Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኮማንድ ፖስት የጉራጌ ሽማግሎችን ያንገላታበት አሳፋሪ የመንግስት ታሪክ!

Post by Horus » 12 Aug 2022, 14:05

ገዥዎች እዚም እዛም ያሻቸውን ግዜ በሰጣቸው ሃይል እያረጉ የነገን መዘዝ ሳያይ የዛሬ ጉልበታቸውን ሊሳዩን ይጥራሉ ። ሕዝብ ግን አይረሳል። የተፈጸመበትን ግፍ አይረሳም። ታሪክ አይረሳም ። ነገርን ነገር ይወልደዋል! ከህዝብ በሰበሰቡት ቀረጥ መሳሪያ ታጥቀው እኛኑ መልሰው ለማዋረድ የሚተጉ የዘመኑ አላዋቂ ተረኞች ከታሪክ ቢማሩ ይሻላል። ታሪክ የሚሰሩ ሕዝቦችና ሕዝቦች ብቻ ናቸው! የገዥዎች ሃይልና ጉልበት እስከ ሚወድቁ ድረስ ነው! ሕዝቡን የማያከብር ገዢ ለውድቀቱ የሚተጋ ባተሌ ነው! ሁልግዜ አሸናፊ ሕዝብ ነው ።

የሕዝብ ድምጽ ምን ማለት እንደ ሆነ፣ የዚያም ሕዝብ መሪና ወኪል መሆን ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ትላንት በጉራጌ አሳይተናል ። ባንዳነትና ከሃዲነት በጉራጌ ከሰውነት በታች የሚያደርግ ጸያፍ ነው ። አባቶቹን የማይሰም ትውልድ ደሞ ባለጌ ፋንዲያ መቆሚያ መሰረት የሌለው ሙጃ ነው። የጉራጌ ወጣት አባቱን አክባሪ ትውልድ ነው። ነገም የሚሆነ ያ ነው ። በጉራጌ የማይፈታ ምንም አይነት ችግር የለም ። ያም የሚሆነው በአባቶቹ ብልሃትና ትልቅ ዊዝደም ነው! ኬር ለኢትዮጵያ! ሰብኛ ማለቅ ዪሁን !