Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

እኔ ይህ ግድብ አስግቶኛል

Post by Ethoash » 13 Aug 2022, 13:44

እስቲ ይህንን የጎርፍ ግዜ ውሃ መልቀቅያ ተመልከቱት ፣ ውሃውን በሽርተቴ እንደርድሮ ወደላይ ይለቀዋል ። ይህ ሲሆን ውሃው ወደ ውሃ አዘል ነጠብጣብ ይሆንና ወደመሬት ሲወድቅ አቅም ስለማይኖረው መሬቱን አይሽረሽረውም ይህ ማለት ግድቡን የመስርቱን ደንጋይ አያናጋም ማለት ነው። ይህ ምንም ላይመስል ይቻላል ግን ውሃ ብረት የሚቆርጥ አይል አለው በፍጥነት የሚመጣ ከሆነ ፣ በአንድ ላይ ውሃው እንደጎርፍ የሚጎርፍ ከሆነ የግድቡን መስረት ሊያናጋው ይችላል። ግን ውሃውን አንደርድሮ ወድ ላይ እንደገና ሲበትነው ልክ እንደዝናብ ውሃው ይበታተናል ። ይህም እያንዳንድ ጥብታ ሲወርድ ሃይል አይኖረውም ፣። እናንተ ሞክሩት ቤታቹ ውስጥ ድቀት በሳህን አለቀምጡና በማንቆርቆርያ ውሃውን ልቀቁበት ውሃው አይለኛ ስለሆነ ድቄቱን ለመቆርቆር ይችላል። አሁን ደግሞ ከጀበና የሚወጣውን ውሃ በእጃቹሁ በማገድ አርክፍክፉበት ውሃው ጥብታ ሆኖ ምንም ድቄቱን ስርስሮ አይገባም። ስለዚህ እኔ ትንሽ ቅር ያለኝ ትንሽ ነው ውሃ ማስተንፈሻ ያለው ወይም አሁን ውሃ ሞልቶ የሚፈስበትን ድረጃ ወድ ፣ ውሃ ሙሌት ማስተንፈሻ በሮች የሚቀየሩ ከሆኑ መልካም አለበዚያ ዋ ብለናል ... watch this video and u will understand what i am talking about