Page 1 of 1

1,283 Eritrean Refugee Elementary School students in Tigray are starting school in September - UNHCR

Posted: 12 Aug 2022, 09:20
by sarcasm
ከሚያዚያ ወር ጀምሮ 4 ሺህ 765 የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ መኪኖች ትግራይ ክልል ደርሰዋል

ነሐሴ 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) ካለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በአጠቃላይ 4 ሺህ 765 የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ መኪኖች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ትናንት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ መንግስትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በትግራይ ክልል እርዳታው እንዲደርስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

በኮሚሽኑ የተሰማሩ 60 መኪኖች መኖራቸውን ኮሚሽኑ አመልክቷል።
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በሚገኙ ማይ አይኒ እና አዲ ሀሩሽ በተሰኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የመማር ማስተማሩ ሂደት መቀጠል መቻሉን ኮሚሽኑ ገልጿል።

አዲ ሃሩሽ መጠለያ ጣቢያ 826 ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ሲሆን በማይ አይኒ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ደግሞ 457 ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

በተጨማሪም ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በሁለቱም መጠለያ ጣቢያዎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አመልክቷል።
በጣቢያዎቹ ውስጥ የሚገኙ አምቡላንሶች ህመምተኞችን ወደ ሸሬ እና ሌሎች ሪፈራል ሆስፒታሎች ማድረስ እንደጀመሩ ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን በክልሉ የሚገኙትን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን ለማገዝ እንደሚሰራ አስታውቋል።
በትግራይ ክልል በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ቁጥራቸው የበዛ የኤርትራ ተወላጆች እንደሚገኙም የኮሚሽኑ መግለጫ ማስነበቡን የፒፕልስ ዴይሊ ኦንላይን ዘገባ ጠቁሟል።
Please wait, video is loading...

Re: 1,283 Eritrean Refugee Elementary School students in Tigray are starting school in September - UNHCR

Posted: 12 Aug 2022, 09:32
by Weyane.is.dead
Terrorist mafia tplf using Eritrean children for begging. You're not educating anyone. Leba weyane

Re: 1,283 Eritrean Refugee Elementary School students in Tigray are starting school in September - UNHCR

Posted: 12 Aug 2022, 10:02
by Meleket
:mrgreen: viewtopic.php?f=2&t=301357 :mrgreen:
sarcasm wrote:
12 Aug 2022, 09:20
ከሚያዚያ ወር ጀምሮ 4 ሺህ 765 የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ መኪኖች ትግራይ ክልል ደርሰዋል . . .