Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጉራጌ በትንሹ 23% የኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ሕዝብ ነው፤ ሌሎች 30% ነው ይላሉ!

Post by Horus » 19 Aug 2022, 02:19

በአገር ቤት ከአበሽጌ እስከ አማውቴ፣ ካማውቴ እስከ ኢንሴኖ ያለው የጉራጌ ባላገር እንዳለ ሆኖ፣ በአዲስ አበባ ብቻ 2 ሚሊዮን ተኩል ጉራጌ አለ። በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉት ግዙፍ ከተሞች እስከ ታናንሽ ከተሞች ጉራጌ የሌለበት የኢትዮጵያ ከተማ የለም ። እንደ ሚታወቀው ይህ ሁሉ ጉራጌ በባህሉ የማይለምን ታታሪ ነጋዴ ፣ አስተማሪ፣ የመንግስት ሰራተኛና ባለ ኢንዱስትሪ ባለሃብት ነው ።

ማንኛውም ከአድልዎ ነጻ የሆነ የስታጽቲክስ ሊቅ የጉራጌ ዲያስፖራ ከቅርብ ምስራቅ፣ አሜሪካና አውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ የሚልኩት በቢሊዮ ዶላር የሚቆጠር ሃብት እንዳለ ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ጉራጌ የሚያስገባው ግብር እጅግ እጅግ በትንሹ 23% ይሆናል፣ 30% የሚያደርሱት ከውነት ብዙ የራቁ አይሆኑም።

የኢትዮጵያን ሲስተም ከሚያነቃንቁትትህ ግዙፍ የፊናንስ፣ ኢኮኖሚ፣ ትምህርት፣ ሳይንስ፣ ሜዲሲን፣ ቴክኖሎጂ፣ የእርሻ ሳይንስ፣ የኢንዱስትሪ፣ ንግድ አርት፣ ሙዚቃ፣ እና ስነጽሁፍ ሊቅ ባሊቅ ጉራጌዎች ብዙ ብዙ ብዙ ናቸው!

አቢይ አህመድና የሆኑ ጉራጌ ጠል የብልጽኛ የቢሮ ከበርቴ ኪራይ ሰብሳቢዎች በጉራጌ ላይ ወታደራዊ አገዛዝ መጫንና ከጉራጌ ጋር ጠብ ያለሽ በዳቦ ያሰኛቸው ሞቲቬሽን ምን ሊሆን ይችላል? በጉራጌ ኢትዮጵያዊነት ተበሳጭተው ከሆነ (እንደ ሟቹ መለስ) አንድ ነገር ማወቅ አለባቸው! ነብር ጠቃጠቆዋን እንደ ማትሸልት ሁሉ ጉራጌ ኢትዮጵያዊነቱን አይሸልትም!

ከንቱ ልፋት ነው!

አቢይ ከጉራጌ ጋር አላስፈላጊ ጠላትነት መጀመሩ የሞኝ ምክር ነው እነለዋለን! ጉራጌ ለዘመናት ያፈራው ሃብት ደርግ ወርሶት፣ የተረፈውን የትግሬ ወያኔ ወስዶት አሁንም ያለ ወደፊት የትም የማይጠፋ ሕዝብ ነው። ጉራጌን ማምከን ከንቱ መባከን ነው!

የጉራጌ ድምጽ የሚሰማበት ታሪክ ላይ እንደርሳለን! ያኔ እንተዛዘባለን!!!

የመስቃኗ እንቁ እንዳለችው ፣ የወረስነው ባንዲራ ነው፣ የወረስነው ኢትዮጵያዊነት ነው፣ የወረስነው ጀግንነት ነው! ጉራጌ ፈረስክን ጫን!!!




Post Reply