Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30898
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የቅቤ ዕቁብ!

Post by Horus » 13 Aug 2022, 01:35

እንደ ዛሬ ነሃሴ 6 ቀን ለቅቤ ዕቁብ ዘግይቷል! ያ የሆነው በሃምሌ ነው ። የጉራጌ መስቀል ዝግጅት በሃምሌ መጠናቀቅ አለበት ። በነሃሴ 15 ቡሄ ለት ደመራ መትከያ ቀን ነው ። የዚያን ቀን ለደመራ የሚፈለግ ቀጥ ያለ ረጅም አጠና ዛፍ ያለው ሰው እንዳይቆረጥበት ሊከለክል አይችልም ። ነውር ነው ። ልክ በገና ጨዋታ አይቆጡ ጌታ እንደሚባለው ነው ። በነሃሴ 15 የተተከለው ደመራ እንጨት እንዲደርቅ ተልጦ ነው የሚመጀረው! ምጅር ማለት ደመራ ማለት ነው።

እስከ እንቁጣጣሽ በቅጠልና በጭራሮ በገድራ ይሰባና ከአክራሚ እንቁጣጣሽ ማግስት ጀምሮ ልጃገረዶች ማታ ማታ ደመራው ጋ ሄደው እስከ መስቀል ይዘፍናሉ ። ስለዚህ የጉራጌ መስቀል የሚጀምረው የቡሄ ለት ነው።