Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12530
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ዮሐንስ ቧያለው : "አሁን ላይ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ የሚኖረው ከሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከሶሪያና ከየመን ስደተኞች በታች ነው"

Post by Thomas H » 16 Aug 2022, 10:35

በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመው ግፍ፣ አማራ ፈፅሞት ቢሆን ምን ይፈጠራል? ኦሮሚያ ውስጥ የታረዱትን ያህል፣ አማራ ውስጥ ሌላ ብሄር ታርዶ ቢሆን ምን ሊፈጠር ይችላል? ብላችሁ አስቡት። በበቀል አፀፋ ኢትዮጵያ የደም ጎርፍ ትሆን ነበር። ሀገር ሙሉ በሙሉ ይፈርስ ነበር። ስንት አኖሌ ሀውልት ይሰራ ነበር።
በኢትዮጵያ 3 አይነት ዜጋ አለ። አማራ በአሁኑ ሰዓት 3ኛ ደረጃ ዜጋ ነው። በወያኔ ጊዜ 2ኛ ደረጃ ዜጋ ነበር። አንደኛ ደረጃ ዜጋው ጊዜው የእኛ ነው የሚለው አካል ነው። ሁለተኛ ደረጃ ዜጋው ደግሞ ሌላው ብሄር ነው። በሶስተኛ ደረጃ የአማራ ህዝብ ነው። አሁን ላይ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ የሚኖረው ከሱዳን ስደተኞች፣ ከኤርትራ ስደተኞች፣ ከሶሪያና ከየመን ስደተኞች በታች ነው።
በጦርነት ጊዜ ያልተባለ፣ ከጦርነቱ በሗላም ያልተነሳ ... ድንገት ሰሞኑን ፋኖ ከመከላከያ ላይ ጥቁር ክላሽ ቀማ የሚለው እንዴት መጣ? አትሞኙ፣ ይሄ አዲስ የአማራ ጥላቻ ትርክት እየተፈጠረልን ነው። ነባሩ ትርክት አልበቃቸው ስላለ ነው። የጥቁር ክላሽ ትርክት የመጣው፣ የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሮችን ጥቁር ታሪክ ለመሸፋፈን ነው። በእነዚህ አመራሮች መሪነት አማራ ታርዷል። የ15 ቀን ህፃን ከእነ እናቷ ተገድላለች። ታዳጊ ህፃን ሁለተኛ አማራ አልሆንም ብላለች። ጥቁር ታሪካቸው ተዘርዝሮ አያልቅም።
( ዮሐንስ ቧያለው - ፋኖነት በሚለው የመፅሐፍ ምርቃት ላይ የተናገረው)