ አለበት ። ያ የነአቢይ ነጂ ፍላጎት ቢሆንም በሌላ በኩል ግን መንግስትን ከንግድ ማስወጣት አንድ ትልቅ የእድገት እርምጃ ነው ።

የመንግስት ሚና ሱካር ማምረትና ሱካር መሸጥ አይደለ። ይህ ነው የቢሮናየመንግስታዊ መሰኛ ኮራፕት ከበርቴ መደብ መፈልፈያ ረግረግ! አው ዛሬ አቢይ ለምን 8 ሱካር ፋብሪካዎችን መቸብቸብ ፈለገ የሚለው ጥያቄ መልሱ አቢይ የጦር መሳሪያ መግዣና ፓርክና ሙዚየሞች መገንቢያ ዶልላር ስለሚፈልግ ነው ። ግን እነዚህ በውያኔ የተጋጡ ኢናኤፊሸንት ሚዲኢቫል ፋፍሪካዎች ለግል ነጋዴ መሸጣቸው ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ።

በአንድ ቃል ፋብሪካዎቹ ትርፋማ ሆነው ለመንግስት ያሰበውን ያክል ዶልላር ማመጨት ስላልቻሉ (ማለትም መንግስት ቢዝነስ ማኔጅመት ስለማይችል) ነው የሚሸጡት እንጂ ጥሩ ማኔጅመንት ይዘው ትርፍ ቢያመጡ በምንም አይነት አቢይ አይሸጣቸውም ነበር ።

ብቻ መንግስት ከነጋዴት በራቀ ቁጥር የፖለቲካ ኮራብሽን ይቀንሳል፣ ይህ ሳይንስ ነው ።

Abere
Senior Member
Posts: 11108
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by Abere » 19 Aug 2022, 14:31

ሆረስ፤

አንተ እንዳልከው በመሰረተ ሃሳቡ ብስማማም ከጊዜ ሰሌዳ ፥ ከአገሪቱ ህዝብ የኑሮ እና የእድገት ደረጃ እንድሁም ከፓለቲካዊ አስተዳደራዊ ብቃት አንጻር ጋር ግን አብሮ አይሄድም ባይነኝ። ወቅቱን ያልጠበቀ፤የቆመበትን ህዝብ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። ህዝባችን ገና sophisticated consumer የመጠቀ ሸማች አይደለም።እነኝህ የግል የሚባሉ ኩባንያዎችም ብዝበዛ እንጅ ማህበራዊ ግደታን (Corporate social responsibility) ከንግድ አገልግሎት ጋር አጣምረው የሚሰሩ አይደሉም በታዳጊ አገር ህዝብ ላይ። ስለዚህ ለጊዜውም ቢሆን መንግስት በነባር ድርጅቶች ላይ ቁልፍ ሚና ሊኖረው ይገባል። ለምሳሌ ምዕራብ አለም ትርፍ ሰብሳቢ የግል ዩኒቨርስቲዎች አሉ፡ የህዝብ ወይም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች አሉ። ምክንያቱም አብዛኛው ህዝብ እንዳይበዘበዝ እና የትምህርት ዕድል እንድ ደርሰው ለማድረግ ሌላው ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም አይነት - የፓለሪካ ስርዐተ መንግስቱ በሙስና የነቀዘ እና የዘቀጠ ከሆነ የህዝብ ንብረት የሆኑት ድርጅቶች ለግል ቢተላለፉም ያው ተጠያቂነት የሌለብት የዘቀጠ አገግሎት እና ብዝበዛ ነው የሚቀጥለው። በሰለጠኑት አለማት ኩባንያዎች ወይም ድርጅቶች በአግባቡ ተጠያቂዎች ናቸው - የቁጥጥር እና የተጠያቂነት ግልጽ መንገድ አለ። ለምሳሌ Security and Exchange Commission (SEC) ውሰድ ስግብግብ ድርጅቶችን አሰራር በደንብ ይፈትሻሉ። የወል ስትሪቱን
Enron Scandal ውድቀት ወዘተ ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ እና መንግስት ገና በዳዴ ነው ያሉት። እነ ዐጼ በጉልበቱ የህዝብ አገልጋይ ነን ያላሉ እንጅ የህዝብ ተገልጋይ ናቸው። አንድ የሚያስቅ ምሳሌ ልንገርህ ኢትዮጵያ ባለሁ ጊዜ አንድ የሜድካል ዶክተር እና አንድ የንግድ ስራ ኮሌጅ በዲፕሎማ ብቻ ፐርቸዚንግ የተመረቁ ሁለቱም ደመወዝ ሊቀበሉ ወረፋ ተሰልፈዋል። ዶ/ሩ እኔ ይገርመኛል እኔ ቤተሰቤን በዚህ ደመወዝ ማስተዳደር አልቻልኩም ተመልከት ይህን የዕቃ ግዥ ሰራተኛ የሚለብሰውን እና የሚያጌጠውን አለኝ። ሚስጥሩ ግልጽ ነበር የውሸት ጫረታ፥የውሸት ፕሮፎርማ እየለቃቀመ የድርጅቱን ገንዘብ ግሽልጥ አድርጎ እየሰረቀ ነበር።መጀመሪያ የፓለቲካ ጥራት ያስፈልጋታል አገሪቱ።


Horus wrote:
19 Aug 2022, 13:53
አበረ፣
እኔ የተለየ ምልከታ አለኝ። እርግጥ ነው ያቢይ መንግስት የራሱ ፋንሲ ማንሲ ዱባይ አይነት ፕሮጀክቶች ለመስራት ብዙ ቢሊዮኖች ዶላር ስለሚፈልግ ካፒታል (ፈንድ) ለማግኘት እነዚህን በመንግሥት የተያዙ ኢንዱስትሪዎች መሸጥ አለበት ። ያ የነአቢይ ነጂ ፍላጎት ቢሆንም በሌላ በኩል ግን መንግስትን ከንግድ ማስወጣት አንድ ትልቅ የእድገት እርምጃ ነው ።

የመንግስት ሚና ሱካር ማምረትና ሱካር መሸጥ አይደለ። ይህ ነው የቢሮናየመንግስታዊ መሰኛ ኮራፕት ከበርቴ መደብ መፈልፈያ ረግረግ! አው ዛሬ አቢይ ለምን 8 ሱካር ፋብሪካዎችን መቸብቸብ ፈለገ የሚለው ጥያቄ መልሱ አቢይ የጦር መሳሪያ መግዣና ፓርክና ሙዚየሞች መገንቢያ ዶልላር ስለሚፈልግ ነው ። ግን እነዚህ በውያኔ የተጋጡ ኢናኤፊሸንት ሚዲኢቫል ፋፍሪካዎች ለግል ነጋዴ መሸጣቸው ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ።

በአንድ ቃል ፋብሪካዎቹ ትርፋማ ሆነው ለመንግስት ያሰበውን ያክል ዶልላር ማመጨት ስላልቻሉ (ማለትም መንግስት ቢዝነስ ማኔጅመት ስለማይችል) ነው የሚሸጡት እንጂ ጥሩ ማኔጅመንት ይዘው ትርፍ ቢያመጡ በምንም አይነት አቢይ አይሸጣቸውም ነበር ።

ብቻ መንግስት ከነጋዴት በራቀ ቁጥር የፖለቲካ ኮራብሽን ይቀንሳል፣ ይህ ሳይንስ ነው ።

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by Ethoash » 19 Aug 2022, 16:03

አቡዋራውና ሆረር ለመጀመሪያ ግዜ ከናንተ ጋራ ሰስማማ

ለምን ዶክተር አብይ የሱካር ፋብሪካውን ለመሽጥ ፈለገ፣ መልሱ ቀላል ይሆናል።

አንደኛ የውጭ ብድር አበዳሪዎች እንደ አለም ባንክ ገንዘብ ስለተበደረ የመንግስት ድርጅቶች ሽጥ ብለውት ይሆናል\ከኢህ ምንም ማምለጫ የለም
እንግዲህ የአለም ባንክም ይሆን የውጭ መንግስታት የሱካር ድርጅቱ መሽጡ ጠቃሚ እንዳልሆነ ያወቁታል ብዙ አገሮች ላይ የቧንቧ ወሃ ሳይቀር በግል አዛወረው ታላቅ የሀብት ብዝበዛ ተካሂዶ ድሃው ለሚጠጣ ውሃ መክፈል አቅቶት ነበር። ይህንን ለማየት ደቡብ አፍሪካ ተመልከቱ ወንዙን ሁሉ ሳይቀር ይሽጥ ነበር ግን ድሃው የሚጠጣ ውሃ እስከሚያጣ ድረስ ። ስለዚህ ዝም ብሎ መሽጥም አይጠቅምም፣ ደግሞ አልሽጥም ብትል እጅህን ይጠመዝዙህል

ታድያ ምንድነው ዘዴው መልሱ በሆረርና በአቡዋራው መሃል ነው። ሁለታቹሁም ልክ ናቹሁ ሆረር ይሽጥ አቡዋራው አይሽጥ፣ በተሀምርም አለመሽጥ አይቻልም እዳ በእዳ ነን ደላር አብይ ይፈልጋል ስለዚህ መልሱ ከተቻለ መሃል መንገድ መላ መፈለግ ነው። አርባ ዘጠኝ በመቶ ሽጦ ፣ አምሳ አንድ በመቶውን በመንግስት እጅ መያዝ ጥሩ ነው።

ሁለተኛው ዘዴ ደግሞ ለአበሾች መሽጥ ነው። ይህም አይቻልም ግልፀ ጨረታ አወጣ ይባላል። መንግስት ዜዴ ፈልጎ ለአገር ወስጥ ኢንቨስተር መሽጥ በጣም ጠቃሚ ነው። አንድ ግዜ አንዱን የሱካር ድርጅት ለመሽጥ ፈልገው የአገር ስዎች ገንዘብ ያጠራቅሙ ነበር

ይህ ምሳሌ ነው አንድ ቢሊዬን ብር መንግስት ይጠይቃል እንበል ለሱካር ድርጅቱ ፣ አበሾቹ ግን አራት መቶ ሚሊዬን ብር ብቻ ስላገኙ መግዛት አልቻሉም የዛን ግዜ መንግስት አንሽጥም ብሎ ሲያቅማማ የአበሻ ኢንቨስተሮች ኢንቨስትመት ይቀዘቅዝና ገንዘቡን ማግኘት አልቻሉም ሳይገዙ ቀሩ ፣ እንግዲህ መንግስት ስልሳ በመቶውን መንግስት ይዞ አርባ በመቶውን ለአበሾቹ ስጥቶ ቢገላገል ጥሩ ነበር ግን ብዙ ጉቦ የሚበሉበት ስለሆን እንቢዬው ብለው ነገሩን አከሽፉ

ሌላው ማየት ያለብን ነገር ለውጭ ድርጅቶች ሱካር ድርጅታችንን ማጣታችን ነው። ለምሳሌ መንግስት አንዱን ሱካር ድርጅት አንድ ቢሊዬን ብር ግምት ቢያወጣም የአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች እንዳልኩት አራት መቶ ሚሊዬን ብር ብቻ ቢያጠራቅሙ ፣ የወጪ በቀላሉ አንድ ቢሊዬን ብር ኢንቨስት አርጎ ሊጠቀልለው ይችላል ። ይህ ሆኖ ቢያቆም ጥሩ ነበር ግን የውጩ ድርጅት አንዳንዴ ድርጅቱን አትራፊ ማረግ አይደለም አላማው ድርጅቱን ማክስር ነው። የሱካር ድርጅታችንን በደንብ ካከስረው በኋላ ተነስቶ ይወጣል ኢትዬዽያ ዚሮ የሱካር ድርጅት ካላት ማለት ከወጭ ሱካር ማስገባት አለብን የዛን ግዜ በደንብ ያገኙናል ማለት ነው። ሱካር ድርጅታችንን አጥተን እንቀራለን ይህ ደባ ነው ብዙ አገር ላይ እንዲህ ተጫወተዋል

የኤርሚያስ አመልጋ ይንገራቹሁ፣ የዘይት ድርጅት ነበረው ደህና ይሄድ ነበር ግን የአሜሪካ ድርጅት በጎ አድራጎት ብሎ ነፃ ዘይት ከተማውን አጥለቀለቀው ። ለአንድ አመት ሳይሆን ለሁለት ለሶስት አመት አጥለቀለቁት በሙሉ የዘይት ድርጅቶች ከስረው ተዘጉ መነሳት አቃተን ይህ አይ በአጋጣሚ የተደረገ ይመስላቹዋል ግን አይደለም ኤርሚያስ ያልደረስበት የመንግስት ድርጅት አነበረም የሚስማው ጠፋ ፣ አሜሪካኖች እራሳቸው በነፃ ስንዴ አምጥተህ አሜሪካ ማስገባት ይከለክሉሀል በቀጥታ ሳይሆን ይህ ከእኛ ደረጃ አይመጥንም ይሉሀል በተሀምርም የራሳቸውን ኢንዱስትሪ ለምሳሌ የወተት ሀብትን የሚጎዳ ምርቶችን አያስገቡም።

አሜርካኖች ይህንን ጫዋታ ደጋግመው ተጫወተዋል። ለምሳሌ ጃማይካ ሄደው ፣ ጃማይካዎች ብዙ የወተት ምርት ነበራቸው ለአገሪቱ በቂ ግን አሜሪካኖቹ ያንን ንግድ ለማወደም አወቀው የዱቀት ወተት በነፃ ገበያ ውስጥ አፈስ ሱት ። በሙሉ ወተት የሚገዛ ጠፍቶ የጃማይካ ገበሬዎች ወተታቸውን ይዛው ፓርላማቸው ላይ ወጠቱን ደፉት ፣ ላይ ወትቱ ተሽጠ አልተሽጠ መታለብ አለባት ይህ ማለት ተደራራቢ ውጪ ምንም ጥቅም ላይኖራቸው። ብቻ ብዙ አገር ላይ ሄደው ይህንን ዘዴ ተጫወተውታል ስለዚህ አወቀው ነው ይህንን ነገር አርግ የሚሉት ለአብይ ካላደረገ ደግሞ አብዬት ያስነሱበታል ማለት ነው።

አማራጪ ያለው እንዳልኩት ግዜ ካለው ለአበሾች አስር በመቶውንም ቢሽጥ ይሻላል የወጭ አገሮችንም በደባል ማስገባት ጡሩ ነው ። ሼራቸው ካልበዛ ጉዳታቸው ተመጣጣኝ ይሆናል ማለት ነው ፣ እንጂ የወጭ አገሮቹ ጥሩ ስለከፈሉ ብቻ ለነሱ መስጠት ትልቅ አደጋ አለው ። ይህንን መቶ በመቶ ማለት አንችልም ለምሳሌ የቢራ ፋብሪካ ተሽጦ ትልቅ ማሻሻያ ነው የተደረገው። ግን ምን ይስርልናል ቢራ ቢሻሻል ባይሻል ። በዚህ ላይ ብቅሉ ከወጭ የሚመጣ ከሆነ ትርፉ ተመልሶ ይወጣል ማለት ነው።

እንደውም የረሳሁት አብይ ስምንት ሱካር ፋብሪካ እያንዳንዳቸውን አንድ ቢሊዬን ደላር ቢሽጥ ስምንት ቢሊዬን አገኘ ማለት ነው ። ስምንቱን ቢሊዬን ኪሱ ከመክተቱ በፊት የአለም ባንክ እዳህን ክፈል ብሎ ጠቅላላ ገንዘቡን ይወስድበታል ስለዚህ መሽጡ እኔ አይታየኝም ።

፣መሆን ያለብት ለምሳሌ አንድ የሱካር ፋብሪካ ስንት ትርፍ ያመጣል በአመት እንበል አንድ ቢሊዬን ደላር ቢሆን
አስር ሺህ ዶላር እንቨስተር መቶ ሺህ ትወልደ ኢትዬዽያኖች ሊገዙ ይችላሉ ማለት ነው ። እያንዳንዳቸው አስር ሺህ ደላር በማዋጣት ።
እንግዲህ ይህ በደላር ነው በብር ቢሆን ደግሞ አስር የሱካር ድርጅቶችን መግዛት ቻሉ ማለት ነው። ያም ባይሆን መንግስት አርባ ዘጠኝ በመቶ ይዞ ሁሉንም ለተወልደ ኢትዬዽያኖች መሽጥ ይችላል ማለት ነው።

ብዙ ብዙ ነገር ተብሎዋል ግን ለአገር ወዳድ በአንድ ብር ቢሽጥ ይሻላል። ለምን ቢባል ጉቦን ለማስቀረት፣ እስከዛሬ ሱካር ከወጭ የሚመጣ የሱካሩን ድርጅቶች መጨረስ ባለመፈለግ ነው። ለምሳሌ ከሕንድ ሱካሩን የምናስገባ ከሆነ ፣ ከሱካር ላኪው ጋራ ተነጋግረን ሚሊዬን ደላር በባካችን ያስቀምጥልናል ስለዚህ የመንግስት ስራተኞች ላይ ያሉት የሱካሩን ድርጅት መጨረስ አይፈልጉም ለምን ሱካር ከውጭ ካልገባ ማን ጉቦ ይስጣቸዋል።

የጤና ሚኒስተር በአቅሚቲ የመቶ ሚሊዬንን ሕዝብ መድሀኒት ከሕንድ ያስገባል ስለዚህ የህንድ company give him bribe so why the health minister give permit for those who wish to produce the medical pill in Ethiopia he will be road block because they r interfering with his business do u get it .. they are their to opp. progress their business is to take kick back so they don't care if they foreigner bought the sugar factory as long as he give them kick back

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by sarcasm » 19 Aug 2022, 19:16

It is very expensive to fund wars - UAE is not going to help now. Wars are funded by selling state assets.


quindibu
Member
Posts: 3279
Joined: 31 Dec 2010, 13:17

Re: Abiy Ahmed's regime is selling 8 Weyane built sugar industries with their plantations to fund another round of war

Post by quindibu » 19 Aug 2022, 19:51

sarcasm wrote:
19 Aug 2022, 19:16
It is very expensive to fund wars - UAE is not going to help now. Wars are funded by selling state assets.

Hallelujah for your blessed land, for shale oil that has made war possible with the 'genociders'. :P


Ethiopia has 3.89 billion tonnes of oil shale located in Tigray State, which borders Eritrea

3.89 tones of oil shale will produce roughly about one trillions barrels of oil. That is huge amount oil if it is extracted successfully not it only it will be satisfy the local market but, it will have some left for export earning much needed hard currency..

https://www.tigraionline.com/articles/a ... 30126.html

Post Reply