Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30667
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በነገው ቀን የጉራጌ ምክር ቤት ክልልነት ላይወስን ይችላል! ጉራጌ ለምን ተከፋፈለ?

Post by Horus » 10 Aug 2022, 18:14

በእኔ እይታ የጉራጌን አንድነት ፈተና ላይ የጣሉት (1) ቋንቋ (2) እድገት (3) መልካም አስተዳደር እና (4) የዋና ከተማ ጥያቄዎች ናቸው ።

በብዙ ዘዬዎች የሚከፋፈሉት የጉራጌ ቋንቋዎች ላይ ያለው ችግር አልተፈታም ። እያንዳንዱ ቤተ ጉራጌ የራሱን ዲያሌክት ለማሳደግ እንጂ ያሉትን ጨፍልቆ አንድ ጉራጌኛ የጋራ ቋንቋ መፍጠር አልተቻለም፣ ወይም ስምምነት ላይ አልተደረሰም ። ለምሳሌ ክስታኔና ቋንቋ እየሞተ ሰልሆነ እንዲያገግም እየተሰራ ነው እንጂ እንዲሞት ሰው አይፈልግም። ስለዚህ አንድ ጉራጌኛ የክልል ቋንቋ ጉራጌ የለውም ። ይህ ችግር ቁ 1 ነው

አሁን ክለስተር ይደግፋሉ የሚባሉት ወረዳዎች፣ አውራጃዎች ወይም ቤተ ጉራጌዎች ባለፈው 27 አመት ፈጽሞ የተረሱና የዛሬ 30 አመት በነበሩበት ያሉ ስለሆነ ነው ። ለምሳሌ ይብዛም ይነስ የጉራጌ አስተዳደር ቁጥር አንድ ታሪካዊ ቦታ በሆነው የጢያ ተክል ድንጋይ ታሪካዊ ቦታ አይደለም ማረፊያ ሆቴልና ሽንት ቤት ጥርጊያ መንገድ እንኳን አላሰራም ። በመላ ጉራጌ የአለም ቱሪስት የሚያየ ባለም ቅርጽነት የተመዘገበ ጢያ ሽንት ቤት የለውም ።

በዚህ አቢያ ሶዶዎች ክልል ባይፈልጉ አልገረምም። የጉርጌ አስተዳዳአሪዎች ባብዛኛው ሰባት ቤት ስለነበሩ ማለት ነው።

ስለዚህ የልማት አለመኖር ብቻ ሳይሆን የመልካም አስተዳደር መጥፋት ሌላው የክፍፍል መሰረት ይመስላል።

አራተኛውና አሁን ትልቁ የክፍፍል መሰረት የጉራጌ ክልል ዋና ከተማ ማን ይሁን የሚለው ነው ። በእኔ እይታ በውበትም፣ ባቀማመጥም፣ በእድገትም ቡታጀራን የሚያክል የጉራጌ ከተማ የለም ። ቡታጀራ ሌላ አዋሳ ሊሆን የሚችል ከተማ ነው ።

ስለሆነም ምዕራብ ጉራጌዎች ከምስራቅ ጋር ተቀምጠው ይህን የዋና ከተማ ጉዳይ መፍታት ነበረባቸው ። እኔ ሌላ ቦታ እንዳልኩት ይህን ችግር ስላልፈቱ ነው ለምሳሌ መስቃኖች ቡታጀራን የምስራቅ ጉራጌ ካፒታል የሚሏት ። በዚህ የወልቂጤ እና ቡታጀራ ፉክክር በመሃል የተረሱት ሌሎች ከተሞች ብዙ ናቸው ።

ጉራጌ ለእድገት በጣም ቀናኢ ሕዝብና ተፎካካሪ ስለሆነ ሁሉም የራሱን ከተማና ቋንቋ ማሳደግ ይፈልጋል።

በነገው የጉራጌ ምክር ቤት ስብሰባ ክልልነት ካለፈ አስገራሚ ይሆናል! እጅግ ትልቅ የጉራጌዎች አንድ መሆን የሚያመልክት ክስተት ይሆናል ። ክልልም ክለስተርም ሳያሸንፉ ስብሰባው ሊበተን ይችላል ። ለእኔ ያ በጣም ጥሩ ውጤት ነው ። ጉራጌ ግዜውን ወስዶ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች መፍቻ ግዜ ያገኛል ። በአሁን ሰዓት ክስታኔ መስቃንና ወለኔ ብዙ ሲካፈሉ ወይም ለክልል ሲታገሉ አይታይም ።

በተቃራኒው ምክር ቤቱ ክለስተር እንዲደግፍ ተደርጎ ከተለያየ ጥቅላላ አካባቢው የሽኩቻና መቃቃር፣ የክፍፍልና ከፍተኛ ፉክክር ቀጠና ይሆናል ። ስለሆነም ጉራጌ እንደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ይበልጥ ይዳከማል።

ነገ ከነዚህ 3 ውጤቶች አንዱን እናያለን! ሰላም እንደር!

eden
Member+
Posts: 9193
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: በነገው ቀን የጉራጌ ምክር ቤት ክልልነት ላይወስን ይችላል! ጉራጌ ለምን ተከፋፈለ?

Post by eden » 10 Aug 2022, 18:31

(1) ቋንቋ Use Amharic language, like Sidama (?)
(2) እድገት Make differences inpoverty levels a factor in resource/ budget allocation
(3) መልካም አስተዳደር Implement complaint management systems
(4) የዋና ከተማ ጥያቄዎች Make one commercial capital and the other political capital/ Seat of government

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: በነገው ቀን የጉራጌ ምክር ቤት ክልልነት ላይወስን ይችላል! ጉራጌ ለምን ተከፋፈለ?

Post by simbe11 » 10 Aug 2022, 20:25

"በዚህ አቢያ ሶዶዎች ክልል ባይፈልጉ አልገረምም። የጉርጌ አስተዳዳአሪዎች ባብዛኛው ሰባት ቤት ስለነበሩ ማለት ነው።"
The blame game already started before even you get you region, pathetic.

"ጉራጌ ለእድገት በጣም ቀናኢ ሕዝብና ተፎካካሪ ስለሆነ ሁሉም የራሱን ከተማና ቋንቋ ማሳደግ ይፈልጋል።"
This is the basics of tribal thinking. Nobody hates to see his/her place to thrive. But when we think collectively, we think about the good of the general public. Instead of crying about Butajira vs Wolkite, you will start thinking which city is for administration and its historical values.
I like both cities but prefer Butajira over Wolkite. Because Butajira is more diverse than Wolkite is.

Horus
Senior Member+
Posts: 30667
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በነገው ቀን የጉራጌ ምክር ቤት ክልልነት ላይወስን ይችላል! ጉራጌ ለምን ተከፋፈለ?

Post by Horus » 10 Aug 2022, 22:24

eden wrote:
10 Aug 2022, 18:31
(1) ቋንቋ Use Amharic language, like Sidama (?)
(2) እድገት Make differences inpoverty levels a factor in resource/ budget allocation
(3) መልካም አስተዳደር Implement complaint management systems
(4) የዋና ከተማ ጥያቄዎች Make one commercial capital and the other political capital/ Seat of government
Eden

በቁ 2፣ 3 ፣ 4 በመሰረቱ እንዳንተ ነው የኔም ሃሳብ ብዙ ቦታ ጽፌበታለሁ ። የእድገት ጥያቄ ትንሽ ውስብስብ ነው ። ከ12 እስከ 16 የሚደርሱት ፖቴንሻል የጉራጌ ክልል ዞኖች ሁሉም የራሳቸው ዋና ከተማ አላቸው። ለምሳሌ የመስቃን ዋና ከተማ ቡታጀራ ነው ። የሶዶ ዋና ከተማ ቡኢ ነው፣ እምድብር፣ ጉብሬ እያለ 12 እስከ 16 ይደርሳል። ብዙዎቹ እነዚህ ራስ ገዝ ዞኖች ነው የሚሆኑት ። እና የቱ ከተማ ፈንድ ይውሰድ የቱ ይቆይ የሚለው ቀላል ውሳኔ አይደለም።

ከላይ ያነሳሁት የጢያ ታሪካዊ የቱሪስት ቦታ የተለየ ስለሆነ ነው ። በጉራጌ ያንን የሚያክል ታሪካዊ ነገር የለም ። ተመድ ያለም ቅርስ ያደረገው ድሮ በደርግ ዘመን ነው ። ገና አዲስ የአርኪዮሎጂ ቁፋሮ ሊድረግበት ነው ። ግን ማንኛውም የጉራጌ አስተዳደር እንደ ራሱ ቅርስ አይቶ ቢያንስ መንገድ፣ ማሪፊያ ቤትና ሽንት ቤት እንዴት ለ30 አመት ሳይኖረ ይረሳል?

ለዚህ የምስለኛል የዛሬ 3 ቀን የቱሪስት ኢኒስቴር ዛፍ ሊተክል እዚያ የሄደው ። ሌላው እስከ 1 ሚሊዮን ሰው የሚሳለመው የምድረ ከብድ አቦ እስከ ዛሬ መንገድ እንኳን የለውም ። እኔ በበኩሌ ሶዶ ጉራጌና ሃዲያ ምንም እንደ ማያገናኛቸው አውቃለሁ። ደሞም የጉራጌ ክልልነት አቀንቃኝ ነኝ ። እኔ ሶዶ ነኝ፣ ከላይ የጻፍኩት ያለው ሃቅ ነው።

በቁንቋ ላይ የጉራጌ የጋራ የመግባቢያ ቋንቋ እጦት አይደለም። ጉራጌ ሁሉ 100% ያማራኛ ባይሊንጓል ነው ። አዲስ ያለው ሃሳብ ወደ 10 የሚጠጉት የጉራጌ ዲያሌክቶች ወደ አንድ ትልቅ የጉራጌኛ ይቀመሩ የሚል ሃሳብ አለ ባንድ በኩል ። በሌላ በኩል እያንዳንዱ ማህበረሰብ ለምሳሌ መስቃን መስቃንኛን፣ ሶዶ ኪስታኔኛ፣ ወዘተ ማበልጸግ አለብን ስለሚሉ አንድ የጉራጌ ብሄራዊ ቋንቋ ላይ ግዙፍ ችግር አለ፣ ያ ነው እንጂ ችግሩ ስለስራ ቋንቋ አይደለም ።

ከዚያ በተረፈ እስማማለሁ ። በህዝብ ሬፈረንደም አንድ ዋና ከተማ መወሰን፤ ሌሎች እንደ እድገታቸው የንድኛ ኢንዱስትሪ ከተማ ብሎ መመደብ ነው። ይህ ሁሉ የክልልነት ውስጥ እንዲካተቱ ማድረግ ሲቻል መንግስት በዚህ ክፍተት ገብቶ የፈለገውን በላያችን ላይ ለመጫን እየተጣደፈ ነው ።

ሁሉንም ነገር እናየዋለን።



Misraq
Senior Member
Posts: 12279
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: በነገው ቀን የጉራጌ ምክር ቤት ክልልነት ላይወስን ይችላል! ጉራጌ ለምን ተከፋፈለ?

Post by Misraq » 10 Aug 2022, 23:58

ሆሩስ

በጉራጌ ዳያሌክት ችግር ትግሬውም ኦሮሞውም ጋር አለ። በኔ እይታ ጉራጌ በብሄርተኝነት አስተምሮ በትግሬውና በኦሮሞው ቢያንስ በገማሽ ምዕተ አመት ተቀድሟል።

የአጋሜና የጋላ ብሄርተኝነት ከ50 አመት በላይ ሲጮህበት ስለነበረ አሁን ሰርፆ "እኛና እነሱ" በሚለው የፉክክር ግልቢያ ማሕበረሰባቸውን ለአንድ አላማ አሰልፈው ሌላውን እየበዘበዙና እያዳከሙ የሚሄዱበት ሁኔታ ነው ያለው።

የአማራ ብሄርተኝነትም ከተኛበት የተቀሰቀሰው የዛሬ 6 አመት በመሆኑና ገና አታጋይ ድርጅት ስላልፈጠረ ተጠቂ ሆኗል። ይህን የብሄርተኝነት ጨዋታ ሕገ መንግስቱ የሚያበረታታ ሲሆን አላማውም ኢትዮጵያን እስከሚችሉ ድረስ መበዝበዝ ካልቻሉ ደግሞ መበታተን አጋሜዎች የሄዱበት ጎዳና ሲሆን ጋላም አዋጪና ጠቃሚ ነው ብሎ እየነጎደበት ነው።

የአማራ ብሄርተኝነት ይህን ተረድቶ በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ስለተረዳ ጉዞውን ሃ ብሎ ሲጀምር ዘረኝነት አይበጅም ብለው አማራን ለማዳከም የሰሩት ጉራጌዎች ኤሊቶች ነው አንተንም ጨምሮ። አሁን ጨዋታው ስለገባህ ደስ ብሎኛል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30667
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በነገው ቀን የጉራጌ ምክር ቤት ክልልነት ላይወስን ይችላል! ጉራጌ ለምን ተከፋፈለ?

Post by Horus » 11 Aug 2022, 01:29

ምስራቅ፣
እኔ አንድም ቀን አማራ ብሄረተኛ ስለሆነ ተገንጣይና የኢትዮጵያ አደጋ ይሆናል የሚል ሃሳብ ባንጎሌ አልፎም ካፌ ወጥቶም አያውቅም ። ለምሳሌ ዛሬ እኔ ጉራጌ ክልልነት መብቱ ነው ብዬ ስከራከር በጉራጌ ወስጥ ለመሪነት ከሚወዳደሩት ፓርቲዎች ውጭ አንድም ሌላ ብሄር ወይ ጎሳ ጉራጌን እንዲደግፍ ጥሪ አድርጌ አላውቅም ። ያ ትክክል አይደለም ። አንዳንድ የአማራ ብሄር ፖለቲክኞች የሚሳሳቱት አንድ ጎሳ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ከሆነ አውቶማቲካሊ አማራ ያነሳውን ጥያቄ መደገፍ አለበት የሚል ስሜት ስለነበራቸው ነው ። ሌላው ቀርቶ አብን እንኳ ወልቂጤ ስብሰባ አድርጎ ጉራጌዎችን ወደ ድርጅቱ ሊመለምል ሞክሯል። እንደዚህ ያለ ህሳቤ ያካባቢው ኦሮሞች ከሚሞክሩት አይለይም ለኛ ማለት ነው ።

ጉራጌ የፕሮፌሰር አስራት ደጋፊ ነበር ። ሰንጋ ታርዶ መዋጮ ተደርጎላቸዋል ። ያ ማለት ግ ን ጉራጌ ያማራ ፖለቲካ ተለጣፊ ነው ማለት አይደለም ። ኦሮሞ ስለ ከበበን የሱ ተከታይ ሊያደርገን ይሞክራል ። ስህተት ነው ። አይደለም ሌላ ጎሳ ጉራጌ በውስጡ እርስ በርሱ በጣም ነጻ የሆነ ማህበረ ሰብ ነው ።

በትክክል ያልከው አማራም ሆነ ጉራጌ ለጎሳ ፖለቲካ አዲስና ፋራ ነው ። ያ ደሞ በጣም ጥሩ ነው ። ምናልባት ከኢትዮጵያ መገንጠል በኤርትራ ያበቃው አማራና ጉራጌ መንገዱን ስለዘጉት ይሆናል ።

እኔ ኦነግን ከቆረቆሩት በጣም የቅርብ ጓደኞች ነበሩኝ ። የነሱ መሰረታዊ ፕላን አቢሲኒያ የተባለች ካባይ በላይ ያለው አገር ትተው ኢትዮጵያ የሚባል ካባይ በታች ኩሻዊ አገር መቆጣጠር ነበር ። በዚህ እቅድ ውስጥ እንደ ጉራጌ ያሉ የሸዋ አካባቢ ያሉ የሴም ሕዝቦች ደንቃራ እንደ ሚሆኑባቸው ያውቁ ነበር ። ይህ ህልም ዛሬ ድረስ አለ ።

ለምሳሌ ነገ በሚጸድቀው ወይም በሚወድቀው ክለስተር ስብሰባ ጉራጌ የሚለው ስም ይደለዝና ዛሬ ጉራጌ የምንላቸው ህዝቦች ከአበሽጌ እስከ ሶዶ እስከ ወለኔ በ3 አዲስ ዞኖች ስም ብቻ ነው የሚጠሩት። ስለዚህ ጉራጌ የሚለው ሕዝብና ቃል ለማጥፋት ነው አባ ዱላ ሌት ተቀን የሚሰራው ። እመነኝ ያካባቢያችን ትግልና ቀውስ ነገ ይለይለታል ።

ስለሆነም አምራ ኢትዮጵያን ባዲስ መንገድ ለማዋቀር የምር ፖለቲካ ንቅናቄ ሲጀም ጉራጌ ድግሱ ላይ ይገኛል። ግን ጉራጌ አማራን እንደ ሚያክበር ሁሉ አማራም ጉራጌን ያክብር ። ጉራጌ አክራሪ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስላለ ቻ አማራ አቅቶማቲክ ደጋፊዬ ነው ሊል አይችልም፣ አማራም እንዲሁ! ዘመናዊ ጥቅማችንን ማጋጠምና ስርዓታዊ ትብብርና ህብረት ማድረግ ነው ያለብን!

eden
Member+
Posts: 9193
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: በነገው ቀን የጉራጌ ምክር ቤት ክልልነት ላይወስን ይችላል! ጉራጌ ለምን ተከፋፈለ?

Post by eden » 11 Aug 2022, 10:25

Horus wrote:
10 Aug 2022, 18:14
በነገው ቀን የጉራጌ ምክር ቤት ክልልነት ላይወስን ይችላል!
Good call Horus, looks like you saw it coming:

Please wait, video is loading...

Post Reply